ይህ ነው የሆነው “በረከትና እርግማን”ያዩትን መግለጽ ያቃታቸው አቶ ጀማል

አንዳንድ የህበረተሰብ ክፍል ሃብት አለው። የአፋር ሕዝብ ሃብት የለውም። አገር፣ እምነትና ቤተሰብ ግን አለው። ይህን ሶስት ነገር አጣ። የእምነት ቤቱ ውስጥ ተጸዳዱ፣ ለሙስሌሞች ልዩ ሃይላና ክቡር ነገራቸው የሆነውን ቁርአን አቃጠሉ። ተጸዳዱበት። ልጆቹን ደፈሩ። ቤሰቦቹን ገደሉበት። ያሉትን ሶስቱንም ነገሮች አሳጡት። የቀይ መስመር እንግዳ አቶ ጀማል የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ ከተናገሩት።

አቶ ጀማል ያዩትን ለመናገር በመቸገር፣ ያዩትን ማመመን እንዳቃታቸው መደበቅ ሳይችሉ ራሳቸውን በመግዛት ሙግት ውስጥ ሆነው የሰጡት ምስክርነት ስሜት የሚፈታተን ነው። የዕምነት ቤቶች እንዴት እንደረከሱ፣ የሰው ልጅ እንዴት እንደተሰቃየና ተቋማት እንዴት እንደፈረሱ የገለጹበት መንገድ ” ጥራኝ ዱሩ” ያሰኛል። “በእርግጥም ከትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ሃይላና የገሃድና የስውር ደጋፊዎቹ ጋር ኢትዮጵያ ምን ቀረት” በሚል “መገላገል ይሻላል” የሚሉ ወገኖች ስቃይና የድምዳሜያቸውን መነሻ የሚያሳይ ነው።

“ወረራው እጅግ አስጨንቆ ነበር።ሕዝብ ሰግቶ ነበር። ዘመቻውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲመሩት እንደ ዜጋ ከፍተኛ ስሜት ፈጥሮብኛል። ውጤቱንም አስደሳች ነው ” ሲሉ አቶ ጀማል አስታወቀው ድሉን “ኢትዮጵያን አምላክ ጥሎ አይጥላትም ” የሚባለው ትክክል መሆኑንን እንዳረጋገጠላቸው ገልጸዋል። ይህንኑ ጉዳይ ” በመርገምት ውስጥ የበቀለ በረከት” ብለውታል።

አትላንታ የባንክ ባለሙያና ሃኪም ወንድም እህቶች እንዳሉዋቸው ያስታወቁት ፖለቲካውን አያውቁም። ምንም ውስጥ የሉም። ሚዲያው ላይ ያለውና የአክቲቪስቱ ነገር አይመቻቸውም። ነገር ግን አሁን ሁሉን ትተው “በቃ” ሲሉ ዘመቻውን እንደተቀላቀሉ ያመለከቱት አቶ ጀማል፣ የህልውና ዘመቻውን ተከትሎ ሕዝብ እንደ አንድ መነሳቱ የወቅቱ በረከት መሆኑንን አመልክተዋል። “ብዙ ወድሟል። የሚያሳስበኝ ሕዝቡ ላይ የደረሰው የስነ ልቦና ጉዳት ነው። እምነቱን፣ ባህሉን፣ አገሩን፣ ቤተሰቡን አጥፍተውበታል … ” ሲሉ የትግሬ ወራሪ ሃይል ያደረሰውን ግፍ ኮንነዋል።

መስማታቸውን ገልጸው እንደተናገሩት እጅግ በሃይማኖቱና በቀኖናው ጥብቅ በሆነው የጎንደር ሕዝብ ቤት አምልኮ (ቤተክርስቲያን) ውስጥ ተጸዳድተዋል። የማይገባ ተግባር አከናውነዋል።

ኮምቦልቻና አፋር ቅዱስ ቁርአን ማቃጠላቸውን። መስጂድ ውስጥ በመጸዳዳት የሕዝብን ስነ ልቦና ማበላሸታቸውን በአይናቸው እንዳዩ የተናገሩት አቶ ጀማል፣ በድርጅታቸው ስር ባለ አንድ የምግብ ማምረቻ ፋብሪካ ላይ ያደረሱትን ውድመትና የስራ አስኪያጁን ቢሮ መጸዳጃ በማድረግ ከሰውነት ተራ የወረደና ለማመን የሚከብድ ድርጊት መፈጸሙን አምልክተዋል። አስከትለውም መጋዘኑ በሴቶች ደምና ኮንዶም…. ሙሉውን ከሳቸው ቪዲዮ ሊንኩን ተጭነው ወይም ከታች ያድምጡ

Leave a Reply