ሽፍታው ወራሪ ኮምቦልቻን አጠባት፤ ከነጻ መውጣት ብሁዋላ ምን?

” ኢትዮጵያ አትደፈርም ያልነው እናንተን ተማምነን ነው። ይህ ባንዲራችን በሌቦችና በሽፍቶች አይደፍረም። በህይወት እስካላችሁ ይህን ባንዲራ ጠብቁ” አሉ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ አብይ አህመድ። ሰራዊቱ መካከል ኮምቦልቻ ከተማ ከድል በሁዋላ። ” ዓላማችን መስረቅ፣ መድፈር፣ ሳይሆን ኢትዮጵያን ማዳን ነው” ሲሉ ለሚመሩትን ሰራዊት ክብር ሰጡ።

“ለምነን፣ ተው ብለን፣ ያልፈለገነው ጦርነት ውስጥ ገባን” አሉ። አከሉና የጠላት ሃይል የሚደርስበትን በትር መቋቋም አቅቶት እንደ ዩኒት ሃይሉን ሰብስቦ እንዳይወጣ ተደርጎ ኪሳራ እንደደረሰበት አመለከቱ። የዘርፈውን ይዞ እንዳይወጣ ተደርጎ የተመታው ወራሪ ተበታትኖ በየስርቻው ከገባው ውጪ መቀጥቀጡን ” እንዳያችሁት” ሲሉ ለቀይ ለባሾቹ በማስረዳት ገለጹ። ይህን ብለው ” ዓላማችን ልማት ነበር” በማለት “በጥባጭ ካለ ማን ንጹህ ይጠጣል” የሚለውን ብሂል የሚያስታውስ ቃል ሰነዘሩ። ግን ባስቸኳይ ወደ ተከጀመረው የልማትና ዕድገት ጉዞ እንደሚዞር አመለከቱ።

ሰውየው ” እንኳን ደስ አለን፣ ድል ምንግዜም የኢትዮጵያ ነው” ሲሉ ብቲውተር ገጻቸው መልዕክት እንዳስቀመጡ በቅጽበት የወረዳላቸው ምስጋና፣ ማነቃቂያ፣ ምርቃትና “መሪዬ” በሚል የተሰጣቸው ክብር ውስጥ ለዓይነት እንኳን የተለመዱ ተሹለክላኪ የስድብ ዛላዎችና የፈጠራ ምስሎች አይታዩም።

በክልላቸው “ክተት” ብለው የትህነግን ግስጋሴ ያሳነቁ በሚል ምስጋና የሚቸራቸው ክቡር አቶ አገኘሁ ተሻገርም ” መሪያችን ወደ ፊት እየገሰገሰ ነው። የተመዘገበው ድል ትልቅ ውጤት የተገኘበትና በጠላት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ የደረሰበት ነው!! ኢትዮጵያዉያንና ትዉልደ ኢትዮጵያውያን ልትኮሩ ይገባችኋል!! አንድነተታችን አጠናክረን እናሸንፋለን!!” የሚል መለከት ነፍተዋል። ለመሪያቸውም ክብርን ሰጥተዋል።

አቻም የለህ ታምሩ ዜናውን በትግርኛ “ሰበር ዜና ሓዱሽ ዓወት ብሳልሳይ ግንባር!” ታልቅ ሰበር ዜና ሲል አትሞታል። “ናይ ወገን ጦር ነዚ ወራሪ ናይ ፋሽስቲ ወያነ ወራር … ሰራዊት እናደምሰሰ ንቕድሚት እናመረሸ ይርከብ!” ብሎ የተለቀቁትን ቦታ በመዘርዘር ዜናውን ሲጨርስ “ዘልኣለማዊ ክብሪ ብዱር ብገደል ን ፋሽስት ወያነ ናይ ወራሪ … ሰራዊት ክተሳዱ ዝወደቕኩም ደቂ ሃገረይ! ኢትዮጵያ ትስዕር ኣላ!” ሲል ድሉን ትግርኛ ተናጋሪዎችም እንዲሰሙት አብስሯል።

በዛሬ እለት በባቲ ለአፋር ጀግኖች የትደረገው አቀባበል

“ደሴ ያለ ባህሪዋ ክህደት ተፈጽሞባታል፤ መልካምነቷንና ደግነቷን ላልተገባ ፍላጎታቸው በማዋል …” ሲሉ የአብን ከፍተኛ አመራር አቶ የሱፍ ኢብራሂም ” ደሴን የማንይበትን ቀን በጣታቸን እየቆጠርን ነው። ምህላ ይደረጋል። አጥፊዎች ተመጣጣኝ ቅጣት ይገባቸዋል” ማለታቸውና ይህ አቋም የሁሉም እንደሆነ መናገራቸው ይታወሳል። ደሴን ጨምሮ በርካታ ከተሞች ወደ እናታቸውና ልምዳቸው መመለሳቸውን ተከትሎ “ከዚያስ” የሚል የስጋትና የፍትህ ጥያቄ እየተሰማ ነው።

“ደሴ፣ ኮምቦልቻ እና ባቲ ከተሞች በጀግኖቹ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት ነጻ ወጥተዋል” ሲል የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ቢገልጽም ስለከተሞቹ ክራሞት በዝርዝር ያለው ነገር ባለመኖሩ፣ ሰሞኑንን ሰሜን ሸዋ ነጻ ሲወጣ እንደታየውና ከዛም በፊት ጋሸናን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች እንደሆነው ዓይነት ሆኖ ይሁን የሚል ስጋት አለ። የከተሞቹ ነጻ መውጣት የፈጠረው የደስታና የአሸናፊነት ስሜት እንዳለ ሆኖ እጅግ ከፍተኛ ቢሆንም ” ደሴ ምን ተሰርቶ ይሆን፣ ኮምቦልቻስ? ቆቦ ላይስ…?” ጥያቄ አለ።

“አሁን ባለው የአገር መከላከያና ጥምር ሃይሉ ጥንካሬ ጦርነቱ በፍጥነት በማስኬድ ከተሞቹን ማስለቀቅና በቀናት ነጻ ማድረግ የሚቻል ቢሆንም፣ በእርጋታ ከበባ በመፈጸም “ወራሪውን ሃይል መውጫ አሳጥቶ ማመናመን” የሚል ስልት እየተጠቀሙ ስለሆነ ጦርነቱ እንደ ማመንዠግ ነው” ሲሉ ቅርብ የሆኑ እየተናገሩ ነው። ዶክተር ደብረጽዮንም ለተከታዮቻቸው ” ተከበናል፣ ከበባውን መስበር አልቻልንም” ሲሉ አደጋውን ይፋ ሲያደርጉ ተደምጠዋል። ሽፋኑንን ” ስልታዊ ማፈግፈግ” በሚል የጠሩትን አልሸነፍ ባይነት ጎን ለጎን ” ከበባውን መስበር አልቻልንም” በሚል ዘግተውታል። “አዲስ አበባ ልንገባ ነው። እጃችሁን ስጡ ወይም ተደመሰሳላችሁ” እያሉ ሲያስጨፍሩት የከረመው ደጋፊዎቻቸው፣ በአደባባይ እየተንከባለሉ የውጩን ዲፕሎማሲ ሲሰሩና ሲያስተባብሩ ለነበሩ፣ “የኢትዮጵያ መከላከያ ንትቧል” በሚል በህብለት ሲፎክሩ የነበሩ ይህን ምክንያታቸውን ምን ያህል እንደተቀበሉት በግልጽ አልተገለጸም። ሆኖም ግን ” የመሰበር ስሜት እንዳለባቸው ሊደበቅ አይችልም” ሲሉ ገልጸዋል።

ታሪካዊቷ የደሴ ከተማ፣ የንግድና የኢንዱስትሪ ኮሪደር የሆነችው ኮምቦልቻ በጀግኖቹ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት ነጻ መውጣታቸው ከተሰማ ብሁዋላ የደሴውን መረጃ ማግነት ባይቻልም፣ ኮምቦልቻ ኢንደስትሪዎቿ እንዳታች መረጃ እየወጣ ነው። የነጮች ንብረት የሆነው ቢጂ አይ ሲቀር ሌላው መዘረፉ ተሰምቷል። በኮምቦልቻ የጅምላ ገድያ መፈጸሙ የተሰማው ገና ወደ ከተማዋ እንደገቡ ነበር። በክህደት ከእምብርታቸው በበሉና በጠጡ ተክደው ጠላት እጅ እንደወደቁ የተነገረላቸው ደሴና ኮምቦልቻ ዝርዝር ዜናቸው ውሎ አድሮ ይሰማል።

ከድሉ ዜና ጋር በተያያዘ ሰፊ ቁጥር ያለው ሃይል መማረኩ፣ በርካታ የጦር መሳሪያ እየተለቀመ መሆኑና አዲስ አበባ ለመግባት ቀናት እንደቀረው የተነገረለት የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ በሚፍልገው ፍጥነት መቀለ መመልስ አለመቻሉ ያሳሰባቸው ” መንግስት የራሱን ሕዝብ በረሃብ እየፈጀ ነው” ሲሉ ድጋፍ እየተማጸኑለት ነው።

በኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተመራው የኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት፣ ከደሴና ኮምቦልቻ በተጨማሪ በምሥራቅ ግንባር ሃይቅ፣ ባቲን፣ ቀርሳን፣ ገርባን እና ደጋንን ነጻ ያወጣ ሲሆን በሐርቡ ግንባር ደግሞ ቃሉ ወረዳን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠሩ ታውቋል። አሁን ቀሪው በቆቦ ወደ ወልደያ እንደሆነም ተሰምቷል።

Leave a Reply