የወገን ጦር ወልደያን ከበበ፤ በርካታ ከተሞችን አጸዳ፣ “በውጫሌና ውርጌሳ የተቆረጠውን ወራሪ ሃይል ሙሉ በሙሉ ደመሰሰ”

ጀግኖቹ የኢዮጵያ የጸጥታ ሃይሎችና የኢትዮጵያ አይረ ሃይል ተወዳጅተው ባካሄዱት ጥቃት ተቆርጦ በውጫሌና ውርጌሳ መሽጎ የነበረውን የትግራይ ነጻ አውጪ ወራሪ ሃይል ሙሉ በሙሉ መደምሰሱ ተገለጸ። ጠላትን ማጥቃቱና ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በርካታ ከተሞች በወገን እጅ የገቡ ሲሆን ወልደያ መከበቧና በአካባቢው ያለው ወራሪ እጅ ከመስጠት ውጭ ሌላ ማራጭ እንደሌለው እየተገለጸ ነው።

የኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት መርሳና ጊራናን በመቆጣጠር ወደፊት እየገሠገሠ መሆኑንን ያስታወቀው የመንግስት ኮሙኒኬሽን መንግስት በመሆኑ ቁጥበንት ያለው ዜና አስተላልፎ እንጂ ሰፊ ቁጥር ያለው የትህነግ ሰራዊት የተደመሰሰ ሲሆን፣ ጉድባውና ሸለቆው ሁሉ አሳዛኝ ክስተት የተሞላ እንደሆነ ምስክሮች አመልክተዋል።

በተራቀቀ ካሜራ የሚንቀሳቀሱት ድሮኖችና ዘመናዊ ተዋጊ ጀቶችን የታጠቀው አየር ሃይል እግር በግር እየተከተለ በሚወስደው እርምጃ የታጀበው እግረኛው ጦር በየስርቻው የሚገባውን ሃይል ከአካባቢው ሚሊሻ ጋር በመሆን እያጸዱ መሆናቸውን የሚገልጹ ” የሚታየው ሁሉ ያሳዝናል” ሲሉ ነው የሚገልጹት።

የትግራይ ወራሪ ሃይል በአማራና አፋር ክልሎች ዘልቆ ገብቶ የፈጸመው ወንጀልና ቀደም ሲል በመከላከያ ሰራዊት ላይ ካደረሰው የክህደት ወንጀል ጋር ተዳምሮ በቀሰቀሰው የቁጣ ሃይል ከደጀን እስከ ግንባር የተፈጠረው አንድነት የትህነግን ሃይሎች እያፈራረሰ መሆኑንን በተለያዩ ሚዲያዎች ዜጎችና አመራሮች እየገለጹ መሆኑ ይታወሳል። በተመሳሳይ ” ለስልታዊ ማፈግፈግ ሲባል ነው” በሚል ያለ ውጊያ ከያዛቸው ስፍራ እየለቀቀ መሆኑንን የትግራይ ነጻ አውጪ አመራሮች መናገራቸው ይታወሳል። ስልታዊ ማፈግፈጉ ግን የት ድረስ እንደሚደርስ አላስታወቁም። መንግስት መግለጫ ከመስተቱ በፊት አቶ ጌታቸው ረዳ አየር ሃይል በሰቆጣ ድብደባ መፈጸሙን አስታውቀው ነበር።

በቆቦ ግንባርና ወልደያ ዙሪያ ያለው የትህነግ ሃይል ከሉት ተዋጊዎች በሙሉ ሰፊ ስልጠና የወሰደ በመሆኑ ሳይመታ ሰብሮ እንዲወጣ ትንቅንቅ እያደረጉ ቢሆንም በሁሉም አቅጣጫ በመዘጋቱ ” እየዋጀጀ” እንደሆነ ግንባር ያሉ አመራሮችና ሃላፊዎች እየገለጹ ነው። አልፎ አልፎ ከሩቅ ከባድ መሳሪያ በመተኮስ ሽፋን ለመስጠትና ወራሪውን ሃይል ለማስወጣት የሚደረገውን ሙከራ አየር ሃይል ስለሚያተቃው እሱም እንዳልሆነ ተመልክቷል። ያም ሆኖ ግን ከሸዋ የተገፋው፣ ከጋሸና ግንባርና ከመላክው የወሎ ግንባር ከመደምሰስ፣ ከማረክና ከመቁሰል ተርጎ ተገፍቶ ወደ ቆቦ መስመርና ሰቆጣ፣ እንዲሁም ወልደያ የተከማቸው ሃይል ቁጥሩ ከፍተኛ በመሆኑ ከከበባ ሳይወጣ እዛው ለማስቀረት ሰፊ ዘመቻ እንደሚጠይቅና ዋጋም እንደሚያስከፍል ውጊያውን የሚያውቁ ይናገራሉ።

See also  በትግራይ ያለው የእርዳታ ምግብ ክምችት የፊታችን አርብ ያልቃል፤ ትህነግ 170 መክኖችን እህል ጭነው እንድይገቡ ከልክሏል

የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ የሚሰኘው ወራሪ ሃይል በሄደበት የሚጸዳዳ፣ ያገኘውን በድርጅትና በግል የሚዘርፍ፣ ሰፊ ማህበራዊ ቀውስ የፈጠረ፣ በረካታ ንጹሃንን በጅምላ የፈጀ፣ አዛውንቶች ሳይቀሩ የደፈረ፣ መሰረታዊ የመገለገያ ተቋማትን ያወደመ መሆኑ በምስል ለህዝብ ይፋ መሆኑ ከጀመረ ወዲህ ሕዝብ እጅግ እየጠየፋቸው መሆኑ በየአቅጣጫው በሚገልጽባትና የፖለቲካው ጨዋታ መቀየር እንዳለበት በስፋት እየተነገረ ባለበት በአሁኑ ሰዓት የጦሩ ወደ ወልደያ መገስገስና አልፎ ሄዶ በሌላ ግንባር ዋጃን መቆጣጠር ቀጣዩን ዕቅድ አጓጊ አድርጎታል። የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ዛሬ ” ሰበር” ሲል የሚከተለውን መግለጫ አሰራጭቷል።

የአትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች ጥምረት በቆቦ ግንባር ቀደም ብሎ የዞብል ከፍተኛ ቦታዎችን ተቆጣጥሮ የነበረ ሲሆን፣ በራያ ሰሜናዊ አቅጣጫ ያሉትን ከፍተኛ ቦታዎችን ጨምሮ ተቆጣጥሯል፡፡

በዞብል ደቡብ አቅጣጫ ደግሞ የጉራ ወርቄ አካባቢዎችን ተቆጣጥሮ የነበረው የወገን ጦር አሁን ደግሞ የጉራ ወርቄ ከፍተኛ ሰንሰለታማ ቦታዎችን ሙሉ በሙሉ በማጽዳት፣ ቀደም ብሎ የተቆረጠውን የወልድያ መቀሌ መሥመር አሰፋፍቶ፣ ወደ ወልድያ በቅርብ ርቀት እየገሠገሠ ይገኛል፡፡

ባለፈው ጊዜ ውጫሌ ከተማን ነጻ ያወጣው የወገን ጦር፣ በዚሁ ግንባር የውጫሌ ወረዳን ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር የውርጌሳ፣ የሊብሶ፣ የጊራና፣ የመርሳ፣ የኪሌ፣ ከተሞችንና በሰሜን ወሎ የሐርቡ ወረዳን ከፍተኛ ሰንሰለታማ ተራሮችን በእጁ አስገብቷል፡፡

በእነዚህ የማጥቃት እንቅስቃሴዎች ጀግኖቹ የወገን ጥምር ጦር በንሥሮቹ አየር ኃይላችን በመታገዝ ጠላትን ከመርሳ በስተጀርባ ቆርጦ በመግባት፣ በውጫሌና ውርጌሳ መካከል የነበረውን ጠላት ሙሉ በሙሉ ደምስሰውታል፤ ምርኮኛና ቁስለኛም አድርገውታል፡፡

የአካባቢው ኅብረተሰብ ከወገን ጥምር ጦር ጋር በመቀናጀት፣ እግሬ አውጪኝ ብሎ የሚሸሸውን ጠላት ከየጢሻው እየመነጠረ በመደምሰስ አኩሪ ጀብድ ፈጽሟል፡፡ ጠላትም የዘረፈውን ንብረትና ተተኳሾቹን ፈጽሞ ይዞ እንዳይወጣ አድርጎታል፡፡

የወገን ጥምር ጦር በወልድያና ሐራ ከተሞች መካከል የሚገኘውንና መውጫ ያጣውን ጠላት ለመደምሰስ፣ በተቀናጀና በተደራጀ መንገድ ወደ ፊት እየገሠገሠ ነው፡፡


Leave a Reply