“ነጻ በወጡ አካባቢዎች በወንጀል ተጠያቂ የሆኑ አካላትን ለፍትሕ ለማቅረብ እየተሰራ ነው” የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎ
ከአሸባሪው ህወሃት ነጻ በወጡ የአማራና አፋር ክልል አካባቢዎች በወንጀል ተጠያቂ የሆኑ አካላትን ለፍትሕ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን መንግሥት አስታወቀ።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ በሰጡት መግለጫ “የተመድ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ከኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጋር ባከናወኑት ምርመራ ውጤትና ምክረ ሃሳብ መሰረት መንግስት የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል” ብለዋል።
መልሶ ግንባታና አገልግሎቶችን ከማስጀምር ጎን ለጎን በወንጀል ተጠያቂ የሆኑ አካላትን ለፍትሕ ለማቅረብ እንቅስቃሴ መጀመሩን አስታውቀዋል።
“በወራራ ተይዘው በነበሩ አካባቢዎች የተፈጸሙ ወንጀሎችን የሚመረምር የወንጀል ምርመራና የማስቀጣት ቡድን በፍትሕ ሚኒስቴር በኩል ተቋቁሞ የምርመራ ስራው ተጀምሯል” ብለዋል።
“የምርመራ ቡድኖቹ በአሸባሪው ትህነግ ተይዘው በነበሩ የአማራና አፋር ክልል አካባቢዎች ከባለፈው ሰኔ ወር ጀምሮ የደረሱትን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችና ወንጀሎችን የሚያሳይ ተጨባጭ መረጃ ለማግኘት በሚያስችል መልኩ ቅኝት ለማድረግ ተሰማርተዋል” ነው ያሉት።
በሽብር ቡድኑ የተፈጸሙ የንጹሃን ዜጎች ሕይወት መጥፋትን፣ የአካል መጉደልን፣ የአስገድዶ መድፈር ወንጀልን፣ ከቤት ንብረት መፈናቀልን፣ የንብረት ውድመትን፣የመንግስታዊ ተቋማት ሰነዶች ውድመት እና ሌሎች እጅግ ዘግናኝ ወንጀሎችን ለማጣራት እነዚህ የመርማሪ ቡድኖች ተሰማርተዋልም ሲሉ ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅት በአፋር ክልል መርማሪ ቡድን መሰማራቱንና በስሩ ሁለት ንዑሳን ቡድኖችን ይዞ ምርመራ እያከናወኑ ይገኛል ያሉት ሚኒስተር ዴኤታዋ “በአማራ ክልል ደግሞ በርካታ ቡድኖች መሰማራታቸውን አንስተው ሸዋሮቢትን ጨምሮ በሰሜን ሸዋ ዞን በአስር ወረዳዎች፣ በደቡብ ወሎ ስምንት ወረዳዎች፣ የኦሮሞ ልዩ ዞን አካባቢዎች፣ በደሴና ኮምቦልቻ፣ ጋሸናን ጨምሮ በሰሜን ወሎ ዞን ምርመራና ምልከታዎችን ለማድረግ ቡድኖቹ ተሰማርተዋል” ብለዋል።
ከነዚህ አካባቢዎች በተጨማሪ ቡድኖቹ ወደ ዋግኽምራ አካባቢዎችና ወደ ወልድያ መሰማራታቸውንም አንስተዋል።
ምርመራዎቹና ምልከታዎቹ የሚካሄዱት በአሸባሪው ትህነግ የተካሄዱትን ጥፋቶች በተጨባጭና በሁለንተናዊ መልኩ ማሳየት በሚችሉበት ደረጃ እንደሆነም አስታውቀዋል። via (አሚኮ)
- ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር ውስጥ ናት፤ በጾሙ ማቅ ለብሰው በንስሃ ችግራቸውን ይፍቱየኢትዮጵያ ታሪክ ቁንጮ እንደሆነች የሚመሰከርላትና እጅግ ውብ ስብዕና ያላቸው አባቶች… Read more: ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር ውስጥ ናት፤ በጾሙ ማቅ ለብሰው በንስሃ ችግራቸውን ይፍቱ
- ሕብረቱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ለዩክሬን ጦር መሳሪያ ግዢ ሊያውል ነውየአውሮፓ ሕብረት በአባል ሀገራቱ እንዳይንቀሳቀሱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ… Read more: ሕብረቱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ለዩክሬን ጦር መሳሪያ ግዢ ሊያውል ነው
- ሳኡዲ የምታስገነባው አዲስ ከተማ – “ኒዮም ሲቲ” (Neom City)በረሃን ወደ ከተማነት የመቀየር ጥበብ ልንለው እንችላለን፡፡ ከ1 ትሪሊየን ዶላር… Read more: ሳኡዲ የምታስገነባው አዲስ ከተማ – “ኒዮም ሲቲ” (Neom City)
- Ethiopia, Somalia dispute won’t transform into turmoil for the Horn of Africadeal between Ethiopia and Somaliland has sent waves of debates… Read more: Ethiopia, Somalia dispute won’t transform into turmoil for the Horn of Africa
- በአማራና ትግራይ ክልል ያሉ የወሰን ይገባኛል ጥያቄ በህዝብ ውሳኔ እንዲቋጭ ስምምነት ተደረሰትህነግ በበላይነት የሚመራው ኢህአዴግ ከፈርሰ በሁዋላ የተነሳውን ጦርነት ተከትሎ የአማራ… Read more: በአማራና ትግራይ ክልል ያሉ የወሰን ይገባኛል ጥያቄ በህዝብ ውሳኔ እንዲቋጭ ስምምነት ተደረሰ
- ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ በምትረከበውን የባህር በር ስፍራ ላይ የሁለቱም አገራት ባለስልጣናት መከሩ“ኢትዮጵያ በክልላዊ ጫና ዉስጥ በመሆኗ የሶማሌላንድን እዉቅና ልትሰርዝ ትችላለች ተባለ”… Read more: ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ በምትረከበውን የባህር በር ስፍራ ላይ የሁለቱም አገራት ባለስልጣናት መከሩ
- የፊልድ ማርሻሉ ሰውኛ ማብራሪያ – “ፖለቲከኞች ባህሪያቸው መመርመር አለበት”More stories አጤ ምኒሊክ እባክዎ ላንዳፍታ ይነሱ!!March 3, 2024 ”… Read more: የፊልድ ማርሻሉ ሰውኛ ማብራሪያ – “ፖለቲከኞች ባህሪያቸው መመርመር አለበት”
- አጤ ምኒሊክ እባክዎ ላንዳፍታ ይነሱ!!ያበደው አንድ ጀግና ታወሰው። አባቱ መቃብር ስር የሚርመጠመጡ ሰዎች ነበሩ።… Read more: አጤ ምኒሊክ እባክዎ ላንዳፍታ ይነሱ!!
- የኢትዮጵያን መጻዒ ዕድል የሚወስኑ “ሁለቱ የውሃ አካላት”ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ተጋሪ የነበረችና አሁንም ቢሆን በቅርብ ርቀት የምትገኝ… Read more: የኢትዮጵያን መጻዒ ዕድል የሚወስኑ “ሁለቱ የውሃ አካላት”