ወልዲያ ዳነች «ሰሰሜን ወሎ ሙሉ በሙሉ ከአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ነጻ ወጣ»

«ወልዲያ ነጻ ወጣች! ቆቦ፡ ስሪንቃና ሮቢትም በጀግኖቻችን ቁጥጥር ስር ውለዋል!!!! ወራሪው ሠራዊት አብዛኛው ሲደመሰስ የቀረው ቁስለኛ ሆኗል፡፡ ተበታትነው ወደ አላማጣ በመሸሽ ላይ ያሉትንም ጀግኖቻችን እግር በእግር » የሰሜን ወሎ ዞን በኢትዮጵያ የጸጥታ ኃይሎች ከአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ነጻ ወጥቷል።

በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ እየተመራ የሚገኘው ዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት በተቀናጀና በተደራጀ መንገድ ማጥቃት ከጀመረበት ጊዜ አንሥቶ አከርካሪው በመመታቱ የጠላት ፍላጎት፣ የማድረግ ዐቅም እና ሥነ ልቡናው ብትንትኑ ወጥቷል፡፡

በትናንትናው ዕለት ማምሻውን እንደተገለጸው የወገን ጦር፣ በራያ ሰሜናዊ አቅጣጫ ያሉትን ከፍተኛ ቦታዎችን ከተቆጣጠረ በኋላ፤ በዞብል ደቡባዊ አቅጣጫ ደግሞ የጉራ ወርቄ ከፍተኛ ሰንሰለታማ ቦታዎችን ሙሉ በሙሉ አጽድቶ፣ ቀደም ብሎ የተቆረጠውን የወልድያ መቀሌ መሥመር በማስፋፋት፣ ወደ ወልድያ በቅርብ ርቀት እየገሠገሠ እንደሚገኝ ተገልጾ ነበር፡፡ ሌሊቱን በሙሉና ዛሬ ረፋዱን ጀግኖቹ የመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራና የአፋር የጸጥታ ኃይሎች ከንሥሮቹ የአየር ኃይል ጋር ባደረጉት የተቀናጀ የማጥቃት ዘመቻ የሳንቃን፣ የሲሪንቃን፣ የሰሜን ወሎ ዋና ከተማ የሆነችውን ወልድያ ከተማን፣ ሐራን፣ ጎብየን፣ ሮቢትን እና ቆቦን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል፡፡

የወገን ጦር በነዚህ አካባቢዎች የመጨረሻ ሙከራውን ሲያደርግ የነበረውን የጠላት ጦር ደምስሶታል፡፡ ከድምሰሳ ተርፎ ወደ ጨርጨርና አላማጣ እየፈረጠጠ ያለውን ኃይል ደግሞ የወገን ጦር እግር በእግር እየተከታተለ ሙት፣ ቁስለኛና ምርኮኛ እያደረገው ይገኛል፡፡

የአካባቢው ኅብረተሰብ በተለይም ወጣቶች ከወገን ጦር ጋር በመቀናጀት በየጢሻው እየተሹለከለከ ለማምለጥ የሞከረውን የጠላት ጀሌ በመልቀም፣ ምንም ዓይነት ንብረት እና ተተኳሽ ይዞ እንዳይወጣ የላቀ የጀግንነት ጀብድ ሠርተዋል፡፡

እነዚህ ከተሞች ረዘም ላለ ጊዜ በጠላት እጅ የቆዩና አያሌ በደሎች ሲፈጸምባቸው የነበሩ በመሆናቸው፣ ጀግኖቹ የመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራና የአፋር የጸጥታ ኃይሎች ከንሥሮቹ የአየር ኃይል ጋር በመጣመር በፈጸሙት አስደናቂ የጀግንነት ገድል ነጻ በመውጣታቸው እንኳን ደስ ያላችሁ ለማለት እንወዳለን፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በላሊበላና በሙጃ መካከል ሾልኮ ገብቶ ጋሸናን ለመቁረጥ ሲሞክር የነበረው የጠላት ኃይል በጀግናው የወገን ጦር ከበባ ውስጥ እንዲገባና እንዲደመሰስ በማድረግ የኀሙሲት፣ እስታይሽ፣ አሁን ተገኝ፣ ድልብ፣ ኩል መስክ እና አካባቢያቸው ሙሉ በሙሉ ከጠላት ነጻ ወጥተዋል፡፡

በአሁኑ ሰዓት ጀግናው የወገን ጦር የላሊበላ አካባቢን ከጠላት በማጽዳት፣ በሰቆጣ ከተማና በዙሪያው ባሉ አካባቢዎች የመሸገውን የጠላት ኃይል እየደመሰሰ ይገኛል፡፡ እንዲሁም እግሬ አውጭኝ ብሎ ወደ ኮረም አቅጣጫ እየፈረጠጠ ያለውን ጠላት እግር በእግር እየተከተለ ሙት፣ ቀስለኛና ምርኮኛ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

የሕዝብ አደራ የተሸከሙት የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ሐሩርና ቁር ሳይበግራቸው፣ ቀን ከሌሊት በተራራማ ሰንሰለቶች እና በየሜዳው በመወርወር፣ በየደረሱበት በጠላት ላይ እሳት የሆነውን ክንዳቸውን በማሳረፍ የሽብር ቡድኑን እስትፋንስ ቆርጠውታል። በተደረገው አስደናቂ የማጥቃት ዘመቻም በአማራ ክልል የሰሜን ወሎ ዞን ከአሸባሪው ሕወሐት ነጻ ወጥቷል፡፡ በሁሉም አካባቢ የሚገኘው ማኅበረሰብ፣ ከወገን ጦር ጋር በመቀናጀት ላደረገው አስተዋጽዖ መንግሥት ምሥጋናውን እያቀረበ፤ የተለመደውን የደጀንነትና የጀግንነት ጀብድ እንዲፈጽም ጥሪ ያቀርባል፡፡

ነጻነታችንን የምናውጀው በተባበረ ክንዳችን ነው!

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

Related posts:

«ሕወሓት ጦርነትን እንደ አምልኮ የሚቆጥር ቡድን ነው» – ፕሮፌሰር ሀረገወይን አሰፋ
«በሕገወጦች ላይ ያለ ምኅረት እርምጃ መውሰድ አለብን፤ ይህ የመንግሥት ተግባር ነው» የአማራ ክልል
125 አዳዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ
«በአገሩ መከላከያ ላይ አፉን የሚከፍት ሕዝብ የለም፤ መንግስትም አይታገስም» ክብር ለመከላከያ ሰራዊት!!
በኢትዮጵያና ቱርክ መካከል የተደረገውን የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት ምክር ቤቱ አጸደቀ
የሞት ፍርደኛው የ25 ዓመታት ሰቆቃ! ከመሬት በታች የታፈኑት አባት
«ኢትዮዽያን ማስቀጠል ከሚፈልጉት ጎን በመሆናችን የሚከፋ ከአለ እርሱ መፍረሷን የሚናፍቅ ብቻ ነው!»
ደብዳቤ ለኢትዮጵያ - ከቢልለኔ ስዩም
የዓለም ባንክ የ300 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ፈረመ
"እናቴ ፍጹም እስር ቤት እንድትገባ አልፈግም" ብሎ እግሩን ያጣው ወጣት ምስክርነት ለሮይተርስ
"አልዘምትም" ወይም "ከጠላት ጎን እሰለፋለሁ" ማለት ሲቻል ማውሰብሰብና ማድበስበስ አይገባም!
አብዱላሂ ፋርማጆ ለአዲሱን ፕሬዝዳንት «ሁሉም ወገኖቼ እንዲደግፉህና እንዲጸልዩልህም እጠይቃለሁ»
መንግስ የጸጥታ ሃይሎች ለየትኛውም ዓይነት ትንኮሳ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ማድረጉን አስታወቀ
በትግራይ 5.2 ሚሊዮን ሕዝብ ዕርዳታ እየደረሰ ነው፤ ከሺህ በላይ የጭነት መኪኖች ታግተዋል፤ 76 ቢሊዮን ብር ወደ ትግራይ ተልኳል
የደህንነት ጥናት አዲሱ ምዕራፍ - ጂኦስፓሻል ኢንተለጀንስ

Leave a Reply