“የሰው ልጅ በመሆንህ ብቻ ወንድሜ ነህ” ካህሊል ጂብራን-

“የሰው ልጅ በመሆንህ ብቻ ወንድሜ ነህ ። ሁለታችንም የቅዱስ መንፈስ ልጆች ነን። ከአንዲት ምድር የተሠራን ፍጡራን።
በሕይወት ጎዳና አብረኸኝ ትጓዝ ዘንድና የእውነታን ምሥጢር እንድረዳ ታግዘኝ ዘንድ ጓደኛዬ ነህ። የሰው ልጅ ነህ ፤ ይህ ለኔ በቂዬ ነው። እንደወንድሜ እወድሃለሁ። አንተ እንደፈቀድህ ልትናገረኝ ትችላለህ። ነገ ሲደርስ ንግግርህን እንደማስረጃ ቆጥሮ ይፈርድብሃል።
ንብረቴን ልትቀማኝ ትችላለህ። ስግብግብ በመሆኔ ያካበትኩት ሀብት ካስደሰተህ ውሰደው፡፡ የፈቀድከውን ልትወስድ ትችላለህ። ነገር ግን ‘እውነቴን’ ልትነካት አትችልም ። ደሜን ማፍሰስ ፤ ሥጋዬን ማቃጠል ትችላለህ ። ሆኖም መንፈሴን መጉዳት አትችልም።
ወንድሜ ነህና እወድሃለሁ ! ባንተ መስጊድ እሰግዳለሁ ፤ በመቅደስህ እንበረከካለሁ ፤በቤተክርስቲያንህ አመልካለሁ። እኔና አንተ የአንድ ሃይማኖት ልጆች ነን። የሃይማኖት መንገዳችን ቢለያይም መንገዶቻችን በሙሉ የአንድ ፈጣሪ እጅ ጣቶች ናቸው። የፈጣሪ እጅ ለሁላችን ሙላትና የመንፈስ ስጦታ የተዘረጋ ነው።
በጨቋኞች ፊት ደካማ ፣ በስግብግብ ባለፀጋ ፊት ደግሞ ደሃ በመሆንህ እወድሃለሁ። በዚህ ምክንያት እያነባሁ አቅፍሃለሁ። ከእንባዬ ጀርባ የፍትህን እጅ አቅፈህ የፈረዱብህን ይቅር ስትል አይሃለሁ፡፡ ወንድሜ ነህና እወድሃለሁ።” – ካህሊል ጂብራን

Via Jimma high school friends ከመጻህፍትና ጸሀፊያን ዓለም….
ካህሊል ጂብራን

(Source: መሳይ መለሰ ማሩ; Book for ALL)

Khalil Gibran (1883 – 1931), born in Lebanon, a great, renowned Lebanese poet who believed and taught that there is little to be gained from speculating on the identity of persons or places represented in it. He taught about the “unity of being”, unification of the human race. He strove to resolve cultural and human conflict by transcending the barriers of East and West, societies. (REF)
http://www.gibrankhalilgibran.org/AboutGebran/Biography/


Leave a Reply