ከመከላከያ ሰራዊት ጋር በጥምረት ሲዋጉና ሲዋደቁ የነበሩት ፋኖዎች ወያኔ የአማራን ንብረት ዘርፎ መቀሌ ከገባ በኋላ የዶ/ር አብይ መንግስት ሆን ብሎ “ህወሓትን ለመታደግ ሲል መቀሌ አንገባም አለ” የሚል ጥያቄ ሊያነሱ ይችላሉ?>> ከሚለው ጥያቄ በስተጀርባ የሆነ እኩይ እሳቤ አለ።

መቼም “የአማራ ንብረት ተዘርፎ ኦሮሞ ዝምታን መረጠ ወይም የተዘረፈውን ንብረት ለማስመለስ ፍላጎት የለውም” የሚሉ በብሄር እይታ የተንሻፈፉ ምልከታዎች አይጠፉም። ይሄ የወያኔ ዘመን ጠባሳ ነው። ይሄን ጠባሳ እያከኩ ቁማር የሚጫወቱት ወይ ወያኔዎች ናቸው አሊያም ደግሞ በማወቅ ሆነ አለማወቅ የእነሱን እኩይ ዓላማ የሚያስፈፅሙ ባንዳዎች ናቸው። የአማራ ወጣት የወደመውን አከባቢ መልሶ ለመገንባት የሚያውለውን አቅምና ግዜ በበቀል ስሜት ተነሳስቶ በቁጣና እልህ ወደ መቀሌ እንዲተምም የሚኮረኩሩ አይጠፉም።

ይሄ ኢትዮጵያ ሁሌም በጦርነት ስትታመስ እንድትኖር የሚሹ ጠላቶች ፍላጎት ነው። የአማራ ወጣቶች እና ፋኖዎች ደግሞ የተሻለ ልምድና ችሎታ የሚቀስሙበት ወታደራዊ ማሰልጠኛ ገብተው መከላከያን ቢቀላቀሉ ይመረጣል። ከዚያ በተረፈ ደግሞ የሁሉም ትኩረት ወደ መልሶ ማቋቋም እና ለዚህ አስፈላጊ በሆኑ ተግባራት ላይ መረባረብ አለበት።

ጉዳዩን “አማራ ተጎድቶ ኦሮሞ ዝም አለ” ዓይነት የወያኔን ጠባሳ በማከክ መከፋፈል ለመፍጠር የሚታትሩ ሰዎችን “መ/አ ጌታቸው ሞረዳ ለምን እና የት ሞተ?” ብላችሁ ጠይቋቸው። ወያኔዎች የሰሜን ዕዝን ሲያጠቁ በዋናነት የአማራና ኦሮሞ መኮንኖችን ለይተው አገቷቸው። ከእነዚህ ውስጥ አንዱ መ/አ ጌታቸው ሞረዳ ሲሆን ከትከሻው ላይ ደግሞ ወንድ ልጁ ነበር።

ጌታቸው ትውልዱ ኦሮሞ ነው። አያቱ “የማይጨው ዘማች” ናቸው። አባቱ ደግሞ በካራማራ የተዋደቁ ናቸው። መ/አ ጌታቸው ደግሞ የሰሜን ዕዝ አባል ነበር። ልጅና አባት ከህወሓት እገታ ካመለጡ በኋላ ወደ ወሊሶ በመሄድ አንድዬ ልጁን ለእህቶቹ አደራ ብሎ ወደ ጦር ግንባር ተመለሰ። በመጨረሻም መ/አ ጌታቸው ሞረዳ ልጁን ለእኛ አደራ ሰጥቶ በጋሸና ግንባር ሲዋጋ ተሰዋ። እንደ ጀግናው ገረሱ ዱኪ እንደ አያቱ እና አባቱ ለኢትዮጵያ አንድነት ሲታገል የወሊሶ ልጅ ወሎ ላይ ሞተ።

የሰው ልጅ ከህይወቱ በላይ ሌላ ምንም ሊሰጥ አይችልም። መ/አ ጌታቸው ሞረዳ የኢትዮጵያ ወታደር ነው። በጎሳ እና ብሔር ለሚያስቡት ደግሞ ጌታቸው ኦሮሞ ነው። ይህ የኦሮሞ ልጅ ጋሸና ላይ የሞተው እንደ አያት እና አባቱ ለሀገሩ ኢትዮጵያ ሲል ነው። ሞትና ጀግንነትን በብሔር ለሚያሰሉ ሰዎች ደግሞ “የወሊሶው ኦሮሞ ጌታቸው ሞረዳ ለወሎ አማራ ህዝብ ነፃነት ጋሸና ላይ ተዋድቆ ተሰዋ።

አንድ ልጁን ለእኛ አደራ ሰጥቶ የወደቀው “ቂሪው ትውልድ ከብሔር ጉጠት ከፍ ብሎ በኢትዮጵያ አንድነት እና አብሮነት ያስባል፣ የልጄን አደራ አይበላም” እኛ ተመልሰን የወያኔዎችን ጠባሳ እያከክን ኦሮሞ እና አማራ የሚል ጭቃ ማቡካት ከጀመርን፣ በእርግጥ እኛ ለቁም ነገር የማንበቃ ድኩማኖች ነን። እንደ ጌታቸው ሞረዳ ያሉ ሺህዎች ለአማራ ህዝብ መብት እና ነፃነት ህይወታቸውን ሰጥተዋል። የእነሱን መስዕዋትነት መዘንጋት የመጨረሻ ውርደት ነው።

Via seyum teshome – https://youtu.be/TBksCkN6qsc

Leave a Reply