1 ሺሕ 563 አማራዎች የማይካድራ ሰማዕታት አንድ ዓመት ሞላቸው

የአሸባሪው ቡድን ጥቅምት 30 ዘጠኝ ስዓት ጀምሮ እስከ ህዳር አንድ ድረስ አማራን ለይቶ በማይካድራ ጭፍጨፋ አካሂዷል፡፡

ትሕነግ በማኒፌስቶ የቀረፀውን አማራን የማጥፋት ግብ ላለፉት 50 ዓመታት በወልቃይት ጠገዴና አከባቢው ብሎም በሌሎች አካባቢዎች አፓርታይድ አገዛዝ በመዘርጋት ከእርስታቸው በማፈናቀል የጅምላ እስር በማካሄድ እንዲሁም አማራ በመሆናቸው ብቻ አፍኖ በመውሰድ የፈፀመውን የድብቅ የጅምላ ግድያ በማይካድራ በግላጭ ጭፍጨፋ ፈፅሞታል፡፡

ጥቅምት 30/2013 የጅምላ ጭፍጨፋው ከመጀመሩ ቀደም ብሎ፣ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈፃሚው ሕወሓት የትግራይ ተወላጅ የሆኑና ዐማራ የሆኑትን ለመለየት መታወቂያ ካርድ እየተመለከቱ ማጣራት ማድረጉ ይታወቃል፡፡ አሸባሪው ትሕነግ የጅምላ ጭፍጨፋውን ከመጀመሩ በፊትም የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ሴቶች እና ህፃናትን ጥቃቱ ከመጀመሩ በፊት አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ተነግሯቸው እንደወጡ የዓይን እማኞች ገልጸዋል።

ጭፍጨፋው ሲጀመር በልዩ ሁኔታ የዐማራ ብሔር ተወላጆች በብዛት በሚኖሩበት ልዩ ስሙ ‹‹ግንብ ሠፈር›› በሚባለው መንደር እስከ ወልቃይት ቦሌ ሠፈር ድረስ የሚገኙ ወገኖቻችን፣ ግፍና ጭካኔ በተሞላበት መንገድ ተጨፍጭፏል።

አሸባሪው ትሕነግ ማይካድራ ላይ ያደረሰውን ጭፍጨፋ ያጠናው የጎንድር ዩኒቨርስቲ 1ሺሕ 563 አማራዎችን ለሞት 81 ሰዎችን ለአካል ጉዳት 1ሺሕ 644 ሰዎችን ደግሞ ለስነ ልቦና ቀውስ እንዲዳረጉ ማድረጉን አጋልጧል፡፡

የኢትዮጵ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ከተባበሩት መንግስታት ሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽን በጋራ ባደረጉት ምርመራ የማይካድራ ጭፍጨፋ ላይ ትሕነግ ካሰማራው ሳምሪ ከተባል ገዳይ ቡድን በተጨማሪ የወራሪው ሕወሓት ልዩ ኃይል ፖሊስ፣ ሚሊሻ እንዲሁም እስከ የሽብር ቡድኑ ታችኛው መዋቅር ድረስ የተዘረጋ ተላላኪ ድረስ እንደተሳተፉበት በምርመራ አርጋግጠናል ብሏል፡፡

የጭፍጨፋው ሰለባ ቤተሰቦች ሆኑ ከሞት የተረፉ ተጎጂዎች እንደሚናገሩት በማይካድራ  አማራዎች ላይ የተደረገው ጭፍጨፋ በካባቢው በሚኖሩ የትግራይ ባለሃብቶችም ድጋፍ የታከለበት ነበር፡፡ ለጭፍጨፋው የሚውሉ የጦር መሳሪያም ሆነ ስለታማ መሳሪያ እንዲሁም ለገዳይ ወጣቶች የአልኮል መጠጥና ገንዘብ እንዲሁም የእሬሳ ማመላለሻ ጭነት መኪናና ትራክተር ያቀርቡ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

ባለፉት ሠላሳ ዓመታት ዓለም ጀሮ የነፈገው የትሕነግ የዘር ማጥፋት ወንጀል በወልቃይት ጠገዴ የዐማራ ሕዝብ ላይ ግፉ ብዙ ነው፡፡ የማይካድራን ጭፍጨፋ ስናስብ ደግሞ ጭፍጨፋው የፀረ-ዐማራ ትርክት ውጤት ስለመሆኑ ልብ ልንለው ይገባል፡፡ ተግባሩም አማራን የማጥፋት የመጨረሻው ደረጃ በግላጭ የፈፀመበት ነው፡፡

አሁንም በወረራ በያዛቸወ አከባባቢዎች እደረገ ያለው የዚሁ የጥፋት ታሪኩ አማራን ማጥፋት ኢትዮጵያን ማፍረስ አካል ነው፡፡ ካለፈው ሰኔ ወር ጀምሮ በቆቦ፣ አጋምሳ፣ ንፋስ መውጫ፣ ጭና እና ኮምበልቻ የተፈፀመው የጅምላ ጭፍጨፋ፣ ወያኔ በዐማራ መቃብር ሀገረ-ትግራይን የመፍጠር ምኞቱ አካል ነው፡፡ via walta

Leave a Reply