22 የአሸባሪው ካዋርጃ አባላት ባሌ ውስጥ በቁጥጥር መዋላቸውን ፖሊስ አስታወቀ

መሣሪያ ታጥቀው በባሌ ደኖች ውስጥ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 22 የአሸባሪው ካዋርጃ አባላት በፀጥታ ኃይሎች ጥምረት ባሌ ውስጥ በቁጥጥር መዋላቸውን የዞኑ ፖሊስ አስታወቀ።

የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ የኦሮሚያ ፖሊስ እና ሚሊሺያ ባደረጉት የተቀናጀ ክትትል አንድ የውጭ ሀገር ዜጋን ጨምሮ የእስልምና ሃይማኖትን የሚሰብኩ በማስመሰል ለሽብር ድርጊት ሰዎችን ሲያሰለጥኑ እና ሎጂስቲክስ ሲያቀርቡ የነበሩ የቡድኑ አባላት ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ነው ፖሊስ የገለጸው።

የፀጥታ ኃይሎች እንደገለጹት የቡድኑ አባላት ወጣቶችን እና ተሰሚነት ያላቸውን ግለሰቦች በመምረጥ የሸሪአ ሕግ የሚያስተምሩ በማስመሰል ወታደራዊ ሳይንስ ሲያስተምሩ ነበር።

በተጨማሪም ትክክለኛው የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ እናንተ ብቻ ናችሁ በሚል ትርክት ሞልተው ሌሎች ሰዎችን እንዲጠሉ እና የአጥፍቶ ጠፊ ድርጊት እንዲፈፅሙ የሚያሰለጥኑ መሆኑም ተገልጿል።

በቁጥጥር ስር የዋለው የአሸባሪው ካዋርጃ ቡድን ለሦስት ወራት ፑንት ላንድ ውስጥ ወታደራዊ ሳይንስ የሰለጠኑ አባላትን ያካተተ መሆኑን ኦቢኤን ዘግቧል።

Leave a Reply