በቀጣዮቹ ሶስት አመታት በቢሊዮን ዶላሮች ወጪ በርካታ ፕሮጀክቶች እንደሚተገብሩ ተገለጸ

በቀጣዮቹ ሶስት አመታት በቢሊዮን ዶላሮች ወጪ በርካታ ፕሮጀክቶች በአፍሪካ እንደሚተገብሩ ተገለጸ
👉 ኢትዮጵያ በ8ኛው የቻይና አፍሪካ ትብብር የሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ እየተሳተፈች ነው


በአፍሪካ በቀጣዮቹ ሶስት አመታት በቢሊዮን ዶላሮች ወጪ በርካታ ፕሮጀክቶች እንደሚተገብሩ በሴኔጋል ዳካር እየተካሄደ
ባለው 8ተኛው የቻይና-አፍሪካ ትብብር የሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺን ጂንፒንግ ተናገሩ።

ኢትዮጵያ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፖለቲካና ኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የተመራ ልዑክ በሴኔጋል ዳካር ከተማ እየተካሄደ ባለው 8ተኛው የቻይና አፍሪካ ትብብር የሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ እየተሳተፈች ነው።

የቻይና-አፍሪካ ትብብር 8ተኛው የሚኒስትሮች ጉባኤ በሴኔጋል ዳካር እየተካሄደ ነው፡፡

በጉባኤው ላይ በአፍሪካ በቀጣዮቹ ሶስት አመታት ቢሊዮን ዶላሮች በጤና፣ በድህነት ቅነሳ፣ በንግድ፣ በኢንቨስትመንት ማስተዋወቅ ፣ በዲጂታል ኢንቨስትመንት፣ በአየር ንብረት ለውጥና በአቅም ግንባታ ፕሮግራሞች፣ በባህልና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት፣ በሰላምና በጸጥታ ላይ ትኩረት ያደረጉ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ እንደሚደረግ የቻይናው ፕሬዝዳንት ተናግረዋል።

“የቻይና አፍሪካን አጋርነት በማጠናከር ቀጣይነት ያለው ልማትን በማበረታታት የቻይና-አፍሪካ ማህበረሰብ በአዲሱ ዘመን የጋራ ተጠቃሚነት” በሚል መሪ ቃል ጉባኤ እየተካሄደ ነው።

በዝግጅቱ ላይ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ፕሬዝዳንቶች፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ እና የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን መገኘታቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል።

Leave a Reply