ትሕነግ – “ከባድ መሳሪያ በመተኮስ በአፋር አብአላ ንፁሀን ዜጎች ላይ ጭፍጨፋውን ቀጥሏል” የክልሉ መንግስት

ከአፋር እና ከአማራ ክልል ተቀጥቅጦ የወጣው የህወሃት የሽብር ቡድን የበቀል ርምጃ ለመውሰድ በአፋር አብአላ በከፈተው አዲስ ግንባር በኩል ንፁሀን ዜጎችን ገድሏል፡፡ ይህን ተከትሎ የክልሉ መንግስት መግለጫ አውጥቷል፡፡

በመግለጫው አሸባሪው ህወሃት ይዟቸው ከነበሩት የአፋርና የአማራ ክልል አካባቢዎች ሽንፈትን ተከናንቦ ሲወጣ ሽንፈቱን ለመሸፋፈን በአፋር ክልል ኪልበቲ ረሱ ዞን አብአላ ወረዳ በንፁሀን ላይ ከባድ መሳሪያ በመተኮስ እኩይ ተግባሩን ዳግም በአፋር ህዝብ ላይ አሳይቷል ተብሏል።

ጁንታው በተደጋጋሚ እየተኮሰ ባለው የከባድ መሳሪያ ሴቶች ህፃናት አዛውንቶችን ለሞት፣ ለአካል ጉዳትና ስደት ዳርጓል። በዚህም ቡድኑ ቀንደኛ የአፋር ህዝብ ጠላት መሆኑን በድጋሚ አረጋግጧል።

ቡድኑ ሰላም ፈላጊ በመምሰል በሚዲያ እንዳስተላለፈው አፋርን እና አማራን ለቅቄያለሁ ብሎ ቢዋሽም በአፋር ክልል በኪልበቲ ረሱ ዞን በኩል አዲስ ግንባር በመክፈት ጭፍጨፋውን ቀጥሏል።

የአለምን ህዝብ በማታለል ፕሮፖጋንዳ ቢነዛም እስከዛሬ በወረራቸው አካባቢዎች ከፈፀመው እኩይ ተግባር በባሰ መልኩ አብአላ ከተማን በመድፍ በመደብደብ የሰው ህይወት በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲጠፋና የግለሰቦች እና የህዝብ አገልግሎት መስጫ ቦታዎች ላይ ትልቅ ውድመት አድርሷል።

አሸባሪው ህወሃት በአፋር ህዝብ ላይ ለ 27 አመታት በርካታ ግፎችን ሰርቷል፤ ይህንንም ጠንቅቆ ያውቀዋል፤ የአፋር ህዝብም ጠንቅቆ መዝግቦ ይዞታል ነው ያለው።

ይህ የ27 አመታት የግፍ ጉዞ አልበቃ ያለው የህወሃት የሽብር ቡድን የአፋር ህዘብ አሁን ከዚህ አስከፊ ስርአት ተላቆ ባለበት ሰአት “ለምን ተላቀቀ! የአፋርን መሬት ወደ ታላቋ ትግራይ የምንከልልበት ስራችን ተደናቀፍብን በማለት ፣ በአፋር ህዝብ ላይ ጦርነት በማወጅ በርካታ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ኪሳራን አድርሰዋል ብሏል።

የአፋር ህዝብ ላይ መቼም የማይረሳ በደል ፈፅመዋል፤ በጋሊኮማ ህፃናት፣ ሴቶችና አዛውንቶች ላይ አሸባሪው ህወሀት የፈፀመው እጅግ አረመኔያዊ ዘር ማጥፋትን ጨምሮ በአፋር ህዝብ ላይ ያደረሰው በደል እጅግ ዘግናኝ መሆኑን መግለጫው አንስቷል።

ሰላማዊውን የአፋር ህዝብ የተለያዩ ወረዳዎች ማለትም ከፈንቲ ረሱ ዞን ያሎ፣ ጎሊና፣ አውራ እና ኡዋ ወረዳዎች፣ ከኪልበቲ ረሱ በራህሌና መጋሌ ወረዳዎች፣ ከአውሲ ረሱ ዞን ጭፍራ እና አድ ደአር ወረዳዎች እንዲሁም ከሀሪ ረሱ ዞን ተላለክ፣ ደዌና ሰሙሮቢ ወረዳ እንዲሁም ሀደሌኤላ ወረዳዎች ዘልቆ በመግባት በርካታ ሴቶች፣ ህፃናትንና አዛውንቶችን በአሰቃቂ ሁኔታ በከባድ መሳሪያ በመደበደብ አረመኔያዊ የዘር ጭፍጨፋ በንፁሀን አርብቶ አደሮች ላይ ፈፅሟል ብሏል።

በርካታ የህዝብ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን አውድሟል፣ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን ዘርፏል፣ መስጂዶችንና መድረሳዎችን አውድሟል።

በዚህ ኢ-ሰብአዊ ድርጊትም የአፋር ህዝብ ከሁሉም አካባቢዎች በቁጣ በመነሳት እና በመዝመት አንድ ሆኖ አሸባሪው ህወሃት በወረራባቸው ግንባሮች ሁሉ ብርቱውን የአፋር ክንድ እንዲቀምስ ሆኗል ነው ያለው።

ሰላም ወዳድ መስሎ የአለምን ህዝብ በማታለል ንፁሀንን መጨፍፈጭፍ በየትኛውም መስፈርት ተቀባይነት የሌለው እኩይ ተግባር መሆኑን አስታውቋል ።

አሁንም አሸባሪው ህወሀት በድጋሚ በአብአላ በኩል በከፈተው ጦርነት የምድር ድሮኖች ተገቢውን ምላሽ የሚሰጡ እንደሚሰጡና ከዚህ እብሪትና ኢትዮጵያን ካላፈረስኩ ሞቼ እገኛለሁ እብደቱ ሊታቀብ ይገባል ብሏል የክልሉ መንግስት በመግለጫው ፡፡

የክልሉ መንግስት መግለጫ

ጁንታው በአፋር አብአላ በከፈተው አዲስ ግንባር በኩል ንፁሀን ዜጎች ጨፍጭፏል!

አሸባሪው ህወሀት ይዟቸው ከነበሩት የአፋርና የአማራ ክልል አካባቢዎች ሽንፈትን ተከናንቦ ሲወጣ ሽንፈቱን ለመሸፋፈን በአፋር ክልል ኪልበቲ ረሱ ዞን አብአላ ወረዳ በንፁሀን ላይ ከባድ መሳሪያ በመተኮስ እኩይ ተግባሩን ዳግም በአፋር ህዝብ ላይ አሳይቷል።

ጁንታው በተደጋጋሚ እየተኮሰ ባለው የከባድ መሳሪያ ሴቶች ህፃናት አዛውንቶችን ለሞት፣ ለአካል ጉዳትና ስደት ዳርጓል። በዚህም ቡድኑ ቀንደኛ የአፋር ህዝብ ጠላት መሆኑን በድጋሚ አረጋግጧል። አሸባሪው ህወሀት ወረራ ካካሄደባቸው ከአፋርና አማራ ክልሎች ወጥቼያለሁ ቢልም ዳግም በኪልበቲ ረሱ አብአላ በኩል ጥቃት በመክፈት ንፁሃንን አሸብሯል።

ቡድኑ ሰላም ፈላጊ በመምሰል በሚዲያ እንዳስተላለፈው አፋርን እና አማራን ለቅቄያለሁ ብሎ ቢዋሽም በአፋር ክልል በኪልበቲ ረሱ ዞን በኩል አዲስ ግንባር በመክፈት ጭፍጨፋውን ቀጥሏል። የአለምን ህዝብ በማታለል ፕሮፖጋንዳ ቢነዛም እስከዛሬ በወረራቸው አካባቢዎች ከፈፀመው እኩይ ተግባር በባሰ መልኩ አብአላ ከተማን በመድፍ በመደብደብ የሰው ህይወት በአሰቃቂ ሁኔታ እንዲጠፋና የግለሰቦች እና የህዝብ አገልግሎት መስጫ ቦታዎች ላይ ትልቅ ውድመት አድርሷል።

አሸባሪው ህወሀት በአፋር ህዝብ ላይ ለ 27 አመታት በርካታ ግፎችን ሰርቷል። ይህንንም ጠንቅቆ ያውቀዋል። የአፋር ህዝብም ጠንቅቆ መዝግቦ ይዞታል። ይህ የ27 አመታት የግፍ ጉዞ አልበቃ ያለው ህወሀት የአፋር ህዘብ አሁን ከዚህ አስከፊ ስርአት ተላቆ ባለበት ሰአት “ለምን ተላቀቀ! የአፋርን መሬት ወደ ታላቋ ትግራይ የምንከልልበት ስራችን ተደናቀፍብን በማለት ፣ በአፋር ህዝብ ላይ ጦርነት በማወጅ በርካታ ሰብአዊ እና ቁሳዊ ኪሳራን አድርሰዋል። የአፋር ህዝብ ላይ መቼም የማይረሳ በደል ፈፅመዋል። በ #ጋሊኮማ ህፃናት፣ ሴቶችና አዛውንቶች ላይ አሸባሪው ህወሀት የፈፀመው እጅግ አረመኔያዊ ዘር ማጥፋትን ጨምሮ በአፋር ህዝብ ላይ ያደረሰው በደል እጅግ ዘግናኝ ነው።

ሰላማዊውን የአፋር ህዝብ የተለያዩ ወረዳዎች ማለትም ከ ፈንቲ ረሱ ዞን ያሎ፣ ጎሊና፣ አውራ እና ኡዋ ወረዳዎች፣ ከኪልበቲ ረሱ በራህሌና መጋሌ ወረዳዎች፣ ከአውሲ ረሱ ዞን ጭፍራ እና አድ ደአር ወረዳዎች እንዲሁም ከሀሪ ረሱ ዞን ተላለክ፣ ደዌና ሰሙሮቢ ወረዳ እንዲሁም ሀደሌኤላ ወረዳዎች ዘልቆ በመግባት በርካታ ሴቶች፣ ህፃናትንና አዛውንቶችን በአሰቃቂ ሁኔታ በከባድ መሳሪያ በመደበደብ አረመኔያዊ የዘር ጭፍጨፋ በንፁሀን አርብቶ አደሮች ላይ ፈፅሟል። በርካታ የህዝብ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን አውድሟል፣ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን ዘርፏል፣ መስጂዶችንና መድረሳዎችን አውድሟል።

በዚህ ኢ-ሰብአዊ ድርጊትም የአፋር ህዝብ ከሁሉም አካባቢዎች በቁጣ በመነሳት እና በመዝመት አንድ ሆኖ አሸባሪው ህወሀት በወረራባቸው ግንባሮች ሁሉ ብርቱውን የአፋር ክንድ እንዲቀምስ ሆኗል።

ሰላም ወዳድ መስሎ የአለምን ህዝብ በማታለል ንፁሀንን መጨፍፈጭፍ በየትኛውም መስፈርት ተቀባይነት የሌለው እኩይ ተግባር ነው። አሁንም አሸባሪው ህወሀት በድጋሚ በአብአላ በኩል በከፈተው ጦርነት የምድር ድሮኖች ተገቢውን ምላሽ የሚሰጡ ሲሆን ከዚህ እብሪትና ኢትዮጵያን ካላፈረስኩ ሞቼ እገኛለሁ እብደቱ ሊታቀብ ይገባል!

የአፈር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት

ሰመራ


MORE STORIES

Loading…

Something went wrong. Please refresh the page and/or try again.

Leave a Reply