ባለፈው አርብ የጸደቀው የውሳኔ ሀሳብ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትና አባል አገሮች የሀሠተኛ መረጃ ስርጭትን ለመዋጋት የበለጠ እንዲተጉ እንደሚያደርግ ታምኖበታል።
‘Countering disinformation and promotion and protection of human rights and fundamental freedoms’ የሚል ርዕስ ያለው ይህ የውሳኔ ሀሳብ የሀሠተኛ መረጃ ስርጭት በሰብዐዊ መብቶችና መሰረታዊ በሆኑ ነጻነቶች እንዲሁም ዘላቂ በሆኑ የልማት ግቦች (Sustainable Development Goals) ላይ እያስከተለ ያለውን አሉታዊ ሚና አጽኖት ሰጥቷል።
ሀሰተኛ መረጃ ለግጭት፣ ለመድሎ፣ ለሰብዐዊ ቀውሶች መከሰትና ለአለመረጋጋት ከፍተኛ ሚና እንዳለውም የውሳኔ ሀሳቡ እውቅና ሰጥቷል። በተጨማሪም የውሳኔ ሀሳቡ የማህበራዊ ሚዲያን ጨምሮ በማናቸው የመገናኛ ዘዴዎች የሚሰራጩ ጥላቻንና ግጭትን የሚቀሰቅሱ እንቅስቃሴዎችን አውግዟል።
የውሳኔ ሀሳቡ አገሮች ለሰላምና ለትብብር ጠንቅ የሆነውን የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት አለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ድንጋጌዎችን በማይጻረር መልኩ የመዋጋት ሀላፊነት እንዳለባቸውም ያሳሰበ ሲሆን የሀሠተኛ መረጃ ስርጭትን ለመዋጋት የፖሊሲ እርምጃዎችን እንዲወስዱ ጥሪ አቅርቧል።
የውሳኔ ሀሳቡ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመግታት የብዙ ባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ እንደሚጠይቅ ያሰመረ ሲሆን የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ግልጽነትን በማስፈንና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን የሚያበረታቱ አሰራሮችን በመቀነስ የራሳቸውን በጎ አስተዋጾ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርቧል፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሃፊ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን በመዋጋት ረገድ ቀዳሚ ሚና እንዲጫዎቱም ሀላፊነት ሰጥቷል።
ይህ የውሳኔ ሀሳብ በፓኪስታን አርቃቂነትና በበርካታ አገሮች ድጋፍ የቀረበ ሲሆን ለወራት ውይይት ሲደረግበት ነበር።
EthiopiaCheck Updates
- ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር ውስጥ ናት፤ በጾሙ ማቅ ለብሰው በንስሃ ችግራቸውን ይፍቱየኢትዮጵያ ታሪክ ቁንጮ እንደሆነች የሚመሰከርላትና እጅግ ውብ ስብዕና ያላቸው አባቶች የሚጠቀሱላት ዕድሜ… Read more: ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር ውስጥ ናት፤ በጾሙ ማቅ ለብሰው በንስሃ ችግራቸውን ይፍቱ
- ሕብረቱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ለዩክሬን ጦር መሳሪያ ግዢ ሊያውል ነውየአውሮፓ ሕብረት በአባል ሀገራቱ እንዳይንቀሳቀሱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ዩክሬንን ጦር… Read more: ሕብረቱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ለዩክሬን ጦር መሳሪያ ግዢ ሊያውል ነው
- ሳኡዲ የምታስገነባው አዲስ ከተማ – “ኒዮም ሲቲ” (Neom City)በረሃን ወደ ከተማነት የመቀየር ጥበብ ልንለው እንችላለን፡፡ ከ1 ትሪሊየን ዶላር በላይ የሚፈጅ… Read more: ሳኡዲ የምታስገነባው አዲስ ከተማ – “ኒዮም ሲቲ” (Neom City)
- Ethiopia, Somalia dispute won’t transform into turmoil for the Horn of Africadeal between Ethiopia and Somaliland has sent waves of debates throughout the… Read more: Ethiopia, Somalia dispute won’t transform into turmoil for the Horn of Africa
- በአማራና ትግራይ ክልል ያሉ የወሰን ይገባኛል ጥያቄ በህዝብ ውሳኔ እንዲቋጭ ስምምነት ተደረሰትህነግ በበላይነት የሚመራው ኢህአዴግ ከፈርሰ በሁዋላ የተነሳውን ጦርነት ተከትሎ የአማራ ክልል ”… Read more: በአማራና ትግራይ ክልል ያሉ የወሰን ይገባኛል ጥያቄ በህዝብ ውሳኔ እንዲቋጭ ስምምነት ተደረሰ
- ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ በምትረከበውን የባህር በር ስፍራ ላይ የሁለቱም አገራት ባለስልጣናት መከሩ“ኢትዮጵያ በክልላዊ ጫና ዉስጥ በመሆኗ የሶማሌላንድን እዉቅና ልትሰርዝ ትችላለች ተባለ” ሲል ኢትዮኤፍ… Read more: ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ በምትረከበውን የባህር በር ስፍራ ላይ የሁለቱም አገራት ባለስልጣናት መከሩ
- የፊልድ ማርሻሉ ሰውኛ ማብራሪያ – “ፖለቲከኞች ባህሪያቸው መመርመር አለበት”More stories አጤ ምኒሊክ እባክዎ ላንዳፍታ ይነሱ!!March 3, 2024 ” የሃይማኖት አባቶች… Read more: የፊልድ ማርሻሉ ሰውኛ ማብራሪያ – “ፖለቲከኞች ባህሪያቸው መመርመር አለበት”
- አጤ ምኒሊክ እባክዎ ላንዳፍታ ይነሱ!!ያበደው አንድ ጀግና ታወሰው። አባቱ መቃብር ስር የሚርመጠመጡ ሰዎች ነበሩ። አባቱ የአገር… Read more: አጤ ምኒሊክ እባክዎ ላንዳፍታ ይነሱ!!
- የኢትዮጵያን መጻዒ ዕድል የሚወስኑ “ሁለቱ የውሃ አካላት”ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ተጋሪ የነበረችና አሁንም ቢሆን በቅርብ ርቀት የምትገኝ ወሳኝ ሀገር… Read more: የኢትዮጵያን መጻዒ ዕድል የሚወስኑ “ሁለቱ የውሃ አካላት”