ዘመቻ ምዕራፍ ሁለት ሊጀመር ነው፤ ትህነግ ተቆርጦ የተሰፋ ቪዲዮ አሰራጨ፤ ” ደጋፊዎቹን ለማጽናናት ነው” ተብሏል

ዘመቻ ሁለት ላይ ዝግጅቱ እየተተናእቀቀ ባለበትና የጦር ሃይሎች ዋና አዛዥ አብይ አሕመድ ቢሯቸውን ጥለው ግንባር በወረዱ በሁለት ሳምንት ጊዜ ወስጥ የታቀደውን ድል አሳክተው ወደ ቢሮ መመለሳቸውን ይፋ ሲያደርጉ፣ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ተቆራርጦ የተገጠመ ፊልም አምርቶ ይፋ ማድረጉ ታወቀ።

“የመጀመሪያውን ምዕራፍ ዘመቻ አጠናቅቄ ወደ ቢሮ መመለሴን አስታውቃለሁ” በማለት ልክ ቢሯቸውን ሲለቁ እንዳስታወቁት ለሕዝብ ለጊዜው ወደ ቢሮ መመለሳቸውን ያስታወቁት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ፣ ሁለተኛው ምዕራፍ ወይም ቀጣዩ ምዕራፍ እንዳለ ፍንጭ ቢሰጡም ዛሬም አላብራሩትም። በአፋር በኩል ድል እንደተበሰረ ለህዝብ ሲያስታውቁ ” ሁለተኛውን ዘመቻ ለጊዜው አንገልጽም” ማለታቸው ይታወሳል።

የጦር ሃይሎች ዋና አዛዥ አብይ አሕመድ ” ጦር ሜዳ የሉም” የሚሉ የኢትዮጵያን መከላከያ ሰራዊት የለበሱ ሲናገሩ ሲያሳይ የከረመው ትህነግ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋሸና፣ ኮምቦልቻና ከሚሴ ሆነው በግልጽ ማብራሪያ ሲሰጡ ታይቶም ይህንን ላስተባበለም። “ጠቅላይ ሚኒስትሩ የት ናቸው? በየትኛው ግንባር እንደተሰለፉ ያያቹህ” ሲሉ ማስታወቂያ በማሰራጨት የማነቃቂያ ክፍያ እንደሚከፍሉ ሲነገሩ የነበሩ የትህነግ ሚዲያዎች፣ እነ ማርቲን ፕላውት አብይ ጭፍራን በሁለት ቀን እንደሚቀሙ እዛው ጦር ሜዳ ተገኝተው ሲናገሩ ካዩ በሁዋላም አላስተባበሉም።

የአልጃዚራ እንግሊዘኛ ዘገባ በጭፍራ ያለውን ሪፖርተሩን ጠቅሰው እንደዘገበው ” ርህራሄ የሚባል ነገር ያከተመ ይመስላል። መንገዱ ሁሉ አስከሬን በአስከሬን ነው “It [Chifra] has been the epicentre of military operations during the past 40 days, Tewekel said during a live broadcast, with gunfire ringing in the background. The scenes we witnessed are very appalling. Dead bodies everywhere on the streets” ብሎ ነው የዘገበው። ተወከል ” በሌላ የአረብኛ ዘገባው ትህነግ ሕዝቡን በምን ምክንያት እንደሚያስጨርስ አይገባም” ማለቱም ይታወሳል።

የትህነግ ወራሪ ሃይል ነፍጥ ተሸካሚዎች እጅ ከሰጡ በሁዋላ ” መትረፋችን ተዓምር ነው። መትረፋችን እድለኞች ነን” ሲሉ በተደጋጋሚ እንደተሰማው ትህነግ ከፍተኛ ሰብአዊ ቀውስ እንደደረሰበት ማሳያ ሆኖ ሳለ፣ ራሱ ትህነግ በመሪው ዶክተር ደብረጽዮን አማካይነት ” ከበባውን መስበር አቃተን” ማለታቸው እያታወቀ አብይ አሕመድ ” ስንት ተሰዉ?” ብለው ሲጠይቁ፣ አንድ አዛዥ የጦር መኮንን ” አስር ሺህ” ሲሉ የሚያሰማ ከኢቲቪ የተሰረቀ ክሊፕ ጌታቸው ረዳ አሰራጭተዋል።

See also  መከላከያ አላጠቃሁም አለ፤ ከተጀመረ ግን "ተጠቃሁ" ለማለት ጊዜ የሚሰጥ እንደማይሆን አመልከተ

አቶ ጌታቸው በረገጠው የአማራና የአፋር መሬት የፈጸመው ተግባሩ ይፋ እየሆነበት ያለውን ወራሪ ሃይል በማጀገን የኢትዮጵያን መከላከያ ገለው እንደጨረሱ ለማሳየት ” የተበጠሰና ድምጽ ተመሳስሎ የተሰራ” የተባለውን ቪዲዮ በቲውተር ገጻቸው ይፋ እንዳደረጉ ሁለት አይነት ግብረ ምላሽ አጋጥሟቸዋል።

ቲዊት ሲያደርጉ የአናባና የጀግንነት ውዳሴ የሚጎርፍላቸው አቶ ጌታቸው፣ አልፎ አልፎ “ጀግና” ያሏቸው ቢኖሩም፣ ወዲያውኑ አቶ አስማማው ሪፖርቱን አስቀድመው ራሳቸው እንደሰሩት ጠቅሰው ትክክለኛውን መረጃ በማሰራጨት እንዴት እንደተሰረቀ አሳይተዋል። አቶ ጌታቸው ድርጅታቸው ትህነግ ፊልም ቆርጦና አመሳስሎ ማሰራጨቱ ሲገለጽበት ማስተባበያም ይሁን ሌላ ምላሽ አልሰጠም።

“መከላከያም ሆነ ከብልጽግና ጋር ያለህ በሙሉ እጅህን ስጥ” ሲሉ ዶክተር ደብረጽዮን በተደጋጋሚ ጥሪ ማቀረባቸው፣ አቶ ጌታቸውም ” ጦርንርቱ አልቋል፤ አብይና የአብይን ተከታዮች …” እያሉ ማስጠንቀቂያ ሲሰጡ እንዳልነበር፣ የቀድሞ ለተናል ጀነራል ጻድቃንም ” ከማን ጋር ነው ውይይቱ” ሲሉ ጦርነቱ መተቃለሉንና ለትህነግ የሚወግኑ ሚዲያዎችና አገራት ትህነግ አዲስ አበባን ለመያዝ ቀናት እንደቀሩት እያወጁ ባለበት ወቅት፣ ትህነግ ስልታዊ ማፈግፈግ ማድረጉን አስታውቋል።

በራሱ ደጋፊዎች ሳይቀር ተቀባይነት ያገኘ የማይመስለው የትህነግ የማፈግፈግ ጉዳይ መነጋገሩያነቱ ሳይደበዝዝ ” በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ገደልኩ” ለማለት የተዘጋጀው የሃሰት ፊልም ” በማፈግፈግ አስር ሺህ ሰው ይገደላል እንዴ” በሚል ” ጌቾ ተፎግረሻል” ተብሎ መፈገጊያ ቀልድ ተሰንዝሮበታል። ፊልሙ በማይጸብሪ ግንባር አብይ አህመድ ሙሉ ማብራሪያ ሲሰጣቸው ከተቀረጸው ፊልም ላይ የተመነተፈ መሆኑ ከፊልሙ ይከታተሉ ዘንድ አትመነዋል።

Asmamaw Ayenew@asmaheran·2hውጊያ ሳይደረግ ስልታዊ ማፈግፈግ ነዉ ያደረግነው ሲል የነበረው @reda_getachew አሁን ደግሞ ሌላ ውሸት ይዞ መጥቷል። ጄኔራሉ ይህን ያሉት @AbiyAhmedAli የአዲስ አመት ማይጸብሪ ግንባር ጉብኝት ወቅት ሲሆን 10K የሞቱት ደግሞ የ@tplf ታጣቂዎች ናቸው::

በዚህ ደረጃ ትህነግ ፊልም ሲመረት ማርቲን ፕላውት ለአልጃዚራ ” ደሴና ኮምቦልቻን ጨምሮ በረካታ ቦታ ሲይዙ መስዋዕትነት ከፍለዋል” ሲል ምን እየሆነ እንደማይገባው አመልክቷል። በሌላ በኩል ጥቃት እንደሚጀመሩ መናገራቸውን ማስታወቁ የኤርትራ የስለላ ድርጅት ዕቅድ ሁለት ሲል ትህነግ ሊሞክረው ስላቀደው አዲስ ግንባር ፍንጭ ሰጥቷል።

See also  "ሁመራ ተረፈች"ከአፋር መልስ አሸባሪው ሃይል አስከሬን በማጓጓዝ " በጅምላ ተጨፈጨፍን" የሚል ቪዲዮ እያዘጋጀ ነው

መንግስትን የሚያጠለሽ መረጃ እንደሚሰጠው ተነገሮት መረጃውን ሊወስድ የተቀጠረበት ቦታ ሲደርስ ሊጥ የተደፋበት ማርቲን ፕላውት፣ አልጀዚራ ላይ ሲያወራ በሆነው ነገር ስሜቱ የተበላሸ መሆኑንን መደበቅ እንዳልቻለ ለማየት ተችሏል።

መንግስት ትሀንግ “ሁለተኛ ስጋት እንዳይሆን ይደረጋል” ከማለቱ በቀር፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ” መጀመሪያ ህዝባችንን ነጻ እናውጣና ቀጣዩን ጉዳይ ከዚያ በሁዋላ እናየዋለን” ሲሉ ቀሪ ጉዳይ እንዳለ ፍንጭ መስተታቸውና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉብኤ አቶ አገኘሁ ” በቀናት ውስጥ ታላቅ ድል ይመዘገባል” ሲሉ በድሬደዋ የብሄር ብሄረሰቦች በዓል ላይ መናገራቸውና በርካታ ዕልህ የወለዳቸ አመራሮችና ባለስልጣናት፣ እንዲሁም የተቀናጀው ሃይል በተመሳሳይ “ወደፊት” ማለታቸው ሁለተኛ የሚባለው ዘመቻ ስለመጀመሩ አመላካች እንደሆነ እየተሰማ ነው። ከምንም በላይ ሕዝብ ግፊት እየፈጠረም መሆኑ በገሃድ እየታየ ያለ ጉዳይ ነው።

Leave a Reply