የትግራይ የሃይማኖት ጉባኤ የሰላም ጥያቄ አቀረበ፤ ትህነግ ቅድመ ሁኔታ ለመቀበል “እስማማለሁ” ማለቱ ተሰማ፤ ኮምቦልቻና ሃይቅ ተለቀቁ

የትግራይ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለሃይማኖት ተቋማት ” ሰላምን አስቀድመን እንስራ” ሲል ጥያቄ አቅረበ። ትህነግ መንግስት ያቀረበውን ቅድመ ሁኔታ እንደሚቀበል ማሳወቁ ተሰማ። ሃይቅና ኮምቦልቻ በመከላከያ እጅ መግባታቸው ተሰማ።

የትግራይ ቴሌቪዥን አማርኛ ላይ እንደተገለጸው የትግራይ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ፅ/ቤት ሁሉም ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች እንዲሁም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በትግራይ ህዝብ ላይ የደረሰውን እና እየደረሰ ያለውን ግፍና ጭፍጨፋ በስልጣን ጥመኞች አማካኝነት በሌሎች ህዝቦችም ድርጊት ያለማቋረጥ እየተፈፀመ በመሆኑ ይህንን ግፍ እንዲያበቃም ሁሉም ህዝብና የሃይማኖት ተቋማት በሞላ ለሰላም ዘብ በመቆም የህዝባችንን ሰላም አስቀድመን እንስራ ሲል ጥሪ አቀረበ” ሲል ዜናውን በምስል አስደግፎ ይፋ አድርጓል።

የአፍሪካ ህብረትን ምንጮችን የጠቀሰው የአዲስ አበባ ተባባሪያችን እንዳለው ይህ የሃይማኖት ተቋማት ጥሪ ከመተላለፉ አንድ ቀን በፊት የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ለአፍሪካ ህብረት የምስራቅ አፍሪካ የሰላም አምባሳደር መንግስት ያስቀመጠውን ቅድመ ሁኔታ እንደሚቀበል ማስታወቁን አስታውቋል።

ድፍን የአፋር ክልል ከትህነግ ወረራ ነጻ መውጣቱ ይፋ በሆነበትና ባቲና ኮምቦልቻ በአገር መከላከያና በአማራ ልዩ ሃይል እጅ መውደቃቸው በተሰማ ቅጽበት የትግራይ የሃይማኖት ጉባኤ ጽህፈት ቤት ላቀረበው ጥያቄ እስካሁን በገሃድ ምላሽ የሰጠ አካል የለም። ከዚህ ቀደም የትግራይ ኦርቶዶክስ ሲኖዶስ ዋናውን ሲኖዶስ ” አላውቅህም” ሲል በይፋ በመግለጫና በቃለ ምልልስ በተለየዩ መገናኛዎች ሲያወግዝ እንደነበር ይታወሳል።

ዛሬ ጉባኤው ” … ሰላምን አስቀድመን እንስራ ” ሲል ጥሪ ለማቅረብ ያነሳሳው ምክንያት አልተዘረዘረም። ቀደም ሲል ጦርነት ከመከፈቱ በፊት የሰላም አባቶችና እናቶች በትግራይ በመገኘት የዕርቅ ጥያቄ ሲያቀርቡ የትግራይ የሃይማኖት ምክር ቤት አቋም ግልጽ አልነበረም። የሰላም አሳብ እጅግ የሚደገፍ ቢሆንም ጉባኤው ለምን ዛሬ ላይ ይህን ጥሪ እንዳቀረበ ማብራሪያ አለመስጠቱ ማብራሪያ አላስቻለም። ማብራሪያ መስጠት ባይቻልም የአፍሪካ ሕዝብረት ምንጮቹን የጠቀሰው ተባባሪያችን እንዳለው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር መንግስት ያስቀመጠውን ቅደም ሁኔታ በመቀበል ለድርድር ዝግጁ መሆኑንን አስታውቋል።

መንግስት ትህነግ ጦር እንደሚያፈርስ፣ ትጥቅ እንደሚፈታና መንግስትን እንደ መንግስት ተቀብሎ ከወረራቸው ስፋራዎች በሙሉ በመልቀቅ ላደረሰው ውድመት በህግ አግባብ የሚጠየቁ ክፍሎችን ለህግ አሳልፎ እንዲሰጥ የሚል እንደሆነ የተለያዩ ሚዲያዎች ዘግበዋል።

አዲስ አበባ ለመግባት ሰላሳና አርባ ኪሎሜትር እንደቀረው ሲገለጽለት የነበረው ትህነግ ” ከተሞች እንዳይጠፉ የገጠር ትግል ጀምሬ ወደፊት እየገሰገስኩ ነው። የሚሞት መንግስት …” በሚል ሲገልጸውና ” እጅህን ስጥ” በሚል በተደጋጋሚ ጥሪና ማስጠንቀቂያ ሲያቀርብለት የነበረው ሰራዊት ሰሞኑንን ጋሸናንና ላይሊበላን፣ ትናንት ካሳጊናን ዛሬ ደግሞ ባቱና ኮምቦልቻን ተቆጣትሮ ወደ ደሴ እያመራ መሆኑ በሚገለጽበት ቅጽበት የትግራይ የሃይማኖት ጉባኤ ያቀረበው ” ለሰም አብረን እንስራ” ጥያቄ በርግጥም ትህነግ በጦር ሜዳ ድል እንዳጣ አመላክች ሆኖ ተወስዷል። ቢሆንም ግን የሰላም ሃሳብ ምንም ግዜም ቢሆን ሊበረታታ እንደሚገባ አስተያየት ተሰጥቷል።

የአፍሪካ ህብረት ምንጮች እንዳሉት ትህነግ ላቀረበው ጥያቄ እስካሁን መልስ አልተሰጠውም። ዛሬ አቶ ዛዲግ ይፋ እንዳደረጉት ከሆነ መንግስት ከሽብረተኛና አገር ለማፈራረስ ከተነሳ ድርጅት ጋር አይነጋገርም።

የኢትዮጵያ መከላከያ ከአማራና አፋር ልዩ ሃይል እንዲሁም ሚሊሻ ጋር በመሆን ማጥቃቱን እንደቀጠለ መንግስት ማስታወቁ ይታወሳል። ፊርልትስ ማን የትህነግ የአዲስ አበባ ጉዞ የከሸፈ መሆኑንን ማስታወቃቸውና ” ዛሬ 1983 አይደለም ብለን ነግረናቸዋል” ማለታቸው አይዘነጋም።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጦር ሜዳ መሄዳቸውን ተከትሎ በርካታ ሕዝብና ታዋቂ ዜጎች ወደ ግንባር መዝመታቸውና የጦሩ የመዋጋት አቅም እጅግ እንደተነገነባ የተለያዩ አስተያየት ሰጪዎች እያስታወቁ ነው።

Leave a Reply