«ሠራዊቱ ጠላትን በአጭር ጊዜ ደምስሶ ለወገኑ የድል ብሥራት ለማቅረብ በከፍተኛ ወኔ እየገሰገሰ ነው»

የጠላት መግቢያና መውጫ ከወገን ጦር ዕይታ ስለማይወጣ በገባበት እንደሚቀር በወሎ ግንባር ወታደራዊ አዛዥ ገለጹ።

የጠላት መግቢያና መውጫ ከወገን ጦር ዕይታ ስለማይወጣ ጠላት በገባበት እንደሚቀር በወሎ ግንባር አንድ ወታደራዊ አዛዥ ገልጸዋል። በተለያዩ ግንባሮች ከፍተኛ ምት እየገጠመው ያለው ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ኃይል ሙትና ቁስለኛ እየሆነ ነው። በኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ያልተቋረጠ ድብደባ እየተደረገበት የሚገኘው ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ኃይል እየተሽመደመደ ነው። በገባበት ሁሉ እየተደመሰሰ እንዲቀር ግድ ሆኖበታል።

በወሎ ግንባር የገባው የወገን ጦርም የሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ኃይልን አንገት እያስደፋ ሙት እያደረገው ነው።

ከአሚኮ ጋር ቆይታ ያደረጉት የአማራ ልዩ ኃይል አባላትም ጠላት ተሰቅዞ ተይዞ እየተገረፈ መሆኑን ተናግረዋል። አባላቱ ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ኃይልን ድባቅ እየመቱትና እየተደናበረ መሆኑንም ገልፀዋል። የወገን ጦር ከአሁን በፊትም በተለያዩ ግንባሮች የጠላትን አንገት እያስደፋ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡ እኛ እያለን ሕዝባችን እንዲበተን፣ እንዲገደል አንፈልግም፣ ደጀኑ ሕዝባችንን ይዘን ጠላትን እንደመስሰዋለንም ብለዋል።

ጠላት ከፍተኛ ኪሳራ እየደረሰበት፣ እየተሽመደመደ ወደኋላ እየፈረጠጠ እንደሚገኝም ተናግረዋል። ሕዝቡና መሪዎች ከላይ እስከ ታች በአንድነት የተነሱበት ነው ያሉት አባላቱ ይህን ይዘን ጠላትን ያለ ጥርጥር በአጭር ቀናት እንደመስሰዋለን ብለዋል። ሠራዊቱ ጠላትን በአጭር ጊዜ ደምስሶ ለወገኑ የድል ብሥራት ለማቅረብ በከፍተኛ ወኔ እየገሰገሰ መሆኑንም አስታውቀዋል።

ሠራዊቱ የጠላትን መሳሪያዎች በመማረክና በመደምሰስ ግዳጁን በአስደናቂ ብቃት እየተወጣ እንደሚገኝም ተናግረዋል። በዚህ ሰሞን አስደናቂ ግዳጅ እየተወጡ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

በግንባሩ የሻለቃ አዛዥ በግንባሩ የገባው የወገን ጦር ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ኃይልን ድባቅ እየመታው እንደሚገኝም አስታውቀዋል። በግንባሩ ታምር የሆነ ውጊያና ድል እየተገኘ መሆኑንም ገልፀዋል። ጠላትን እያሳደድን በገባበት ሁሉ እንለቅመዋለን ብለዋል።

የጠላት መውጫና መግቢያዎች በወገን ጦር ዕይታ የማይወጡ በመሆናቸው በገባበት እንደሚቀርም ተናግረዋል። ሠራዊቱ የገባ ጠላት መውጣት የለበትም በሚል እሳቤ ጠላትን እየመታ እንደሆነ ነው የገለጹት። ያለ ምንም ጥርጥር በቅርቡ ታላላቅ ድሎች ለሕዝባችን እናደርሳለንም ነው ያሉት። ልዩ ኃይሉ በተሟላ አቋም ላይ እንደሚገኝና በቀጣይም አስደናቂ ተግባርም ለመፈፀም እየተፋለሙ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ

ሕዳር 17/2014 ዓ.ም (አሚኮ)

Leave a Reply