የፍጻሜው መጀመሪያ ሁሉም ግንባር ምን እየሆነ ነው? ነገሮች ወደ መጠናቀቅ?

ስለ ጭፍራ ስትራቴጂካዊነት በጥቂቱ! ሲል ስሙ ከስር የተጠቀሰው ጸሃፊ ያስረዳል። የመሳይ መኮንና የዚህ አስተያየት ሰጪ እየታ ትህነግ ለምን ጭፍራ ላይ ተሟሟተ ለሚለው ጥያቄ መስል ይሰጣል።

❶.ከወልድያ 76 ኪ.ሜትር(የ1:30 ሰአት) ርቀት ላይ የምትገኝ ስትሆን ወደ ሰሜን ማእከል ደሴና ኮምቦልቻ የወረደ ጁንታ ለሁለት ለመቁረጥ መሰረታዊ የሚሊቴሪ ኢንተርቬንሽን ቦታ ነች።

❷.ወደ ሚሌ የሚወስዱት ኮምቦልቻና ጭፍራ መሆናቸው የጭፍራ መያዝ ጁንታው ወደ ሚሌ የመጓዝ እጣፈንታው በአጭሩ የሚያስቀር ድል ነው። የመቆረጥ ስጋት የሚበረታበት ለጁንታው አስጨናቂ ሽንፈት ነው።

❸.ጭፍራ በአማራና አፋር ድንበር የምትገኝ እንደ መሆኗ በዚህ ድል መላው አፋር ነጻ ስትወጣ ለኢትዮጵያ መከላከያ ግስጋሴ ወሳኝ የሞራል ስንቅ ትጥቅ እንዲሁም ብቃት የሚጨምር ቀጣይ የድል ማሳያ ነው።

በማጠቃለያው ጭፍራ እጅግ የድል ፋና የሚፈነጥቅ ድል ነው። አንዳንዴ አቅሞች ሁሉ አንድ አይደሉም አንዳንዶቹም አቅም ፈጣሪ አቅሞች ናቸው የጭፍራና ካሳጊታ ድል ከድል በላይ ነው።

ድል ለኢትዮጵያ🇪🇹
Weraksa ወራቅሳ


ከስር የመሳይ መኮንን እየታ እንዳለ ቀርቧል

የጦር ሜዳ ውሎዎችን በተመለከተ የሚደርሱንን መረጃዎች በአስቸኳይ አዋጁ ምክንያት በዝርዝር ከማካፈል እንቆጠባለን። በአጭሩ ግን ጀግኖቹ ስራቸውን በስኬትና በፍጥነት እያከናወኑ ነው። ጋሸና፣ ጭፍራ፣ ደሴ-ኮምቦልቻ፣ ማይጠብሪ፣ የምንሰማው ነገር መጪውን ጊዜ የድል ዜናዎችን እየተበሰሩ የምናሳልፍበት ይሆናል። የጋሸና ዋናው የህወሀት ምሽግ ተሰብሯል። ጋሸናና ዙሪያው ስትራቴጂክ አከባቢ ነው። ህወሀት አርሚ ሁለት የተሰኘውን ትልቁን የሰራዊቱን ክፍል ያሰለፈበት ጋሸና ላይ መሆኑ ያለምክንያት አይደለም። ጋሸናን ካጣ መቆሚያው መቀሌ ይሆናል። እሱንም ማምለጥ ከቻለ። ጋሸና ለስድስት ወሳኝ አቅጣጫዎች ቁልፍ መገናኛ በመሆኗም እንደፍልፈል ጉድጓድ ሲቆፍር ከርሞ ግዙፍ ምሽጎችን ሲገነባ ነበር። ሰሞኑን በኢትዮጵያ ሰራዊት በተወሰደ ብርቱ የማጥቃት እርምጃ ምሽጎቹ፣ ዋናውን ጨምሮ ተሰብረው በወገን እጅ ተይዘዋል። የጋሸና ጉዳይ ያከተመ ይመስላል። የህወሀት ጀሌ ወደ መቀሌም መሸሽ እንዳይችል መሀል ላይ ተቆርጧል።

ክንዳቸው የሚፋጅ የምድር ድሮኖቹ በጭፍራ ባንዴራውን ተክለው አውለብልበዋል!!

በአፋር በኩል ጭፍራም ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ ሰራዊት ቁጥጥር ስር ሆኗል። ዙሪያውን ለሁለት ቀናት ከቦ የቆየው የወገን ሃይል በዛሬው ዕለት ጭፍራ ገብቶ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ሰቅሏል። ወታደራዊ ባለሙያዎች እንደነገሩኝ ጭፍራም እንደጋሸና ወሳኝ ቦታ ነው። የመቀሌን መስመር ለመቁረጥ የጭፍራ ነጻ መሆን ትልቅ ሚና ይኖረዋል። ሚሌን ቋምጦ የአፋር በርሃ ላይ እንደቅቤ የቀለጠው የህወሀት ጀሌ የተረፈው ወደ መቀሌ ለማምለጥ እንኳን እንዳይችል ሆኗል። በጭፍራ በኩል ያለው ግንባር በወገን የበላይነት ተያዘ ማለት የወልዲያን ነገር በቀናት ውስጥ እንዲለይለት ያደርገዋልም ተብሏል።

የደሴ-ኮምቦልቻም እጣ ፈንታ ከእነዚህ አከባቢዎች ጋር የተያያዘ ነው። እንደሰማሁትና ቀድሞም እንደነበረኝ መረጃ በደሴና ኮምቦልቻ የህወሀት ሀይል ብዙም የለም። አጠቃላይ የማጥቃት ውሳኔ በመንግስት በኩል እስኪሰጥ መጠበቁ ግድ ስለነበረ እንጂ የሚገዳደር የህወሀት ሃይል በሁለቱም ከተሞች እንደሌለ መረጃው አለኝ። ምናልባት ሰርገው የገቡና በነዋሪነት ዓመታትን የቆዩ የህወሀት ሰዎችን የማጥራቱ እርምጃ በራሱ ጊዜ ሊወስድ ይችላል።

ከዚያ ባለፈ ለሚሌው ግንባር አብዛኛውን ሃይል ወደባቲ በማንቀሳቀሱ ደሴና ኮምቦልቻ በአብዛኛው ከህወሀት ነጻ ናቸው። በሚቀጥሉት ቀናት የሁለቱ ከተሞች ጉዳይም መቋጪያ ያገኛል። በነገራችን ላይ ህወሀት እንደምንም የሞት ሞቱን በሱዳን በኩል መተማ አከባቢ ጥቃት ከፍቶ እንዳይሆን ሆኖ ተመትቷል። የህወሀት መደምሰስ ያሳመማት ሱዳን ኢትዮጵያ አጠቃችኝ ስትል አለቃቅሳለች። አፍንጫ ሲመታ ዓይን ያለቅሳል ሆኖባት ነው።

በነገራችን ላይ የጋሸናውም መስመር ለወልዲያ ጨምሮ እስከ አላማጣ-ኮረም ድረስ ለኢትዮጵያ ሰራዊት አልጋ በአልጋ እንደሚሆንለትም ነው ያነጋገርኳቸው ወታደራዊ ባለሙያዎች ያጫወቱኝ።

ሰሜን ሸዋ ያለው ወቅታዊ ሁኔታም ስጋት ላይ የሚጥል አይደለም። በትንሽ ሃይል ሾልኮ በመግባት ከአንዳንድ የሸኔ ታጣቂዎች ጋር የተገናኘው የህወሀት ጀሌ ግስጋሴው ተገትቶ ግራ በተጋባ ሁኔታ በየጥሻውና ዋሻው ሲሯሯጥ ይታያል። መንዝ አከባቢ ሰሞኑን ሊፈራገጥ ሞክሮ ወገቡ ሲቀነጠስ ጊዜ እግሬ አውጪኝ መፈርጠጡ ተሰምቷል። በሞላሌ አንገቱን ቀና ከማድረጉ የድሮን ሲሳይ መሆኑም ታውቋል። ይሁንና አሁንም በጥቂት ቁጥር አንዳንድ ቦታዎች መታየታቸው አልቀረም። ተበጣጥሰው የተበተኑ በመሆናቸው የመልቀሙ ስራ ትዕግስትንና ጥንቃቄን ይጠይቃል። በሰሜን ሸዋ የተጀመረው የማጥቃት እርምጃ በቅርቡ የዚያን አከባቢ ሁኔታ የሚቀይረው እንደሚሆን ይታመናል።

በአጠቃላይ ያለው የየግንባሩ ወቅታዊ ሁኔታ ለጠላት ሃይል የጨለማው ዘመን ከደጃፉ መድረሱን ያመላክታል። በአንጻሩ ለኢትዮጵያውያን የእፎይታ ጊዜ እየመጣ እንደሆነ ማረጋገጫ ይሰጣል። አሁንም እንጠይቃለን። ሌ/ጄ ጻድቃንን የበላ ጅብ ምነው አልጮህ አለ? በደህና ይሆን የጠፉት?

እንበርታ!

Mesay Mekonnen

Image
“በአፋር የሆነው ይህ ነው” ሲሉ የክልሉ መገናኛ ሰራተኞች ያሰራጩት ምስል ነው

Leave a Reply