“አብይ እንዲኮበልሉ አሜሪካ ጫና ስታደርግ፣ ‘አታስቡት ወረራውን እንቀለብሰዋለን’ ብለዋቸዋል” – ዛሬ ለስራ ከግንባር ቱርክ ገብተዋል

አብይ አሕመድን የሚጠሏቸው እጅግ ብዙ መንገድ ይሄዳሉ። የሚወዷቸውም ደግሞ ልዩ ቦታ ይሰጡዋቸዋል። የሚጠሏቸው ተደራጅተው ለተራ አሉባልተኛ እስከ ዓለም ዓቀፍ ተጽዕኖ ሚዲያ፣ አገራት፣ ግለሰቦችና ተቋማት ቢረባረቡም እሳቸው “ወይ ፍንክች” አይነት ናቸው። ከሁሉም በላይ ግን ሕዝብ ክንፉ ስር ከቷቸዋል። ይጸልይላቸዋል። እሳቸውም ” የእናቶች ጸሎት” ሲሉ ያነሳሉ። አብይ ዛሬ በቱርክ ልዩ እንግዳ ሆነዋል።

” ፈታሪ ደግ ነው መሪ ሰጦናል” ሲሉ ሚስጢር የሆነውን ጉዳይ ለሁለተኛ ጊዜ የተናገሩት የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌንዴሞ ዛሬ በቀይ መስመር ፕሮግራም ቀርበው ” አሜሪካ ወደ ውጪ አገር እንዲከዱ ስታግባባ በፍጹም አገሬን ጥዬ አልሄድም” ማለታቸውን ምስክር ሆነው አመልክተዋል። አያይዘውም ” አታስቡ ይህንን ጦርነት እንቀለብሰዋለን” ሲሉም ነግረዋቸው እንደነበር ገልጸዋል።

ጦርነቱ ወደ ሸዋ በተቃረበና የሳምንታት ጊዜ እንኳን እንደሌለ በሚዲያቸው እያወጁ ዓለም ዓቀፍ ጫና ሲያፋፍሙ የነበሩት አሜሪካኖች በጎን ” ነገሩ ተበላሽቷል” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አገራቸውን ጥለው እንዲኮበልሉ ግፊት ያደርጉ እንደነበር የመሰከሩት አቶ ደስታ ” እንደ ቃላቸው እሳቸው አመራር እየሰጡ በሁለት ሳምንት ውስጥ ወራሪውን ሃይል እንዳይሆን ሲደረግ ዓለም እንዲያይ አድርገዋል” ብለዋል። ኢትዮጵያንም በጽኑ መሰረት ላይ እየተከሉ መሆኑንን ገልጸዋል።

በነጮች እምነትና ጥገኝነት ላይ መተከሉና ያል እነሱ ድጋፍና እርዳታ ምንም ማድረግ የማይችለው የትግራይ ወራሪ ሃይል አመራሮች የአሜሪካና የአውሮፓ ደጋፊዎችቻቸውንና ታዋቂ ሚዲያዎች የሚሰጡዋቸውን ” ወሬ የፈታው” ተረት ተጠቀመው ለሁለተኛ ጊዜ ኢትዮጵያ ላይ የመንሰራፋት እድላቸው መክሰሙን አቶ ታዬ ደንደአ የሰላም ሚኒስትር ዳኤታ በተመሳሳይ ሰሞኑንን ይፋ ማድረጋቸው፣ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ወደ አረብ ኢምሬትስ እንዲኮበለሉ ተምጀቻችቶላቸው እንደነበር ሚስጥሩን ገልጸዋል።

ፊልትስ ማን የሚባሉት የምስራቅ አፍሪካ ሹመኛ በተደጋጋሚ በኢትዮጵያ ጉዳይ ተልዕኮ ተቀብለው ጎረቤት አገሮች፣አረብ ኤምሬትስ፣ ቱርክና ሌሎች አገራት እየተመላለሱ ማሳረጊያቸውን አዲስ አበባ እያደረጉ ለሪፖርት ወደ አገራቸው ሲመላለሱ መሰንበታቸው አይዘነጋም። በዚህ ምልላሳቸው ውስጥ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አገር ጥለው እንዲኮበልሉ ሲሰሩ እንደነበር ሲታማ እንደነበርም ይታወሳል። አሜሪካኖችም “የተጀመረ ጥረት አለ። ተስፋ አለን” ሲሉ ቢቆይም አብይ አሕመድ አስቀድመው እንዳሉት ” አንገቴ ይቆረጣል እንጂ” በማለታቸው እስካሁን ሁሉም ሳይሆን ቀርቷሎ።

የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር መሪዎች ገና ከለውጡ ጀምሮ ” እረኛውን ምታ በጎቹ ይበተናሉ” በሚል መርህ ከተራ ስድብና ዘለፋ ጀመሮ በግልና በቡድን ዘመቻ ከፍተው እሳቸውን ብቻ በመለየት ከሕዝብ ለመነጠል ዘመቻ ሲያካሂዱ መቆየታቸው፣ ከቆይታም በሁዋላ ይተካሂደው ዘመቻ የተሳካ መሆኑ ገምግሞ እንደነበር፣ በወቅቱ ገና ስለጦርነት ሃሳብ እንዳለ ሳይጠቆም፣ አብይ አህመድን የዓለም ዓቀፉ የጦር ወነጀለኞች ፍርድ ቤት እንደሚያቆሙና የቀሩትንም የብልጽግና ዋና መሪዎች ቂሊንጦ እንደሚጥሉዋቸው በገሃድ ይነገር እንደበር የሚታወስ ነው። አሁን ድምጹ የማይሰማው ዳንኤል ብርሃኔ ” ጊዜ መፍጀት የለብንም” እያለ በተደጋጋሚ ይህንኑ ሲያስታውቅ እንደነበርም አይዘነጋም።

በሌላ ዜና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከግንባር ወደ ቱርክ በማምራት ከፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ጋር እየተወያዩ መሆኑ ተመልክቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከቱርክ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይብ ኤርዶጋን ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል፡፡

“ከቱርክና አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን፣ እኔና የልዑካን ቡድኔ ከፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ጋር የሁለትዮሽ ውይይት ዛሬ አካሂደናል። የሁለቱ ሀገራት ታሪካዊ ግንኙነት ሁሌም በመከባበር ላይ የተመሠረተ ነው። ትብብራችን በገንቢ ተሳትፎ ላይ በመመሥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በማህበራዊ አምዳቸው አመልክተዋል።

ሶስተናው የቱርክና አፍሪካ ህብረት ስብሰባ እየተካሄደ ሲሆን ከ39 አገራት የሚወከሉ ሚኒስትር ተሰብሳቢዎችና 13 ፕሬዚዳንቶች ይካፈሉበታል በተባለው ስብሰባ ላይ ለመገኘት ልዑካቸውን ይዘው ወደ ቱርክ ያቀኑት አብይ አህመድ ነገ ፕሬዚዳንት ኤድሮጋን ንግግር ከማቅረባቸው በፊት በሁለትዮሽና በአንህጉራዊ ጉዳዮች ተወያተዋል። ዝርዝሩ ይፋ አልሆነም።


Leave a Reply