
የአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር የሀገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ እና የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን የኑሮ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ የቤት ኪራይ ዋጋ መጨመርም ሆነ ተከራይን ከተከራየበት ቤት ማስለቀቅ እንደማይቻል ውሳኔ ማተላለፉ ይታወሳል፡፡
አስተዳደሩ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ፥ ” ይህ ያለንበት ወቅት አገርን ከተጋረጠባት የህልዉና አደጋ የማዳን በመሆኑ ውሳኔውን ለቀጣይ ሶስት ወራት ባለበት እንዲጸና ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ” ብሏል።
በመሆኑም ከዛሬ ሕዳር 17 / 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለቀጣይ ሶስት ወራት የቤት ኪራይ ዋጋ መጨመርም ሆነ ተከራይን ማስለቀቅ ፈጽሞ የተከለከለ መሆኑን ገልጿል።