«ልጄንና የእህቴን ልጅ እጃቸውን ወደ ኋላ አስረው ይዘዋቸው ከግቢ አውጥተው ገደሏቸው» ሂውማን ራይትስ ዎች

ሂውማን ራይትስ ዎች በአማራ ክልል ንጹሀን ዜጎች መጨፍጨፋቸውን ማረጋገጡን የዐይን እማኞችን በመጥቀስ ወንጀሉን አጋልጧል‼

– የ70 አመቱ አዛውንት ምስክርነት

የ70 አመት የእድሜ ባለጸጋ የሆኑትና ሂውማን ራይትስ ዎች የዓይን እማኝ ናቸው ብሎ የጠቀሳቸው አዛውንት በአሸባሪው የህወሓት ቡድን የ23 ዓመት ልጃቸውን እና የ24 ዓመት የእህታቸው ልጅ እንደተገደለባቸው በሪፖርት ገልጿል።

ጭና ጉሽ ሜዳ አጠገብ እአአ ከመስከረም 2/2021 ሁለት የአሸባሪው ቡድን አባላት በአዛውንቱ ግቢ ገብተው መታወቂያ ይጠይቋቸዋል። አዛውንቱ ታጣቂዎቹን ማን እንደሆኑ፣ ከየት እንደመጡም መልሰው ሲጠይቋቸው የአከባቢው የፀጥታ አባላት እንደሆኑ ነገሯቸው፡፡ ነገር ግን ታጣቂዎቹ የአሸባሪው ቡድን አባል ነበሩ።

“ልጄንና የእህቴን ልጅ እጃቸውን ወደ ኋላ አስረው ይዘዋቸው ከግቢ አውጥተው ገደሏቸው ከዛም ወደ እኔ ተመለሱ። እንዳይገድሉኝ ለመንኳቸው። ጥለውኝ ሄዱ”

በአማራ ክልል ንጹን ዜጎች መጨፍጨፋቸወን አረጋግጫለሁ ብሏል!

– ሁለተኛው የዓይን ምስክር ቃል‼
እአአ መስከረም 9/2021 የአሻባሪው ቡድን ታጣቂዎች ቆቦ አከባቢ ምግባታቸውን እና በርካታ ንጹንን መግደላቸውን መመልከታቸውን ሁለተኛው የዓይን እማኝ ለሂውማን ራይትስ ዎች ተናግረዋል።

በተባለው ቀን 8 ሰዓት አከባቢ የአይን ምስክሩ ቤት ተንኳኳ። “…በቀዳዳ ስመለከት 50 የሚደርሱ ታጣቂዎች ቆመው አየሁ። ከእነሱ መካከል አምስቱ ወደ ቤቴ ውስጥ ገቡ። ደነገጥኩ። ጮህኩም። ታጣቂዎቹ ግን ቤቴ ውስጥ የነበሩትን አራት ጎረቤቶቼን ጎትተው አወጣቸው። ያለምንም ርህራሄም ተኩሰው ገደሏቸው። እነሱን ለምን መርጠው እንደገደሏቸው የማውቀው ነገር የለም” ሲል የዓይን እማኙ ቃሉን ለአምንስቲ ተናግሯል።

– ሶስተኛ የዓይን እማኝ‼
የአይን እማኞች እንደነገሩኝ በሚል ሂውማን ራይትስ ዎች ባቀረበው ሪፖርት መሰረት፤ የአሸባሪው ቡድን ታጣቂዎች ንጽሀንን ከለላ አድርገው ወደ መከላከያ ሰራዊት ሲታኮሶ ቆይተዋል። ይህም ዓለም አቀፍ የጦር ወንጀል ነው። ይህን በተመለከተ መልስ እንዲሰጡበት ለአሸባሪው ቡድን አመራሮች የተጠቃለለ ሪፖርት ቢልክ መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም ሲል ሂዊውማን ራይትስ ዎች አስታውቋል።

– አራተኛዋ የዓይን እማኝ‼
የጭና ነዋሪዋ ማርታ የአሸባሪው ቡድን ታጣቂዎች ግፍ ሰለባ ናት። እርስዎም የደረሰባትን ትናገራለች፤

“ታጣቂዎቹ ወደ ቤቴ በመግባት ምግብና መጠጥ ጠይቀውን ሰጠናቸው። ተመግበው ሲጨርሱ ባለቤቴንና የወንድሙን ልጅ እደበደቡ ይዘዋቸው ወጡ። እኔም መለየት አልችልም ብዬ ተከተልኳቸው። እንድመለስ ቢነግሩኝም አልመለስም ብዬ ስከተላቸው ደበደቡኝ። በትግረኛ ያወራሉ።
የሚሉትን መረዳት አልቻልኩም። ከዛም በአማርኛ ባለቤቴንና የወንድሙን ልጅ የሰራዊት አባላት ነበራችሁ አይደል ሲሉ ጠየቋቸው። እነሱም አርሶ አደሮች ነን ሲሉ መለሱላቸው፡፡ አንደኛው ታጣቂ ባለቤቴን ፊቱን አዞሮ እንዲንበረከክ አዘዘው። ከእነሱም መካከል አንደኛው ባለቤቴን ከጀርባ ተኩሶ ገደለው። እኔም እራሴን ሳትኩ፡፡ የባለቤቴን ወንድም ይልቀቁት ይግደሉት እስካሁን የማውቀው ነገር የለም” ስትል ተናግራለች፡፡ via EPD

Leave a Reply