ሰሚ ያጣው የአሜሪካ ኤምባሲ በ10 ቀን ውስጥ ብቻ ለ13ኛ ጊዜ ዜጎቹ እንዲወጡ ልመናውን ቀጥሏል

በሃሰት መረጃ ለማሸበር በሚያደርገው ጥረት ሰሚ ያጣው በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ዜጎቹ እንዲወጡ መማፀኑን ቀጥሏል።

አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ጫና ለማሳደር ውስጥ ለውስጥ ከሚሸርበው ጫና የማሳደሪያ ሴራ ባሻገር በማኅበራዊ ትስስር ገጾቹ በኩል ዜጎቹን ከኢትዮጵያ እንዲወጡ የሚማፀንበት መልዕክት በ10 ቀን ውስጥ ብቻ ለ13ኛ ጊዜ ከግማሽ ሰዓት በፊት አሰራጭቷል።

ሆኖም ከኢትዮጵያ እውነት ጎን የቆሙ አሜሪካዊያንን ጨምሮ በርካታ የውጭ ዜጎች የሚያሰጋ ነገር አለማስተዋላቸውን በመግለፅ ኤምባሲውንና የባይደንን አስተዳደር እየተቃወሙት ይገኛል።

በሺሕዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን የማኅበራዊ ትስስር ገጾች ተጠቃሚዎችም ኤምባሲው በሚለጥፈው የፈጠራ ሽብር ነዥ መልዕክቶቹ ስር በመግባት እያወገዙት ይገኛሉ።

ኢትዮጵያ ውስጥ እንደፈለገው የሚዘውረውን መንግሥት ያጣው የባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ለመምከር ከኢትዮጵያ ውጭ ወደሆኑ አገራት እየባዘነ ይገኛል።

የአሜሪካ መንግሥት የአሸባሪውን ሕወሓት ዓላማ ለማሳካት እየጣረ ቢሆንም ኢትዮጵያዊያን የሽብር ቡድኑን ወደ ተመኘው ሲኦል ሊሸኙት በገባበት ሁሉ እየደመሰሱት ነው።

የኢትዮጵያዊያን ዘመናዊ ቅኝ ግዛትን አንቀበልም የሚል ትግል ዓለም ዐቀፍ ቅርፅ ይዞ የአሜሪካ መንግሥት ከፍ ያለ ተቃውሞና ትችትን እንዲያስተናግድ እያደረገውም ነው። via (ዋልታ)

Leave a Reply