የ”አብይ የትኛው ግንባር ናቸው?” ራስ ምታት፤ትህነግ “ከተማ ትቼ ገጠር ገባሁ”

“ቀድሞ በማሰብ ወደር የለውም” በሚል የሚያውቋቸው የሚመሰክሩላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በድነገት ከባልደረቦቻቸው ጋር የወሰኑት ውሳኔ “ነገር አለሙን በታትኖታል” ለሚለው አስተያየት ማረጋገጫ የሚሆን ማስረጃ መሰራጨት የጀመረው ወዲያው ነው። ” ስውሩ ሰው” የት መሽገው እንደሚያታኩሱ መረዳት ያቃታቸው ነጮቹ ብቻ ሳይሆኑ ራሱ ትህነግም ነው። ትህነግ ግራ መጋባት ብቻ ሳይሆን በግንባር እየተበተነ ለመሆኑ ራሱ እምነት ክህደት ቃሉን ሰጥቷል። ከተማ ትቶ ገጠር ገጠሩን እንደመረጠ አስታውቋል።

“ነገረ አለሙን ሁሉ በታትኖታል”

አገሪቱን እያስተዳደረ ያለው የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች ከአገር ለመውጣት ሰልፍ መያዛቸውን፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተማሩበት ደቡብ አፍሪካ ቤት ገዝተው ለመሸሽ መዘጋጀታቸውንና ቤተሰቦቻቸውን እንደላኩ፣ አዲስ አበባ ዙሪያ ያሉ የኦሮሚያ ከተሞች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ፣ የኦሮሚያ አመራሮች ከብልጽግና እንደከዱ፣ የሶማሌ ክልል ከሚመጣው መንግስት ጋር ለመስራት እንደተስማማና ተመሳሳይነት ያላቸው ዜናዎች በየደረጃው ሊለቀቁ ዝግጅቱ አልቆ ነበር። ሁሉም ዝግጅት በገሃድ እጁ የደረሰው መንግስት አስቀድሞ በመሰብሰብ በድንገት ” ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከነገ ጀምረው ወደ ጦር ሜዳ ያመራሉ” ሲል በሰበር ዜና አሰራጨ።

መለስ ዜናዊ – ለትውስታና ለብስጭት ንፅፅር

በደርግ ወቅት ሻለቃ ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ ከሲአይ ኤ ጋር መስትሮ እንዲከሽፍ አድርጎ ያዘጋጀው መፈንቅለ መንግስት ቀደም ብሎ ኤርትራ ላይ ተፈጽሞ ስለነበር፣ ከኤርትራ በሚተላለፈው ሬዲዪ ዜናው እየተደጋጋመ መንግስት መውደቁ ሲነገር ታጋዮች ” መንግስቱ ወደቀ” በሚል ደስታቸውን እየገለጹ በጭፈራ እነ መለስ ካሉበት ዋሻ ይደርሱና ሬዲዮውን ያሰሙታል። መለስም ሬዲዮውን ሰምቶ ሲጨርስ ሬድኗን ከሰከሳት። ለምን? መፈንቅለ መንግስቱ ተሳካ ማለት የኢትዮጵያ ሰራዊት ሳይበተን የጣምራ ወይም አዲስ መንግስት ስለሚቋቋምና ትህነግ እቅዱ ስለሚከሽፍ!! ልክ እንደዚህ ነበር የአብይ አሕመድ ዜና ለፕሮፓጋንዳ ዘመቻ የተሰለፉትን ሰነዳቸውን ያስከሰከሰው።

May be a Twitter screenshot of ‎2 people and ‎text that says '‎Martin Plaut @mart... 23 Nov 21፤ 21 Anyone have a photograph of PM Abiy on the battlefield? I have seen nothing yet... 256 tר 85 259 Edao Dawano @EdaoDawano Replying to @martinplaut Do you have a recent picture of Debretsion? 8:33 pm. 23 Nov 21. 21 Twitter for iPhone‎'‎‎

አብይ

የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወደ ጦር ግንባር መዝመት ያልተጠበቀ ዜና መሆን ከላይ የተገለጸውን የፕሮፓጋንዳና የተግባር ስልት በደቂቃ ውስጥ እንደምናምንቴ ጉዳይ አደረገው። ይህ ብዙ የተለፋበትንና ትህነግን በግርግር ገፋፍቶ ወደ ስልታን ለመመለስ የተወጠነ ሴራ እንደ ባሉን ያስተነፈሰው የተቅላይ ሚኒስትሩ የግንባር ዘመቻ በሳቸው ብቻ ያበቃ ሳይሆን መላ የፓርቲውን አመራሮች፣ መላው የክልል መሪዎችና ካቢኔዎቻቸው፣ እንዲሁም እንደ ሃይሌና ፈይሳ ሌሊሳ፣ የኪነትና የምድረክ ሰዎች … በየቀበሌው፣ መስሪያ ቤቱ እንዲሁም በግንባር ላለው ሃይል እንደ ነዳጅ ሆነና በቀናት የትህነግን ቁንጮ ወታደራዊ አመራሮች ያደቀቀ ዜና ይዞ መጣ።

ይህ ብቻ አይደለም በርካታ ከተሞች መለቀቃቸው ተሰምቷል። መንግስት የጦር ሜዳ ውሎን በህግ ስልጣን ከተሰጠው አካል ውጪ ማስታወቅን በመከለከሉ ዝርዝር ውስጥ መግባት ባያስፈልገም ትህነግ ትናንት ባወታው መግለጫ ይህንኑ ያመነ ወይም የተቀበለ ይመስላል። ትህነግ እንዳለው ለከተሞች ሲባል ሰራዊቱ ገጠር ገጠሩን እየገሰገሰ መሆኑንን ነው። መንግስት 12 ጀነራልና ኮሎኔሎችን እንደደመሰሰ ባስታወቅ በሰአታት ጊዜ ውስጥ ትህነግ ባሰራጨው መግለጫ የመኮኖቹን መሞት በዝምታ ነው ያለፈው ወይም ለማስተባበል እንኳን አልሞከረም።

ስማቸው ተጠቅሶ የተለቀቁና በምስልና በማስረጃ ዜናቸው ይፋ የሆኑ ከተሞችን አስመልክቶ ምንም ያላለው የትህነግ መግለጫ ሃያሉ ወደ ፍጻሜ እየገሰገሰ እንደሆነ ከማመልከቱ ውጭ የት እንደደረሰና ምን ያህል እንደቀረው ይፋ አላደረገም። አምባሳደር ብረሃነ ገብረክርስቶስ ሰሞኑንን በሚስጢር በተደረገ ስብሰባ ላይ ሲናገሩ እንደተሰማው ግን ወደ አዲስ አበባ ማምራት እንደማይቻል ነው። ፌልትስ ማንም ዘመኑ 1983 ባለመሆኑ እንዲህ ያለው ሃሳብ እንደማይቻል ለትህነግ ሰዎች በግልጽ እንደተነገራቸው አመላክተዋል። ሕዝብም ትህነግን እንደማይፈልግ ባገኘው ሁሉ አጋጣሚ እያስታወቀ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወደ ግንባር ማምራታቸው ከተሰማ በሁዋላ ዕቅዳቸው መፍረሱ ካበሳጫቸው የሚዲያ ጦር አውርዶች መካከል አንዱ ማርቲን ፕላውት ነው። ማርቲን ፕላውት “የጠቅላይ ሚኒስትሩን የግንባር ፎቶ ያያችሁ” ሲል በአደባባይ ደጋግሞ በቲውተር ገጹ ” እባካችሁን አጋሩኝ፣ የት ናቸው” ሲል ተማጽኗል። ራሱ የትህነግ ሚዲያም ይኑረው አይኑረው ባይታወቅም 11 ሚሊዮን ብር እንደሚከፍል ጠቁሞ ” ያሉበትን አመላክቱኝ” ሲል ተዛብቷል።

May be an image of 1 person and text that says 'Tweet Martin Plaut @martinplaut + + Sad'
ሃይሌ እዘምታለሁ በማለቱ ማርቲን ፕላውት ማዘኑንን የገለጸበት

ከሁሉም በላይ ግን አስገራሚ የሆነው የኦሎምፒክና የዓለም ጀግናው ሃይሌ ገብረስላሴ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ተከትሎ ወደ ግንባር የመዝመት ሃሳቡን ይፋ እንዳደረገ ማሪን ፕላውት ” አዝናለሁ” ሲል እምባ አሳይቷል። ለምን አዘነ? እስካሁን ምንም ፍንጭ ማገኘት ያልቻሉት የሚዲያ አስተኳሾች የተቅላይ ሚኒስትሩን የግንባር ምስል ለማግኘት ቢገፉም፣ ቢጥሩም፣ ቢተናኮሉና በማንቋሸሽ መልኩ ቢሞክሩም ሰሚ ማግኘት አልቻሉም።

የመጨረሻው የንዴቱ ጣሪያ ላይ ቁጭ ብለው በሚያስታውቅ ደረጃ አብይ አህመድን መራገም እየቀራቸው አስተያየታቸውን የሰጡት የሙሉ ጊዜ የትህነግ አቅጣጫ አመላካችና መረጃ አወናቻፊው ኖርዌጂያኑ ፕሮፌሰር ትሮድቮል ሼትል ናቸው። ” አብይ ግንባር ይሁን ይደበቅ” አናውቅም ሲሉ ያስታወቁት።

በግንባር ወታደሮችና ሚሊሻዎች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የግንባር መገኘት ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የሞራልና የአንድነት ስሜት እንደተሰማቸው ሲገልጹ፣ ድል በድል እየዳደራረቡ ሲገሰገሱ እየተሰማና ትህነግ ” ስልታዊ” ባለው ምክንያት ከተማ እንዳይጎዳ ገጠር ገጠሩን ወደ ፍጻሜ ለመገስገስ መሞከሩን በገሃድ እያስታወቀ፣ ፕሮፌሰሩ ” አብይ ግንባር ይሁኑ ይደበቁ የሚታወቅ ነገር የለም” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያሉበት ከፍታና ቀበሌ እንዲነገራቸው በዚህ የቴክኖሎጂ ዘመን ላይ ሆነው ይሞግታሉ።

እሳቸው ብቻ ሳይሆኑ አብዛኞች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያሉበት ግንባር ብቻ ሳይሆን ገዢ መሬቱ የት እንደሆነ የሚያሳይ መረጃ እንዲሰጣቸው ይከጅላሉ። ሰሞኑንን 12 ወታደራዊ መኮንኖቹ የተሸኙበት ትህነግ፣ በርካታ ከተሞች የተነጠቀው ትህነግ አብይ የት እንዳሉ ለማወቅ ቢቧጥጥም፣ ነጮቹ የሚዲያና የፖሊሲ ተውጊዎች ቢወተውቱም ድሉና የድሉ ፍንጭ እንጂ ስውሩ ሰው የሉም። መረጃቸውንም የሚያወጣ ጅል ዜጋ እልተገኘም። ስውሩ ሰው ግን ትህነግን ለጊዜው ከከተማ ትግል መውጣቱን ለደጋፊዎቹ እንዲናዘዝ አድርገውታል። ፌልትስ ማን እንዳሉት ዓላማው የትህነግን ወራሪ ሃይል ከወረራቸው አካባቢዎች ማስለቀቅ ብቻ ነው። ይህ በሁሉም ወገን የታመነበት ይመስላል። ኮምቦልቻና ደሴ ወደ ቤታቸው ሲቀላቀሉ ሁሉም ነገር ይቀየራል።

Leave a Reply