ተራው የኛ ነው!

"Helen Clark" የቀድሞው ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊና በ"WHO" የአሸባሪው ትህነግ ቃል አቀባይ የሆነው የዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የቅርብ ወዳጅ ነች። እ ኤ አ ከ1999-2008 የኒውዝላንድ 37ኛ ጠ/ሚኒስትር፣ ከ2009-2017 ደግሞ የተባበሩት መንግስታት አድሚኒስትሬተር ነበረች።

ታዲያ የአሸባሪው የትህነግ ሰዎች የቀኝ እጅ የሆነችው “Helen Clark” ዘ ጋርዲያን ላይ ከሌሎች አጋሮቿ ጋር በመሆን…አዲስ አበባን ጨምሮ በሌሎቹም የኢትዮጵያ አካባቢዎች በትግራይ ብሔር ላይ ጄኖሳይድ ሊፈፀም ምልክቶች እየታዩ ነው… በማለት ዘ ጋርዲያንን በውሸት ቅርሻቷ ለቅልቀዋለች(ሊንኩ በኮመንት ሳጥን ውስጥ ይገኛል)። ይህ በነዚህ በአፍቃሪ ትህነግ አንጃዎች የተለቀቀው መጣጥፍ ሙሉ በሙሉ የተዘጋጀው በቴዎድሮስ አድሃኖም መሆኑ ግልፅ ነው። ዘለግ ባለ ዐ/ገር ለዓለም አቀፉ ሕብረተሰብ ቀጭን ትዕዛዝ የሚያስተላልፍ የሚመስለው የመጣጥፉ ርዕስ “The Warning Signs are there for genocide in Ethiopia–the World must act to.prevent it.” የሚል ነው። በእኔ በኩል ለ”ዘ-ጋርዲያን” ይህን ሽፍጥ በተመለከተ ምላሽ ተልኮላቸዋል። የምትችሉ እውነታውን በተመለከተ በ opinion@theguardian.com ኢ-ሜይል አድርጉላቸው። በ”WHO” የአሸባሪው ትህነግ ቃል አቀባይ የሆነው ቴዎድሮስም በእነ “Helen Clark” ስም የቀረበውን የራሱን ፅሁፍ ስላጋራ ገብታችሁ በ twitter@Dr Tedros የበኩላችሁን ምላሽ ስጡ።

ይህን የምናደርገው ያለ ምክንያት አይደለም። በአሁኑ ወቅት አሸባሪው ትህነግ በጦር ሜዳ ያጣውን ድል በዓለም አቀፍ መድረኮች ለማግኘት ተፍ ተፍ እያለ ይገኛል። በጄኖሳይድ ስም የኢትዮጵያን መንግስት በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት (ICJ) ለማቆምና ከተሳከለትም “Humanitarian Referendum” አከናውኖ ትግራይን በእነ አሜሪካ፣ እንግሊዝና ግብፅ አለን ባይነት ለመገንጠል የሞት ሽረት ጥረት እያደረገ ይገኛል። “Humanitarian Referendum” ቀጥሎም “Humanitarian Secession” በስመ ጭቆናና ጂኖሳይድ በተባበሩት መንግስታት ጣልቃ ገብነት ያለ ኢትዮጵያ ፈቃድ በተናጠል ሊወሰን የሚችል የመገንጠል አካሄድ ነው። በእርግጥ ይህን ስልት ተጠቅመው በዓለም አቀፍ ደረጃ የሀገርነት ዕውቅና ያገኙ ሀገራት የሉም…ከባንግላዴሽ በስተቀር። ኮሶቮም ብትሆን እስከአሁን ከፊል የሀገርነት ዕውቅናን ነው ያገኘችው። ለዚህም በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት (ICJ) በኮሶቮ ጉዳይ ዳኞቹ ለሁለት መከፈላቸው በምክንያትነት ይጠቀሳል።

ባለፈው የተባበሩት መንግስታት ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጋር በጣምራ ባደረጉት ጥናት ትህነግ ቀን ከሌት የሚለፍፈውን ጄኖሳይድ በተመለከተ ትግራይ ውስጥ ምንም ማስረጃ እንዳልተገኘ ሪፖርት ማድረጋቸው ይታወሳል። ሪፖርቱ በተለቀቀበት ወቅት የትህነግ ሠራዊት ወደ አዲስ አበባ እየተቃረበ ስለነበር ለይዘቱ ምዕራባውያን ትኩረት አልሰጡም ነበር። ሆኖም ትህነግ አከርካሪው ተመትቶ ወደ ትግራይ መሸምጠጥ ሲጀምር ምዕራባውያን በአውሮፓ ሕብረት አጋፋሪነት የጄኖሳይድ ትሪክቱን እንደ አዲስ ቀስቅሰውታል…ይህ እንቅስቃሴ ትህነግ የራሱን የሽግግር መንግስት አቋቁሞ ለማካሄድ ያሰበው ሕገመንግስታዊ ሪፍረንደም ሲከሽፍበት በሰብዓዊ ሪፍረንደም (Humanitarian Referendum) ለመተካት የሚደረግ መፍጨርጨር ነው። በወታደራዊ ሜዳ ያጡትን በዲፕሎማሲያዊው ለመቀልበስ የሚደረግ ሩጫ ነው። ከትናንት ወዲያ ቢቢሲ ላይ የቀረበው የትህነግ ጄኔራል ፃዲቃን ገ/ትንሳኤ “የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ሂደቶች ከወታደራዊ አካሄዳችን ጋር ሊጣጣሙ አልቻሉም” ያለውን የቤት ሥራ አሁን አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ የአውሮፓ ሕብረትና የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ተረበርበው ሊሰሩለት ደፋ ቀና እያሉለት ነው።

አንድ እውነት ላስቀምጥ፤ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በጦር ሜዳ የኢትዮጵያን ሕልውና ለማስቀጠል የሕይወት መስዋዕትነት ሁሉ ሳይቀር ከፍሏል። አሁን ተረው የኛ ነው፤ መላ ኢትዮጵያዊያን በሀገር ውስጥም ከሀገር ውጪም ያለን ፤ ትህነግ በጦር ሜዳ ያቃተውን በዲፕሎማሲያዊ መድረክ ለማንበርከክ ከተሳካለትም በስመ ጄኖሳይድ ሪፍረንደም ለማከናወን የሚያደርገውን መፍጨርጨር የምናመክንበት ወቅቱ አሁን ነው። ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በሐሩር፣ በውርጭ፣ በደጋት ቁልቁለት ፣ ተራራ በመውጣት በመውረድ የከፈሉትን መስዋዕትነትና ድል እኛ በሶሻል ሚዲያና በ”No.More” እንቅስቃሴ ለመድገም እንደምን ያቅተናል?

Via Getahun Heramo (Nita Color) Fb

Leave a Reply