“በወሎ ህዝብ ውሎና ክራሞት ዙሪያ ግምገማ ይደረጋል፤ የቃለ-መሃላ ማረጋገጫ ይዘጋጃል”

ማስታወሻ—በሰላምና በነፃነት የመወለድ መብት ተነፍጓቸው በመንገድ ዳርና በካምፖች ውስጥ ለተወለዱት ውድ ህፃናት!

“ ኢንሻአላህ! ለተከታታይ ትውልድ የጋራ ደህንነት ሲባል የቃለ-መሃላ ማረጋገጫ ይዘጋጃል፣ ተራና አፍራሽ አፈንጋጭነት ቦታ አይኖረውም። ዳግም እንደዋዛ የምንገብረው ሀብት፣ ህይወት፣ ክብርና ታሪክ አይኖርም!”

By – Yesuf Ibrahim (Haji Nesrellah) የአብን ከፍተኛ አመራር

ወራሪው ስብስብ የቁስ ሰቀቀኑን ለማስታገስ ከተማና ቤታችንን አራቁቷል። ለዘረፋና ግድያ ሲግተለተል አጋፋሪዎቹ “Loading” በሚል የፈረንጅ ቃል ላይ ወፍራምና ቀይ የቃል አጋኖ ምልክት አስከትለው ሃሴት ሲያደርጉ ነበር። But, the series of “Loading” bravado turned to a continuous “Unloading” in total disarray!

ግን፣ ግን – የስደትና የሰቆቃ ምዕራፍ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ሊዘጋ ይገባል! ወደፊት ለጠኔና ለጥላቻ ማራገፊያ የሚሆን ህዝብ አይኖርም! ማድረግ ቀርቶ ማሰብ ከባድ ይሆናል! ይህ ትንቢት ሳይሆን በቃል ኪዳንና በስራ የሚገለፅ ነው።

ቆቦና ወልዲያ ባይናችን ዞረዋል፣ እናት ዓለም ደሴ እጅግ ተናፍቃለች! ትላንት የኛ ቀን እንዳልነበር ሁሉ ነገ የነሱ ቀን አይሆንም! ነገ ሌላ ቀን ነው፣ እሱም የኛ ይሆናል።

በወገናችን ላይ የደረሰውን ሰቆቃና ምስቅልቅል በጨረፍታ ተመልክተናል። ሆኖም ለቅሶ ወንዝ አያሻግርም፣ መፍትሄው ትግል ብቻ ነው። “ሊያልፍ ውሃ አደረገኝ ድሃ” የሚባለው አይነት! በወሎ ህዝብ ውሎ ዙሪያ ግምገማ ይደረጋል፣ አቅጣጫ በማስቀመጥ ወደ ስራ ይገባል!

የጋራ ፖለቲካና ደህንነት ጉዳያችን ይሉኝታ፣ መዘናጋት፣ መጠላለፍ፣ ሀሜት፣ ፌዝ፣ የዋህነት፣ አፈንጋጭነት የሚባሉ ስምሪቶችን፣ ቅይጥ፣ ውህድ፣ አቃፊ፣ የመሳሰሉ የሽንፈት ማጣቀሻዎችን አያስተናግድም።

ለተከታታይ ትውልድ የጋራ ደህንነት ሲባል የቃለ-መሃላ ማረጋገጫ ይዘጋጃል፣ ተራና አፍራሽ አፈንጋጭነት ቦታ አይኖረውም። ዳግም እንደዋዛ የምንገብረው ሀብት፣ ህይወት፣ ክብርና ታሪክ አይኖርም!

ወያኔና ጀሌዎቹ እርማችሁን አውጡ፣ ጥይት እንጂ አስቤዛ ታገኙም። የሰርጎ ገቦች ድንኳን ይቀደዳል፣ ባንዳዎች እርቃናቸውን ይቀራሉ!

ሰምና ወርቅ፣ ሽለላ፣ ቀረርቶ፣ ጋቢ፣ ጃኖና ቡልኮ የነጭ ለባሾች ከለላ አይሆኑም! ከጀርባ ለወጉን ወዬላቸው!

ማስታወሻ—በሰላምና በነፃነት የመወለድ መብት ተነፍጓቸው በመንገድ ዳርና በካምፖች ውስጥ ለተወለዱት ውድ ህፃናት!

ክብር— ነፃ ሆና ለኖረችውና የነፃነት ተምሳሌት ለሆነችው ሀገራችን—ኢትዬጵያ!

ክብር— ነፃነቱን ጠብቆ ላቆየው—የኢትዬጵያ ሕዝብ!

ክብር—ለጀግኖች አርበኞቻችን!

ሽንፈትና ውርደት— ለፋሽስቶች፣ ለዘረኞችና ለባንዳዎች!

Now—Jam in Jama, Break in Bati, Slay in Shewarobit, Grind in Gashena, Tear in Tselemet.

Next—Wow in Woldia, Dove in Dessie, Kindle in Kombolcha.

What’s more?—Show up in Shire and Meet in Mekele!

Related posts:

«ሕወሓት ጦርነትን እንደ አምልኮ የሚቆጥር ቡድን ነው» – ፕሮፌሰር ሀረገወይን አሰፋ
«በሕገወጦች ላይ ያለ ምኅረት እርምጃ መውሰድ አለብን፤ ይህ የመንግሥት ተግባር ነው» የአማራ ክልል
125 አዳዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ
«በአገሩ መከላከያ ላይ አፉን የሚከፍት ሕዝብ የለም፤ መንግስትም አይታገስም» ክብር ለመከላከያ ሰራዊት!!
በኢትዮጵያና ቱርክ መካከል የተደረገውን የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት ምክር ቤቱ አጸደቀ
የሞት ፍርደኛው የ25 ዓመታት ሰቆቃ! ከመሬት በታች የታፈኑት አባት
«ኢትዮዽያን ማስቀጠል ከሚፈልጉት ጎን በመሆናችን የሚከፋ ከአለ እርሱ መፍረሷን የሚናፍቅ ብቻ ነው!»
ደብዳቤ ለኢትዮጵያ - ከቢልለኔ ስዩም
የዓለም ባንክ የ300 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ፈረመ
"እናቴ ፍጹም እስር ቤት እንድትገባ አልፈግም" ብሎ እግሩን ያጣው ወጣት ምስክርነት ለሮይተርስ
"አልዘምትም" ወይም "ከጠላት ጎን እሰለፋለሁ" ማለት ሲቻል ማውሰብሰብና ማድበስበስ አይገባም!
አብዱላሂ ፋርማጆ ለአዲሱን ፕሬዝዳንት «ሁሉም ወገኖቼ እንዲደግፉህና እንዲጸልዩልህም እጠይቃለሁ»
መንግስ የጸጥታ ሃይሎች ለየትኛውም ዓይነት ትንኮሳ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ማድረጉን አስታወቀ
በትግራይ 5.2 ሚሊዮን ሕዝብ ዕርዳታ እየደረሰ ነው፤ ከሺህ በላይ የጭነት መኪኖች ታግተዋል፤ 76 ቢሊዮን ብር ወደ ትግራይ ተልኳል
የደህንነት ጥናት አዲሱ ምዕራፍ - ጂኦስፓሻል ኢንተለጀንስ

Leave a Reply