የኦሮሞን ህዝብ ለማደናገር ሸኔ በሚል የተደራጀው አሸባሪ ቡድን እድል ተሰጥቶት ወደ ስልጣን ከመጣ በቀሉ የሚከፋው በዋናነት በኦሮሞ ህዝብ ላይ ነው።
የሕወሓትና የሸኔ ጥምረትም የስም ልዩነት ካልሆነ በስተቀር ሁለቱም አንድ ናቸው ሲሉ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ጉዳይና ደህንነት ቋሚ ኮሚቴ አባል እና የኦነግ መስራች የሆኑት ዲማ ነገዎ(ዶ/ር) አስታወቁ።
ዶ/ር ዲማ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በሰጡት አስተያየት፣ አሸባሪው ሕወሓትና ሸኔ የስም ልዩነት ካልሆነ በስተቀር በተግባርም በዓላማም የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች በመሆናቸው ሁለቱን የተለያዩ አካላት አድርጎ ማየት አይገባም።
አሸባሪው ሕወሓት ዛሬ ህዝቡን ለማደናገር የኦሮሞ ህዝብ ወገንተኛ ለመምሰል ከፍተኛ መፍጨርጨር እያደረገ መሆኑን ያነሱት ዶ/ር ዲማ፣ ዳሩ ግን በታሪክም ሆነ በተግባር ወደኋላ መለስ ተብሎ ከተቃኘ ቡድኑ በማስተር ፕላን ምክንያት በርካታ የኦሮሞ ወጣቶች በጠራራ ፀሐይ ያለምንም ርህራሄ በጥይት የፈጀ፣ ይሄ ሳያንስ የእሬቻ በዓል ለማክበር የወጡ የኦሮሞ ንጹሃንን በመጨፍጨፍ ጥቁር ጠባሳና ዘግናኝ ድርጊቶችን ጥሎ ያለፈ ቡድን መሆኑን አስታውሰዋል ።
የሽብር ቡድኑ ፍላጎት ትናንትም ዛሬም ኦሮሞን በመስበር የኦሮሞን ሀብት መውረስ መሆኑን የጠቆሙት ዶ/ር ዲማ፣ ለዚህ ዓላማ ማሳኪያም እውነተኛ የኦነግ ታጋዮችን በመግደል እንዲሁም በማሰር በሕይወት የተረፉትን ከአገር በማባረር ከአሥር ዓመታት ወዲህ ደግሞ ተላላኪውን በማደራጀትና በኦሮሞ ስም አምሳያውን ቡድን በማቋቋም ኦሮሞን የማደናገር ሥራ እየሠራ መሆኑን ተናግረዋል።
ቡድኑ ኦሮሞን ለማደናገር በኦሮሞ ስም ሸኔ በሚል ስም ተደራጅቶ መምጣቱ ምናልባት ለማያውቁት ለአንዳንዶቹ ማደናገሪያ ቢሆንም እውነታው ግን የሕወሓት ትልቁ ዓላማ እንደ አጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ በተለየ መልኩ ደግሞ የስልጣኑን እድሜ ያሳጠረውን ኦሮሞን ህዝብ ክፉኛ ለመበቀል መሆኑ መታወቅ አለበት ያሉት ዶ/ር ዲማ፣በቡድኑ አምባገነናዊ አገዛዝ በግፍ ያልተገደለ፣ያልተሰቃየና አገር ጥሎ ያልጠፋ ብሔር ባለመኖሩ የቡድኑ ዳግም ወደ ስልጣን የመመለስ ቅዠት ከንቱ ለማድረግ በጋራ መቆም ጊዜው አሁን ነው ብለዋል።
አሸባሪው ሕወሓት ትንሽ ቀዳዳ አገኝቶ ወደ ስልጣን የመመለስ እድል ካገኘ ሁሉም ኢትዮጵያዊ አንገቱን ደፍቶ የሚኖርባት የሰቆቃ ምድር እንደምትሆን የተናገሩት ዶክተር ዲማ ህዝቡ አገሩን ከምስቅልቅል፤ ራሱንም ከስቃይ ለመታደግ ብቸኛው አማራጭ በጋራ መታገል መሆኑንም አስምረውበታል።
በመጨረሻም የሽብር ቡድኑ በሸረበው ሴራ የህይወት መስዋዕትነት በመክፈልና በመፈናቀል እንዲሁም በውጭ ኃይሎች ጫና ሳይንበረከክ የጋራ ጠላቶቹን በአንድነት በጽናት እየተፋለመ ላለ ለኢትዮጵያ ህዝብም ምስጋና አቅርበዋል።
ምንጭ :ኢ.ፕ.ድ
- ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር ውስጥ ናት፤ በጾሙ ማቅ ለብሰው በንስሃ ችግራቸውን ይፍቱየኢትዮጵያ ታሪክ ቁንጮ እንደሆነች የሚመሰከርላትና እጅግ ውብ ስብዕና ያላቸው አባቶች የሚጠቀሱላት ዕድሜ… Read more: ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር ውስጥ ናት፤ በጾሙ ማቅ ለብሰው በንስሃ ችግራቸውን ይፍቱ
- ሕብረቱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ለዩክሬን ጦር መሳሪያ ግዢ ሊያውል ነውየአውሮፓ ሕብረት በአባል ሀገራቱ እንዳይንቀሳቀሱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ዩክሬንን ጦር… Read more: ሕብረቱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ለዩክሬን ጦር መሳሪያ ግዢ ሊያውል ነው
- ሳኡዲ የምታስገነባው አዲስ ከተማ – “ኒዮም ሲቲ” (Neom City)በረሃን ወደ ከተማነት የመቀየር ጥበብ ልንለው እንችላለን፡፡ ከ1 ትሪሊየን ዶላር በላይ የሚፈጅ… Read more: ሳኡዲ የምታስገነባው አዲስ ከተማ – “ኒዮም ሲቲ” (Neom City)
- Ethiopia, Somalia dispute won’t transform into turmoil for the Horn of Africadeal between Ethiopia and Somaliland has sent waves of debates throughout the… Read more: Ethiopia, Somalia dispute won’t transform into turmoil for the Horn of Africa
- በአማራና ትግራይ ክልል ያሉ የወሰን ይገባኛል ጥያቄ በህዝብ ውሳኔ እንዲቋጭ ስምምነት ተደረሰትህነግ በበላይነት የሚመራው ኢህአዴግ ከፈርሰ በሁዋላ የተነሳውን ጦርነት ተከትሎ የአማራ ክልል ”… Read more: በአማራና ትግራይ ክልል ያሉ የወሰን ይገባኛል ጥያቄ በህዝብ ውሳኔ እንዲቋጭ ስምምነት ተደረሰ