መቀለ ስር ሲካሄድ የሰነበተው ውጊያ በድል ተቋጨ፤ ስለ ድርድሩ መንግስት ይፋ መልስ ሰጠ

የሰላም ጥሪ እያሰማ ያለው የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር አብዓላ ከተማን ለመውረር ሞክሮ ሙሉ በሙሉ መደምሰሱና ውጊያው ዛሬ መፈጸሙን የአፋር ሃይሎች አካል የሆኑ በተለይ ለኢትዮ12 አመለከቱ። መንግስት ድርድሩን አስመክቶ የተቋቋመው ኮሚሽን ተግባሩ ትህነግንና ሸኔን እንደማያካትት አስታወቀ።

ትህነግ ከመቀለ ስር አፋር ክልል የምተገኘው የድንበር ከተማ የሆነችውን አብዓላ ከተማን ለመውረ የተነሳውና ሃይል ያዘመተው ከሶስት ቀን በፊት ነበር። የአፋር ሕዝባዊ ሰራዊት ጥቃቱን መክቶ ሙሉ በሙሉ በትናንትናው ዕለት ማታ ወደ አበዓላ የተጠጋውን ሃይል ሙሉ በሙሉ ማስወገዱን ከላይ የተገለጹት ክፍሎች አመልክተዋል።

ትህነግ ሊይዛት የሞከራት አበዓላ ከተማ በትንሽ ርቀት ላይ ስምሪት የሚጠባበቅ የኮማንዶና ሜካናይዘድ ሃይል እንዳለ ቦታውን በትክክል በስም ሳይጠሩ እነዚሁ ክፍሎች አመልክተዋል። ማክሰኞ በሚቆም ገበያዋ የምትታውቀውና በርካታ ፍየል ለንግድ በሚቆምባት የዞን ሁለት ከተማ አበዓላ ላይ በነበረው ጦርነት ትዕዛዝ የሚጠባበቀው ልዩ ሃይልና ሜካናይዝድ ተወርዋሪ ክፍል ድጋፍ ማድረግ ሳያስፈልግ የአፋር ሕዝባዊ ሰራዊት እርምጃ ወስዶ ድል መቀዳጀቱን የመረጃው ምንጮች አመልክተዋል።

“የምድር ላይ ድሮኖቹ በሚግባቡት ቋንቋ ወጥተው የሚደረገውን ሆኑ አድርገው ጸጥታ ወርዷል” ያሉት የአፋር አክቲቪስቶች “ትህነግ እርቅና ሰላም የሚለው ሲያምታታ ነው” ብለዋል። አቶ ጌታቸውም ሆኑ ዶክተር ደብረ ጽዮን ወታደሮቻቸውን ለሰላም ተስፋ ሲባል ወደ ትግራይ እንደመለሱ በሚያስታውቁበት ቅጽበት አበዓላን ለመውረ ሙከራ መደረጉን ዶከተር ኮንቴ ማስታወቃቸውን ገልጸን መዘገባችን ይታወሳል።

” ለሰላማ ሲባል ታላቅ ውሳኔ ወስነናል” ያሉት አቶ ጌታቸው ዓለም ሊረዳቸውና ሊታደጋቸው እንደሚገባ መግለጻቸውን ተከትሎ ” እብሪቱና ትዕቢቱ ሲያስለፈልፈው የነበረርውን፣ ጠመንጃ ነክሶ ጀመሮ ተመንጃ ነክሶ ለመሞት የሚክለፍለፈውን ሽፍታ እስከ መቸረሻው በሳት ክንዳችን እንለበለበዋለን” ሲል የምንግስት ሚዲያ ዛሬ አረፋፋዱ ላይ ልዩ ዘገባ አቅርቧል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዳዔታ ሬድዋን ሁሴን በቲውተር ገጻቸው “አንዳንድ ሰዎች ሁሉን አቀፍ ውይይትንና ድርድርን አደበላልቀውት ሲቸገሩ ይታያል” ሲሉ ትህነግ የሰላም ንግግር ጥሪ ማቅረቡን ተከትሎ መንግስትን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ በምኞታቸው በመንዳት ለማነሳሳት ለሚሞክሩ ምላሽ ሰጥተዋል።

” ውይይቱ ከዓመት በፊትም የነበረና አሁን ግን ራሱን በቻለ ኮሚሽን ተጠናክሮ የሚቀጥል ነው” ሲሉ አዲስ ሃሳብ ሳይሆን የተጀመረውን ሂደት ድርጅታዊና ህጋዊ ቅርጽ በማሲያዝ የማስቀጠል ጉዳይ እንደሆነ አቶ ሬድዋን ገልጸዋል። አያይዘውም ” ስለ ህወሓት ወይም ሸኔ አይደለም። ይህኛው የራሱ ሌላ መልክ አለው” ሲሉ አሁን ኮሚሽን የተቋቋመበት ንግግር በሽብር ከተፈረጁት አካላት ድርጅቶች ጋር አብሮ ተደባልቆ መታየት እንደሌለበት አስታውቀዋል።

ትክክለኛ መረጃ ማግኘት የሚቻልበት አውድ ሰፊ ሆኖ ሳለ ለሳንቲም ለቀማ በተቋቋሙ፣ አሁን የተገኘው ድል ባሳመማቸው ተከፋዮችና የትህነግ መክሰም የሚያሳባቸውን የመከተል በሽታ የተጣናወታቸው ክፍሎች፣ በዚህ ጥንቃቄ በሚያስፈልገበት ወቅት ላይ ስህተት ከማግበስበስ እንዲቆጠቡ የሚመክሩ ” በስህተት ለትህነግ እድል እንዳንሰጥ፣ ትግሉ ገና አላለቀም። ትግሉ መኩና ቅርጹ ሰፊ ነው። ከሁዋላው ሰፊ ብርና ሃያላት አሉ” ሲሉ አሳስበዋል። በአቶ ሬዲዋን ቲውተር ስር ” ትክክለኛ የሆነ መረጃ ማግኘት በቀለለበት ዘመን ለሆዳቸው የተሸጡ የበግ ለምድ ለብሰው ህብረተሰቡን የተሳሳተ መረጃ የሚያቃብሉ የ ሚዲያው ጡረተኞች የበዙበት ዘመን ስለሆነ በተቻለ መጠን በተረጋጋ መንፈስ ትክክለኛ መረጃ ከሚያቀብሉን አንለያቸው” የሚል አስተያየት ተመልክቷል።

“በሃሳብ ያረጡ” በሚል የሚሳቅባቸው አማትበው፣ በስመ አብ ወልድ ወ መንፈስ ቅዱስ ብለውና ከአንገታቸው ሶስቴ ዝቅ ብለው የአምላክን ስም በየቀኑ እየጠሩ ሴራ ከሚያመርቱ የዛር አምላኪዎች መጥንቀቅ እንደሚያሻ በተደጋጋሚ ሲነገር እንደነበር ይታወሳል።


Leave a Reply