ቻይና-አሜሪካን በሽብር ስም ከ37 ሚኒዮን ሕዝብ በላይ ከተፈጠሩበት ምድር እንዲፈናቀሉ አድርጋለች

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ ዋንግ ዊንቢን ራሷን ጻድቅ አድርጋ የምታቀርበውን አሜሪካ ከነግብሯ አሳይተዋል። “የሽብር ላይ ጦርነት” በሚል አሜሪካኖች በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ንጽሃንን ከተለያዩ ሀገራት እንዳፈናቀሉ በማስረጃ አስደግፈው ወንጅለዋል። እሳቸው ባይገልጹትም አሜሪካ አንድ ሉዓላዊ አገር ማፍረስና መውረር ስትፍልግ በዋናናት የምትለጥፈው ታርጋ ” አሸባሪ” የሚል ሲሆን ዓላማዋን ለማሳከትና ህጋዊ ሽፋን ለማግነት እንዳሻት የምትጋልባቸውን ዓለም ዓቀፍ ተቋማት እንደምትጠቀም በተደጋጋሚ ምሁራን አስታወቀዋል።

አሜሪካ እንደ ሀገር ከተመሠረተች ጀምሮ የዕድሜዋን ዘጠና ሁለት በመቶ ያሳለፈቸው ወይም የተጠቀመችው በሌሎች አገራት ላይ ጦርነት በማካሄድ መሆኑንን የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማስረጃቸውና በቁጥር አስደግፈው በማህበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ይፋ አድርገዋል። ይህ በመረጃ የተደገፈ መረጃ በስፋት መነጋገሪያም ሆኗል።

እኤአ ከ1992 እስከ 2017 ድረስ ባሉት ሃያ ስድስት ዓመታት ብቻ አሜሪካ ለ188 ያህል ጊዜ በሌሎች ሀገራት ላይ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነት ፈጽማለች። በዚህ የአሜሪካ ወታደራዊ ጣልቃገብነት የተነሳም የተለያዩ አገራት ወይም ጣልቃ የተገባባቸው አገራት ከፍተኛ ለሚባል ፓለቲካዊ፡ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ውጥንቅጥ ተዳርገዋል። አንዳንዶቹ ረዥም ጊዜ ቆይተውም ከዚህ ውጥንቅጥ መላቀቅ ሳይችሉ ቀርተዋል።

አሜሪካ “ሽብርን ለመዋጋት” በሚል ባካሄደችው ጦርነት ከሰላሳ ሰባት ሚሊዮን በላይ የተለያዩ ሀገራት ንጽሃን ዜጎች ከተፈጠሩበት የሀገራቸው ምድር ተፈናቅለዋል። አሜሪካ በኢራቅ፡ በአፍጋኒስታን፡ በየመንና በሶሪያ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት ያደረገችው ወታደራዊ ዘመቻ ለዜጎቹ መፈናቀል ዋና ምክንያት መሆኑን ባለስልጣኑ ገልጸዋል።

Leave a Reply