ፕ. ይስሀቅ የሚመሩት የሰላም ልማት ማዕከል በህግ ተዘጋ፤ ኢሌኒ “የለሁበትም” አሉ፤ መስራች መሆናቸው ማስረጃ ተገኘ

Image

አገር ለማፍረስ በድብቅ ሲወያዩ የነበሩትን የእነ ፕሮፌሰር ይስሀቅ ኤፍሬም፣ ኢሌኒገብረመድህ፣ አሸባሪው ብርሀነ ገብረክርስቶስና አጋሮቻቸውን አካቶ ውይይት ያዘጋጀው የሰላም ልማት ማዕከል ሴራው በሚጨበጥ ማረጋገጫ ይፋ መሆኑንን ተከትሎ ድርጅቱ በህግ መዘጋቱ ተገለጸ። ኢሌኒ ገብረመድህን “የለሁበትም” ሲሉ ምላሻቸውን በማህበራዊ ገጽ ቢያሰራጩም ሂደርቱን ሲያዘጋጁ የነበሩ ቅድሚያ አስተባበሪ እንደሆኑ መረጃ ቀረበባቸው።

የሲቪል ማህበረሰቦች ባለስልጣን ለኢፕድ በላከው ደብዳቤ እንዳስታወቀው ድርጅቱ ፈቃዱ የተሰረዘው የድርጅቱ ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሀቅ፣ ኢሌኒገብረመድህ፣ አሸባሪው ብርሀነ ገብረክርስቶስና አጋሮቻቸው በአንድነት በድብቅ መንግስት ለመገልበጥ ሲያሴሩ የሚያሳይ ቪዲዮ ይፋ ከሆነ በሁዋላ እንደሆነ ተመልክቷል።

በፕሮፌሰር ኤፍሬም አወያይነት የቀድሞ የአሜሪከና አውሮፓ ጡረተኛ ዲፕሎማቶች የአሸባሪው ህወሓት አባላትና የጥቅም ተጋሪዎች፣ እንዲሁም የሶማሌ አሜሪካ አምባሳደር ያማምቶ የተካተቱበት ሲሆን፣ የተካሄደውንና ኢትዮጵያን የማፍረስ ውይይት ከፍተኛ ቁጣ ያስነሳ መሆኑ ይታወሳል።

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አንቀጽ 4 ንዑስ አንቀጽ 9 መሰረት፤ “የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መምሪያ እዝ የሀገርን ህልውናና ሉዓላዊነት እንዲሁም ሰላማዊ ዜጎችን ለመጠበቅ አስፈላጊ ነው ብሎ ሲያምን፤ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ድጋፍ ያደርጋል ተብሎ የሚጠረጠር የሲቪል ማህበር ድርጅትን ፈቃድ እንዲሰረዝ ያዛል” በሚለው መሰረት የሰላም ልማት ማዕከሉ ፈቃድ ተሰርዟል።

ድርጅቱ ከውጭ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚደረግለት መንግስት መረጃ ማግኘቱን፣ ሚሚ አለማየሁ በሚባሉ ሴት የሚመራ ሲሆን ሴትየዋ እነ ኤፍሬም በዋይት ሃወስ ተጋብዘው እንደተገኙና በርካታ

No photo description available.

በተመሳሳይ ስብሰባው ከመካሄዱ ከቀናት በፊት “እንዴት ቤቴ ይበረበራል” በሚል ከፍተኛ የተቃውሞ ሃሳብ ሲያሰራጩና ዜና ሲያደርጉ የከረሙት ዶ/ር እለኒ ገብረመድህን በዚህ የሽግግር መንግስት ምስረታ ምክክር ላይ በይፋ መታየታቸው ጉዳዩን የተጋጋለ ዜና አድርጎታል። በመግስት ሚዲያዎችም ሆነ በማህበራዊ ገጾች እጅግ የከረረ ተቃውሞና ውግዘት የደረሰባቸው ዶክተር ኢሌኒ ” የለሁበትም” የሚል መረጃ በትነዋል።

ዶክተርዋ በፌስቡክ ገፃቸው በእንግሊዝኛ ቋንቋ ባሰፈሩት መልዕክታቸው ስብሰባውን ያዘጋጀው የሰላምና ልማት ማዕከል የሚባል ዓለምአቀፍ ተቋም መሆኑን ጠቅሰው የስብሰባ ተሳትፏቸውን በተመለከተ በሰላም ጉዳይ መምከራቸውን ጠቁመዋል። ስብሰባው ከቀጣሪ ድርጅታቸው (UN ) ጋር እንዲሁም በአዲስአበባ መኖርያ ቤታቸው መፈተሽ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም ብለዋል።

See also  በመንግስት የሚሰጡ መግለጫዎች ሁሉ የሚያመለክቱት የትግራይን ህዝብ ሳይሆን ወንጀለኛውን ህወሓት ብቻ ነው-- ወቅታዊ ሁኔታ መረጃ ማጣሪያ

ስለ ድርጅቱ ካብራሩ በሁዋላ “የኢኮኖሚ ባለሙያ ነኝ። በቅንነት ከጦርነቱ በኋላ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እንዴት ሊያንሰራራ ይችላል ብዬ እጠይቃለሁ። ስለኢትዮጵያ፣ ስለአፍሪካ ልማትና እድገት እሰራለሁ። በሽግግር መንግስት ምስረታ ጉዳይ አልመከርኩም።” ብለዋል። በምርጫ ሥልጣን የያዘ መንግስት በህገወጥ መንገድ ለማስወገድ የሚደረግ ሙከራን እንደሚያወግዙም አመልክተዋል። እሳቸው ይህን ቢሉም በስብሰባው መንግስት እንዴት እንደሚወድቅ፣ ከወደቀ በሁዋላ እንዴት የሽግግር መንግስት እንደሚቋቋም … ሲዘረዘር ” በምርጫ የተመረጠ መንግስት ስለመጣልና አዲስ መንግስት ስለመመስረት አይመለከተኝም። የለሁበትም” ሲሉ መቃወማቸው አልተሰማም።

https://twitter.com/jeffpropulsion/status/1464003393249239052?s=20

ይልቁኑም በሽግግሩ ወቅት ስለሚኖረው የኢኮኖሚ ማገገሚያ ምን ዕቅድ እንደተያዘ አሸባሪ ተብሎ ከተፈረጀ ትህነግ መሪ ጋር መቀመጣቸው በራሱ ህግን መጣስ እንደሆነ በደብዳቤያቸው አላነሱም። ወይም አላስተባበሉም።

በግልጽ መንግስት እንዴት እንደገና እንደሚዋቀር፣ እነማን እንደሚካተቱበት በገሃድ በተገለጸበት ስብሰባ ላይ ተቀምጠው ሳለ ” የለሁበትም፤ ኢኮኖሚስት ነኝ…” ማለታቸው ያስገረመውና ቪድዮውን ይፋ ያደረገው ጋዜጠኛ ጄፍ ፔርስ በቲውተር አምዱ ምንጩን ጠቅሶ ዶክተር ኢሌኒ የቡድኑ አንዱ መሆናቸውንና ለዚህ ቡድን ዌብሳይት እንዳዘጋጁ አመልክቷል።

በዚህ ስብሰባ ላይ አምባሳደር ታዬ ተጋብዘው ” ወግዱ” ማለታቸውን ያስታወቀው ጄፍ ዶክተር ኢሌኒ ” አይቀልዱ” አይነት አሽሙር ጋብዟቸዋል።

ቪዲዮው ይፋ እንደሆነ አዲስ ዘመን “በታዋቂነት ስም የተሸፈነው የአሸባሪው ህወሓት ደጋፊዎች ጭምብል እየተገፈፈ ነው” በሚል ርዕስ ዘግቦ ነበር። በአገር ያገኙትን ታዋቂነትንና ሃላፊነትን በመጠቀም መልሶ አገር ለማፍረስ ለአሸባሪው ህወሓት ሲደረግ የነበረው ድብቅ ድጋፍ ጭምብሉ እየተገፈፈ መጥቷል።ኢትዮጵያውን ለውድ ሀገራቸው ሕልውና ከኢትዮጵያ ማኅጸን እስከ አለም ጫፍ መነሳታቸውን ተከትሎ የኢትዮጵያን መፍረስና ደካማ መንግስት መፈጠርን የሚፈልጉት በሌላ ወገን ከተደበቁበት ጉድጓድ ብቅ ብለዋል።የምእራባውያንን ዘመናዊ ቀኝ ግዛት በማስፈጸም ለዘመናት በስልጣን ላይ ቆይቶ የነበረው አሸባሪው ህወሃት በኢትጵያውያን ገድል ወደ መቃብር እየወረደ መሆኑን ተከትሎም ሀገር ከፍ አድርጋ የምታያቸው እነሱ ግን ሀገረን ለማፈረስ ወደ አሸባሪዎች ህወሃትና ሸኔ መቃብር የወረዱ ባለ ጭምብሎች ገሃድ ወጥተዋል።የተሸፈኑበት ጭምብል ጊዜን የማያሸንፍ በመሆኑ በኢትዮጵያዊነት ጊዜ ከሽፋኑ ተገልጦ ሀገርን ለማፍረስ ሲዶልቱ ለአደባባይ አብቅቷቸዋል።አሸባሪው ህወሓትን ከሚቀበርበት ጉድጓድ ለመታደግ የሽብር ቡድኑ አባላት፣ በድብቅ ሽፋን የሚሰጡት ተባበሪዎቹ እንዲሁም ምዕራባውያን የጥቅም አጋሮቹና ዲፕሎማቶች በዙም ያካሄዱት ምሥጢራዊ ስብሰባ ነው የተጋለጠው። ለሽብር ቡድኑ እውቅናቸውን በመጠቀም በድብቅ ድጋፍ ሲሰጡ ጭብላቸው ተገፎ በአደባባይ ከተጋለጡት መካከል ዶክተር እሌኒ ገብረ መድህን፣ ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሐቅን ፣ ፕ/ር ጥላሁን በየነ፣ አምባሳደር በቀለ ገለታ (ቀይ መስቀል)፣ዶ/ር ታደሰ ወሂብ (CDC)፣ ኩለኔ ጀለታ (Uscongress) ዋና ዋናዎቹ ናቸው።እንደ ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሐቅ ያሉት በሀገር ሽማግሌ ስም ሀገርን ለቀኝ ግዛትና ለዳግም ግፍ ለመዳረግ ከጀርባ ሆነው እንደሚዶልቱ በዚህ መረጃ ተረጋግጧል።በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የኢኮኖሚ አማካሪ በመሆን ሀገር ሃለፊት ሰጥታቸው የነበሩት እንደ ዶክተር እሌኒ ያሉት የእናት ጡት ነካሾች በበኩላቸው አሸባሪው ህወሃትን ከሚቀበርበት ወደ ስልጣን መመለስ አለበት ሲሉ ተሰምተዋል።ከነዚህ በተጨማሪም በተሰማሩበት የስራ ዘርፍ ታዋቂ የሆኑ ግለሰቦች የሐሰት ጭምብላቸውን በመጠቀም እና የአሜሪካ አውሮፓ ባለስልጣናትን የማግባባት ሥራ ከጀርባ በማከናወን አሸባሪውን ወደ ስልጣን ለመመለስ የቁም ቅዠት ላይ መሆናቸው በዚህ ምሥጢራዊ ስብሰባ ተጋልጧል።-አካባቢህን ጠብቅ _ ወደ ግንባር ዝመት _ መከላከያን ደግፍ

See also  "ልጆቻችን የት ናቸው?" የትህነግ አዲሱ ፈተና "ግፋ በለው" ሲሉ የነበሩ ሚዲያዎች የከበሩበት፣ የድሃ ልጆች ያለቁበት...

Leave a Reply