ትህነግ በውጊያ በቆሰሉና በሞቱ ታጣቂዎቹ “የጅምላ ጭፍጨፋ ተደረገ የሚል” የሴራ እቅድ ማዘጋጀቱ ተጋለጠ

  • ወራሪ ኃይል የድል አድራጊ አቀባበል እንዲደረግለት ቢሞከርም ተቃውሞ እየገጠመው ነው

ታጣቂዎች ወደ ከተማ ሲገቡ ጥይት ወደ ላይ በመተኮስ በከበሮና በጡሩንባ እንዲታጀቡ ጥረት ቢደረግም በርካታ ልጆቹን መስዋዕት ያደረገውና ወደ ‹‹አዲስ አበባ ለመግባት ጫፍ ደርሰናል›› በሚል የሀሰት ፕሮፕጋንዳ እየተጭበረበረ እንደነበር የተገነዘበው ህብረተሠብ አጋጣሚውን ተቃውሞውን ለመግለጽም እየተጠቀመበት ይገኛል፡፡


በኢትዮጵያ ጥምር ጦር የተቀናጀ ጥቃት ሽንፈት ተከናንቦ ወደ ትግራይ የሸሸው ወራሪው የህወሓት ኃይል በየአውደ ውጊያው ከሞቱና ከቆሰሉ ታጣቂዎቹ የተወሰኑትን ወደ ትግራይ ይዞ በመሸሽ ላይ መሆኑን ታማኝ የመረጃ ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡

ቡድኑ ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክቶ በምስጢር ባደረገው ስብሰባ የኢትዮጵያ ጥምር ጦር አሁን ባለው ቁመናና ግስጋሴ ወደ መቀሌ በአጭር ጊዜ ሊገባ ይችላል የሚለውን መላምት ሊያጋጥሙት ከሚችሉት ችግሮች እንደ አንዱ አድርጎ የገመገመ ሲሆን፥ ይህ ከተከሰተ በሚልም ዓለም አቀፉን ማህበረሠብና የትግራይን ህዝብ የሚያጭበረብርበት የሴራ እቅድ ማዘጋጀቱ ታውቋል፡፡

እንደ መረጃ ምንጮቻችን፤ ወራሪው የህወሓት ኃይል ባዘጋጀው እቅድ መሰረት በየአውደ ውጊያው ከሞቱና ከቆሰሉ ታጣቂዎቹ የተወሰኑትን ወደ ትግራይ ይዞ በመሸሽ የመከላከያ ሠራዊት ወደ ትግራይ ከገባ “የመንግሥት ኃይል ጅምላ ጭፍጨፋ ወይም የዘር ማጥፋት እየፈጸመ ነው” በማለት በሙትና ቁስለኛ ታጣቂዎቹ ምስል ለመነገድ አስቧል፡፡

እየተቀነባበረ ያለው ሴራ ሰሞኑን የተመድ ሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት ልዩ ስብሰባ አድርጎ ካሳለፈው ውሳኔ ጋር ተመጋጋቢ መሆኑን የጠቆሙት ምንጮቻችን፥ ምክር ቤቱ ከዚህ ቀደም ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ጋር በመሆን ምርመራ አድርጎ ሪፖርት የቀረበበትን ጉዳይ እንደ አዲስ እንዲታይ በምዕራባውያን ዘዋሪነት ያሳለፈው ውሳኔ ለዚህ ሴራ አጋዥ እንዲሆን ታቅዷል የሚል ጥርጣሬ ማሳደሩን ገልጸውልናል፡፡

የመከላከያ ሠራዊት ወደ ትግራይ ቢገባ ቡድኑ ከየግንባሩ የሰበሰባቸውን ሙትና ቁስለኛ ታጣቂዎቹን ምስል በማሰራጨት የተመድ ሰብአዊ መብቶች ምክር ቤት የሰሞኑ ውሳኔ ምክንያታዊ ነው የሚል ተቀባይነት እንዲያገኝ ለምእራባውያን ታዛዥ ከሆኑ የተለያዩ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ድርጅቶችና መገናኛ ብዙሃን ጋር ተናቦ ለመስራት የታቀደ መሆኑን የገለጹት ምንጮቻችን፥ የተመድ ውሳኔ የሀገር ሉዓላዊነት የሚጋፋና ፖለቲካዊ አንድምታ ያለው ነው በሚል ከ22 ሀገራት ተቃውሞ እንደገጠመው አስታውሰዋል፡፡

See also  የፌዴሬሽን ምክር ቤትየወልቃይት ጠገዴና የራያ የማንነት ጥያቄዎች መልስ እንዲያገኙ እየሠራ ነው

በሌላ ዜና በተለያዩ ግንባሮች ሽንፈት ተከናንቦ ሙት፣ ቁስለኛና ምርኮኛ ከሆነው የህወሓት ወራሪ ኃይል የተራረፈው ታጣቂ ወደ  ትግራይ ሲገባ የድል አድራጊ አቀባበል እንዲደረግለት ቢሞከርም ተቃውሞ እየገጠመው መሆኑን ታማኝ የመረጃ ምንጮቻችን ገልጸውልናል፡፡

እንደ መረጃ ምንጮቻችን ከሆነ፤ አሸባሪው ቡድን  የፈጸመው ወረራ ተቀልብሶ ክፉኛ ሽንፈት አጋጥሞት ወደ ትግራይ  ክልል እየገባ ነው፡፡

ሽንፈቱ ሊዋጥላቸው ያልቻለው የቡድኑ አመራሮች ወራሪ ኃይሉ ከፍተኛ ድል አስመዝግቦ  የመጣ በማስመሰል የድል አድራጊ አቀባበል እንዲደረግለት እየመከሩ ነው፡፡

ታጣቂዎች ወደ ከተማ ሲገቡ ጥይት ወደ ላይ በመተኮስ በከበሮና በጡሩንባ እንዲታጀቡ ጥረት ቢደረግም በርካታ ልጆቹን መስዋዕት ያደረገውና ወደ ‹‹አዲስ አበባ ለመግባት ጫፍ ደርሰናል›› በሚል የሀሰት ፕሮፕጋንዳ እየተጭበረበረ እንደነበር የተገነዘበው ህብረተሠብ አጋጣሚውን ተቃውሞውን ለመግለጽም እየተጠቀመበት ይገኛል፡፡

በድል እንደተመለሱ ለማስመሰል የሚሞክሩት የአሸባሪው ቡድን አመራሮች ሽንፈታቸውን ለማድበስበስ እንዲሁም አሁንም የሀሰት ዘመቻውን በማቀጣጠል ህብረተሠቡ ምንም መረጃ የለውም በሚል ንቀት ለተጨማሪ እኩይ አላማቸው ለማነሳሳት ‹‹ከፍተኛ ድል አስመዝግበናል። ጠላትን ስበን ወደምንፈልገው ቦታ ያመጣነው በመሆኑ አሁን ከመቼውም ጊዜ በላይ መስዋዕትነት የሚጠይቅ ወቅት ላይ እንገኛለን፡፡ የመጣውን ጠላት ለመደምሰስ ተጨማሪ ኃይል ስለሚያስፈልግ ሁሉም ትግራዋይ  የድሉ ተቋዳሽ  እንዲሆን  ወደ ግንባር መቀላቀል አለበት፡፡ ሁሉም  ሰው ያለውንም ሀብትና ጥሪት ለዘመቻው ማዋል ይጠበቅበታል›› በማለት ቅስቀሳ እያደረጉ መሆናቸውን ምንጮቻችን አረጋግጠውልናል፡፡

via FBC


Leave a Reply