የከረዩ አባ ገዳ በአሸባሪው ሸኔ ተገደሉ፤ ግድያው ከረዩ በስለፍ በመቃወሙ ነው

በኦሮሚያ በርካታ ንጹሃንን እየገደለና እያፈናቀለ ያለው ኦነግ ሸኔ እጅግ የተከበሩና የሚወደዱ እንደሆነ የሚነገርላቸውን የከረዩ አባገዳ ከድር ሁዋስ ቦሩን መግደሉን የኦሮሚያ ክልል አስታወቀ።ክልሉ ባይገልጽም በርካታ የከረዩ ሽማግሌዎች ተገድለዋል። ከአካባቢው እንደሚሰማው ከረዩዎችና አባገዳውን የሚያውቁ ኦሮሞዎች ተቆጥተዋል።

“የየከረዩ ህዝብ በሸኔ ላይ ያደረገውን የተቃውሞና ለመንግስት የሰጠውን የድጋፍ ስልፍን ተከትሎ ተስፋ የቆረጠው አሸባሪው ሸኔ ህዝቡ በእኛ ላይ እንዲነሳና ሰልፉን እንዲያካሂ ቀስቅሰዋል” በሚል አባ ገዳ ከድርን እንደገደላቸው የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ አመልክቷል።

“ከዚህ በፊትም ሽብር ቡድኑ አሰቃቂ ግድያዎችን መፈጸሙ ይታወሳል ያለው” ቢሮው ሸኔ ከገደላቸው መአካከል የተከበሩ የአገር ሽማግሌ የሆኑት ሀጂ ኡመር ዋጩሌ አንዱ ናቸው፡፡ ሸኔ በየጊዜው በሰላማዊ ዜጎች ላይ የሚፈጽመው ግድያ አሸባሪው ቡድኑ ህዝባዊ ዓላማ እንደሌለው ማረጋገጫ መሆኑን ቢሮው አክሎ ገልጿል። ክልሉ የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ገልጿል።

ሸኔ በርካታ የኦሮሞ ልጆችን ቤታቸው ድረስ እየሄደ የሚገድል፣ ልጆችን ያለወላጅ የሚያስቀር ይህንንም የሚያደርገው አለቃውን ትህነግን ለማስደሰትና በሚከፈለው መጠን ግብረ ምላሽ ለመስጠት እንደሆነ በተደጋጋሚ እየተነገረ ነው።

የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ዝርዝሩን ባያሳውቅም ባገኘነው መረጃ ከአስር በላይ የከረዩ ሽማግሌዎች በሸኔ ተገድለዋል። ይህን ተከትሎም የከረዩ ተወላጆች ሸኔን ሊበቀሉ እንደሚችሉ ተሰምቷል።

“ሸኔ የፖለቲካ ድርጅት አይደለም። ገንዘብ እየተከፈለው የሚሰራ ቅጥረ ነብሰ ገዳይ ነው” የሚሉ ወገኖች ” ሸኔ እየተከፈለው ነብስ የሚያጠፋ ቅጥረ ነብሰ ገዳይ ድርጅት ባይሆን ኖሮ ቀድሞ ትህነግ ኦሮሞን ሲያጠቃ፣ ሲያሰቃይና ሲጨፈጭፍ ክንዱን ባሳየ ነበር። ይህ የሚያሳየው ሸኔ ቀድሞውንም ትህነግ ያዘጋጀው ተከፋይ ቅጥረ ነበስ ገዳይ መሆኑንን ነው። አሁንም ትሀንግን ተሸክሞ ለማንገስ ኦሮሞና ሌሎች ወገኖች እየጨፈጨፈ ነው” ሲሉ አምርረው በገጻቸው እየጻፉ ነው።

Leave a Reply