የደብረ ብርሃን ከተማ ከንቲባ ታሰሩ፤ ጭፍራ ወደ ቤቷ ተመለሰች

በደብረብርሃን ላይ የበላይነት እንደሚይዙ፣ ይህም የሚሆነው በጥቂት ቀናት ውስጥ እንደሆነና ከተማዋን ” ትግራዋይት እናደርጋታለን” በሚል በማህበራዊ ሚዲያ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር የፕሮፕጋንዳ ሰዎች ሲናገሩ ነበር። በአስቸኳይ ከደሴ በተወሰደ ትምህርት እስካሁን ምንም የሆነ ነገር የለም። ዛሬ ኢሳት ይፋ እንዳደረገው የከተማዋ ከንቲባ አቶ ደስታ አንዳርጌ በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ተደርጓል።

ከንቲባው በቁጥጥር ሥር የዋሉት ከሕወሓት ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል ተጠርጥረው እንደሆነ ኢሳት “ነገሩኝ” ያላቸውን ምንጮች ጠቅሶ አስታውቋል። ከከንቱባው መታሰር ውጭ ምንም ዓይነት ችግር እንደሌለና በመስመሩ የወገን ጦር ወደፊት እያጸዳ እየሄደ መሆኑን በስፋራው የሚገኙ አስታውቀዋል።

Image

ከንቲባው በፌዴራል ኮማንድ ፖስት ትዕዛዝ፣በብሔራዊ እና መረጃ ደህንነት ግብረኃይል በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን፣ ከንቲባው አቶ ደስታ ትላንት ሕዳር 18 ሌሊት በቁጥጥር ሥር እስከዋሉበት ድረስ የደብረብርሃን ከንቲባ ሆነው እየሰሩ እንደነበር ታውቋል። በአገሪቱ የአስተዳደር መዋቅር መሰረት ከንቲባ ው የከተማዋ የጸጥታና የድህንነት ሃላፊ ነው።

የትህነግ ሰዎች ” ደብረብርሃንን ተግረዋይ እናደርጋለን” በሚል ሲፎክሩ የነበሩት በዚህ መሰል የውስጥ ለውስጥ ትሥሥር ተማምነው እንደሆነ በመግለጽ ዜናውን የሰሙ በማህበራዊ ገጻቸው መረጃውን እያሰራጩና “የተበላ ዕቁብ” እየአሉ ነው።

የደብረብርሃን ከተማ መታወቂያ የሌላቸው ከተማዋ ውስጥ መንቀሳቀስ እንዳይችሉ፣ ተፈናቅለው ከሌላ አካባቢ የመጡ በተለይም ከደሴ በተዘጋጀላቸው የመጠለያ ጣቢያ እንዲቆዩ መታዘዙ አይዘነጋም። ከዚህ ውሳኔ ጋር ተያያዞ የጫት ሱስ ያለባቸው ተፈናቃዮች ዘይትና ብርድልብስ እየሸጡ በድብቅ ኮንትሮባንድ ጫት ለመግዛት በሚል ችግር እየፈጠሩ እንደነበር የዝግጅት ክፍላችን ሰምቷል።

የእርዳትና ድጋፍ ችግር ሳይኖር ዓመል ያለባቸው የጸጥታውን አካሄድ እንዳያስተጓጉሉ ከትትል እየተደረግ መሆኑ ተሰምቷል። የከተማዋ ፖሊስ አዛዥም በህግ የሚፈለጉ ተጠርጣሪዎችን ከእስር በመፍታታቸው ከሃላፊነታቸው ተነስተው በታሰራቸው ይታወሳል።

Image
የአፋር ልዩ ሃይል አባላት በጭፍራ

በሌላ ዜና የአፋር ጀግኖች ከመለከላከያ ጋር በመሆን ጭፍራን እጃቸው ከተው ደስታቸውን ሲገልጹ የሚያሳይ ምስልና ቪዲዮ አሰራጭተዋል። ወልደያ እንደናፈቀቻቸውም እየተናገሩ ነው።

Leave a Reply