“የአገር መከላከያ ሰራዊት ባቲና ኮምቦልቻን ለመቆጣጠር እየገሰገሰ ነው”

ከመንግስት ኮሚኒኬሽን የተሰጠ መግለጫ እንዳመለከተው የባቲና ቡርቃ ከተማ ዙሪያ ተራሮችን ተቆጣጥሪ ባቲና ኮምቦልቻን ለመቆጣጠር እየገሰገሰ ነው። ማምሻውን ኮምቦልቻ በወገን ጦር እንደምትሆን ይገመታል።

” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መላውን የጸጥታ ኃይል ራሳቸው በመምራት የህልውና ዘመቻውን ከዳር ለማዶረስ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ቃል በገቡት መሠረት በግንባር ተገኝተው ቃላቸውን ተግባራዊ እያደረጉ ነው።

በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቁርጠኝነት የተነቃቃው ጀግናው ሠራዊታችን በባቲ ካሳጊታ ግንባር ሲደረግ በነበረው ውጊያ ካሳጊታን አስቀድሞ ከአሸባሪው ሕወሐት ነጻ ያወጣ ሲሆን ወደፊት በመገሥገሥ ቡርቃንና በባቲ ከተማ ዙሪያ ያሉ ተራሮችን ተቆጣጥሮ ወደ ባቲ ኮምቦልቻ እየገሠገሠ ነው።

በአፋር ክልል ፣ በጭፍራ ግንባርም ጪፍቱን ፣ የጭፍራ ከተማንና አካባቢውን ከወራሪው ነጻ አውጥቶ ወደፊት በመገሥገሦ ላይ ነው። ” ያለው የመንስት ኮሙኒከርሽን መግለጫ በደብረበርሃን ዙሪያ ስላለው ሁኔታ ባይገልጽም የተበታተነው የትህነግ ሰራዊት በየገጠሩ ተበትኖ እየተለቀመ መሆኑንና ውጊያው ከአዲስ አበባ 360 ኪሎሜትር መራቁን፣ በ360 ኪሎ ሜትር ርቀት የሚደረገው ውጊያም ሊጠናቀቅ ከጫፍ መድረሱን ከርስፍራው ለመረድፋት ተችሏል።

የአብን ምክትል ሊቀመንበር አቶ ዩሱፍ ኢብራሂም “ደሴና ቆቦን የምናይበትን ቀናትን በጣታችን እየቆጠርን ነው” ማለታቸው አይዘነጋም።

Leave a Reply