“ሰውየው በዶጎሎ ማማ …”

ክፋት፣ምቀኝነትና ነቀፌታ እንዲሁም ቧልትና አሉባልታ የማይለየው የኢትዮጵያ ፖለቲካ በዚህ ባህሪው የተነሳ አስሊዎች እንዳሻቸው ያላጉታል። ሃብታሙ አያሌው የሚባለው ” ተንታኝ” ኮምበልቻና ደሴ ነጻ መውጣታቸውን፣ ነጻ የወጡትም በአማራ ሃይል መሆኑን፣ ዜና ያልተነገረው ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስቀድመው መረጃ መስጠት ስላለባቸው … በሚል መቀመጫውን ለሸነቆሩለት ይሟገታል። በቤቱ እሱም አዋቂ ሆኖ ልዩነትም ለመፍጠር ነው።የ “ጨዋ” ነገር። እጣቢ አዕምሮ ያለው “ጨዋ” ነውና አዋጥተው ሽንቁሩን የደፈኑለትንና ሚስቱን ጨምሮ ቤተሰቡን የታደጉለትን ወገኖቹና ዜጎች ላይ መርዝ ይረጫል። ሚስቱም አትመክረውም። ለሚስቱ ወደፊት እጽፋለሁ። እሱ ግን ገና ብዙ ይላል … ሰውየው ግን በዶጎሎ ማማ ላይ ናቸው። ስራ ላይ!!

የአብን አመራሮች ከአዴፓ ጋር በተናነቁበት ወቅት 360 ልዩነቱን አማራን ለማፍረስ ለተቀጠረበት ዓላማ እያሞካሸ ይጠቀምበት እንዳልነበር፣ ዛሬ በዋሳኙ ሰዓት የአብን አመራሮች ” ቅድሚያ ኢትዮጵያ እናት አገር” ሲሉና ወደ ጦር ሜዳ ዘምተው ዋጋ ሲከፍሉ፣ የእነ ክስርስቲያን፣ ዩሱፍና ጋሻው … ሌሎች የበላይና የበታች መዋቅር ከነደጋፊያቸው የትህነግ ወራሪ ሃይል ላይ የጉሮሮ አጥንት ሲሆኑበት፣ ጌታቸው ረዳ ” ውርጋጦች” እንዳለው ” ተከተል አለቃህን” ነውና ሃብታሙ አያሌው ዛሬ ” አብንና አዴፓ አንድ ናቸው” ብሎ ደምድሟል። “ዶሮ ብታልም ጥሬዋን” እንዲሉ ለተቀጠረለት አላማና ለዚህ ከታችም ከላይም የተሸንቆረ ስብዕናው በሚመጥነው መልኩ ደረጃ መዳቢ ሆኗል። ” ድንቄም” እንዳለችው ባልቴት፤ ይህን ሽንቁር “ድንቄም መዳቢ” ብሎ ከማለፍ ሌላ ምን ይባላል? የሚያስደስተው ሰውየው ስራ ላይ መሆኑ ነው።

“ሚስቱን የት አገኛት? ልጆች አሉት? በዕርግጥ የሱ ናቸው? ለመሆኑ የት ተማረ? ግን ተምሯል?” በሚል በአንደረቢ የዓመድ ስር መንፈስ የሚቀባጥር፣ የሙት መንፈስ ጠባቂና ገረድ የነበረ ዛሬም ሰውየውን ይተቻል? ዛሬም ከጎለደፈ ጭንቅላቱ የሚሰነፍጥ የመናፍስት ዓለም ቅዠት ያፈሳል። ተከትለውት የሱን ፍሳሽ የሚያራቡ ቢንጫጩም ሰውየው ስራ ላይ ነው። ሰውየው ሶስተኛውን ቁልፍ ሊከፍት እየተጋ ነው።

ወሬና ቧልቱን፣ የአመለካከት ልዩነትን፣ ፖለቲካዊ ግብን ወደሁዋላ ትተው ” በአይኔ ያየሁትን እመስከራለሁ ” ያሉ የአብን ልጆች ዋናው ሜዳ ላይ ሆነው ቆሎ እየቆረጠሙ፣ ድንጋይ ተንተርሰው አገር እያቀኑ ነው። ከሃሜትና ከቧልት፣ ከአሽከርነትና ከተራ የቅናት በሽታ ተላቀው በልዩነታቸው ውስጥ ያለችውን አገራቸውን እያታደጉ በመሆናቸው እየተሰደቡ ነው። ይህንኑ የጋለሞታዎች ስድብ የሚያስቆመው ነገር የለምና ሰውየው ከሚመስሉት አገር ወዳዶች ጋር ደጎሎ ነው።

See also  ጋይንት ከአሸባሪው ቡድን ነጻ ሆነ!

ምዕራፍ አንድ አፋር፣ ሁለተኛው ዳሸና ሶስተኛው ደጎሎ። ሰውየው – የኢትዮጵያ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ በሶስተኛው ምዕራፍ ዶጎሎ ሆነው የቦታውን ሚስጢራዊነት ሲያስታውቁ፣ የቦታው መያዝ ከኮምቦልቻ፣ ባቲ፣ ሃይቅና ደሴ እንዲሁም ከሸዋ እየተጠረገ ያለው ሃይል ትጥቅ፣ ንብረትና ራሱ ጭምር እንዳይወጣ የሚአደርግ ነው። ” ጠላት ፈርሷል። ተበትኗል። ቀሪው ስራ መልቀም ነው። በሁለትና ሶስት ቀናት ውስጥ መስመሩ ነጻ የወጣል” ሲሉ ስም ጠርተው መናገራቸው ” እንደርቢና ዛር” የሰፈረባቸውን ሁሉ አንጫጭቷል። ግን የሚሰማ የለም። ሕዝብ በግንባር ላሉት ልጆቹ ስንቅ ብቻ ሳይሆን፣ ከዛ ያለፈ ድጋፍ እያደረገ ነው።

” ቀና በል” የሚለውን የደም ስር የሚያግል ዜማ በተዜመ ማግስት ” ዘምቻለሁ” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በማያውቋቸው ሳይቀር እየተወደሱ ባለበት በዚህ ወቅት፣ እነዚህ የበረከት ሽንቶች፣ የዛር ተማሪዎች፣ የቅጥፈት መንፈስ ልጆች ስለምና ምን እንዲሆን አስበው መርዝ እንደሚተፉ ፍጹም ግልጽ አይደለም።

የሚሆን መስሎት በድጎማና በራሱ በጀት ሲገልላወድ የነበረው የመረጃ ቲሌቪዥን ጉዳይ ወደፊት በዝርዝር የሚነገርለት ብዙ ጉድ ቢኖረውም ለጊዜው ዳፍቆ፣ ዳፍቆ፣ መዙን ረጭቶና አስረጭቶ በበቃኝ መዘረሩ አንድ ግልግል ሲሆን የሌሎችም ሞት የሚጠበቅ ነው። ትህነግ ገመዱ እየጠበበት ሲሄድ፣ ይህ መንግስት ለመሆን እየቋመጠ በሄደበት ሊጥ የሚጠጣ፣ አሻሮ ሳይቀር የሚዘርፍ፣ ንብረትና አገር የሚያወድም፣ ሃፍረቱና እፍረቱን መዘርዘር የማይቻለውን የወንበዴ ቡድን ተማምነው የነበሩ ገና ይራገፋሉ።

ትህነግ “አሸንፋለሁ” ሲል ለሌላ አዲስ ማጥቃት ለመዘጋጀት ስልታዊ ማፈግፈግ እንዳደረገ ለደጋፊዎቹ ሲያስታውቅ፣ ያለምንም ሃፍረት “በድል ዋዜማ ላይ ነኝ” ነው ያለው። ብዙ በትግርኛ፣ ጥቂት በአማርኛ የተጻፈው መግለጫ እንዳለ ሆኖ አልጀዚራ ገለጥኩት ሲል የዝገበው ግን የተለየ ነው። የተባበሩት መንግስታትን ጨምሮ ለወዳጅ አገሮቹ ” መከላከያ መቀለ እንዳይገባ ድረሱልኝ” ነው ያለው። መሳሪያ አትሽጡ ሲልም የኢትዮጵያን ወዳጆች ተማጽኗል። ጦርነት ገብቶ ለቅሶ። “እጃችሁን ስጡ። አለበለዚያ ተቀነደባለህ” ሲል እንዳልነበረ ዛሬ እዬዬ … ለመሆን የሚሞቱት ምስኪኖች ህይወት … ቤቱ ይፍረደው።

ሼትል ትሮድ ቮል ስትራቴጂካል አማካሪና የትህነግ ነጭ አመራር የሚባሉ የኖርዌይ ዜግነት ያላቸው ፕሮፌሰር ናቸው። ዛሬ ” የትግራይ ሃይሎች ስልታዊ ማፈግፈግ ያደረጉት አዲስ የተገዙትን የድሮን ጥቃቶች መቋቋም ባለመቻላቸው ነው” ሲሉ በቲውተር ገጻቸው ጽፈዋል።

See also  አፋር ክልል ንጽሃን እየተጨፈጨፉ ነው ሲል አስጠነቀቀ

ሌሎች ደግሞ በተባበሩት መንግስታትና በኢትዮጵያ የስባዊ መብት ኮሚሽን በጋር ተመርመሮ የጄኖሳይድ ድርጊት አለመፈጸሙ ከተረጋገጠና በትግራይ በኩል ይህ ክስ ተቀባይነት እንደማያገኝ ፋይሉ ከተዘጋ በሁዋላ አዲስ ዶክመንታሪ ተከዜ ወንዝ ላይ ተጥሎ በተገነ አስከሬን ሲኤን ኤን አዘጋጅቷል። ሱዳናዊቷ ዘጋቢ ነች የመራቸው። ይህ ወዴት ሊያመራ ይችላል? በዚህ መልኩ ትህነግን ለማዳን ላይ ታች እየተባለ ነው።

“ልትነድ ነው” የተባለችው አዲስ አበባ አማን ናት። ተሸነፉ የተባሉ ኢትዮጵያዊያን ቀና ብለው እንደዋላ በድል ላይ ድል እያስመዘገቡ እየከነፉ ነው። ባዶ የነበረው ቤታችን በክተት ተሞልቶ። ሰውየው ዶጎሎ ሆኖ የድሉን ወጋገን አብስሯል። ቧልተኞችም በዝግ ቤት ሆነው የታዘዙትን ያወራሉ። ትውልድና ታሪክ ሁሉንም ይከትባሉ።

ድል ለኢትዮጵያ!!

ሰበለ ወንጌል ቃለኪዳን

Leave a Reply