በሰሜን ወሎ ዞን ላልይበላ ከተማ የሚገኘው የቅዱስ ላልይበላ ጠቅላላ ሆስፒታል በከተማዋ ለአራት ወራት ያህል ከርሞ የነበረውን የሽብር ቡድኑን የጭካኔ በትር ተጋፍጦ አገልግሎቱ ሲሰጥ መቆየቱን የሆስፒታሉ ተወካይ ሥራ አስኪያጅ አስታወቁ።
ግፈኛውና አሸባሪው ቡድን የሆስፒታሉን ባለሙያዎች ከመደብደብ አልፎ የሆስፒታሉን ቁሳቁስ በመዝረፍ እና በመሰባበር የክፋቱን ጥግ አሳይቷል ብለዋል።
ሆስፒታሉን በተወካይ ሥራ አስኪያጅነት እየመሩ የሚገኙት ባዮ ሜዲካል ኢንጂነር ሲሳይ ታመነ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳስታወቁት፤ ሆስፒታሉ በአካባቢው ላሉ 300 ሺ የኅብረተሰብ ክፍል አገልግሎት የሚሰጥ ነው። ወራሪው ኃይል ወደ ላልይበላ ከተማ ከገባ ጀምሮ ለአንድ ሁለት ቀን ያህል ሥራ አቋርጦ የነበረ ቢሆንም ወዲያው ኮሚቴ ተዋቅሮ የሽብር ቡድኑን የግፍ በትር በመቋቋም በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ወደሥራ ገብቷል።
በሆስፒታሉ የተቋቋመው ኮሚቴ፣ ለጊዜው የተወሰኑ ዲፓርትመንቶችን በማጠፍ በተለይ ወላጆችንና ስር የሰደደ (ክሮኒክ) ችግር ያለባቸውን ህሙማን አሸባሪው ኃይል የሚያደርሰውን ፈተና በመጋፈጥ ሲያገለግሉ መቆየታውን ተወካይ ሥራ አስኪያጁ አስረድተዋል።
እርሳቸው እንዳሉት፤ የሆስፒታሉ ባለሙያዎች መንገድ ላይ እየተደበደቡም ቢሆን ወራሪው ኃይል ከተማውን ተቆጣጥሮት በቆየባቸው በአራት ወር ውስጥ ወደ 34 እናቶች በኦፕራሲዮን እንዲወልዱ ማድረግ ችለዋል። ከአምስት ሺ በላይ የሆኑ ስር የሰደደ በሽታ ያለባቸው ታማሚዎች ወደ ሆስፒታሉ መጥተው ተስተናግደዋል። በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ውስጥ ስራውን ሳያቋርጥ ቆይቷል።
በወራሪው ኃይል ተደፍረው ከመጡ ሴቶች መካከል ሁለት ታካሚዎች ሲሆኑ፣ አንዷ እመጫት መሆኗን የተናገሩት ተወካዩ፣ በኑሮ ደረጃዋም ዝቅተኛ ከሚባሉት መካከል የምትመደብ መሆኗ ተናግረዋል። ተደፍረው የመጡ ሴቶች በተገቢው መንገድ አገልግሎት እንደተሰጣቸውም አመላክተዋል።
በሆስፒታሉ የተቋቋመው ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ አቤኔዘር ፈንቴ በበኩላቸው፤ ሆስፒታሉ በከባድ ፈተና ውስጥ ሆኖ ሲሰራ የቆየ ነው ብለዋል። በተለይ የሆስፒታሉ የፋርማሲ ባለሙያዎች ይደበደቡ እንደነበርም ተናግረዋል። በዚህ ሁሉ ውስጥ የሆስፒታሉ ባለሙያዎች የወራሪውን ዱላ ሳይፈሩ ተቋቁመው አገልግሎት ሲሰጡ መቆየታቸውን ገልጸዋል።
እንደ ኮሚቴ ሰብሳቢው ገለጻ፤ አንዲት እናት ልትወልድ ወደሆስፒታሉ መጥታ እርሷን ለማዋለድ በሚደረገው ሂደት ለጄኔሬተር ናፍጣ መጠቀም እየተፈለገ ወራሪው ኃይል ግን ናፍጣውን በጉልበት ይወስድ ነበር። ከሆስፒታሉ አውቶቡሶች ውስጥ ሁሉ ናፍጣውን በቱቦ እየሳበ ይጠቀም ነበር።
ሆስፒታሉ ከዚህ በኋላ በርካታ ወረዳዎችን የሚያገለግል እንደመሆኑ የክልል ጤና ቢሮ የተለየ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ሲሉ አቶ አቤኔዘር ጥሪ አስተላልፈዋል። ሆስፒታሉ በመከራ ውስጥ ሆኖ አገልግሎት ሲሰራ በተመቻቸ ሁኔታ አለመሆኑም መታወቅ አለበት ብለዋል።
በሆስፒታሉ የሐብት አፈላላጊ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ መለሰ አሰፋ በበኩላቸው፤ ወራሪው ኃይል ሆስፒታሉን ካምፕ አድርጎ መክረሙን ተናግረዋል። በዚህም የተነሳ ሆስፒታሉ ለአንድ ሁለት ቀን አገልግሎት መስጠት ያቆመ መሆኑን ጠቅሰው፤ ኮሚቴ ተዋቅሮ ከሁለት ቀን በኋላ ወደ ሆስፒታሉ ሲገባ ምንም አይነት መድኃኒት እንዳልነበር ገልጸዋል። በዚህም የተነሳ የላስታ ላልይበላ ተወላጆች አስቸኳይ እርዳታ በማቋቋም መድኃኒት ተገዝቶ ከዞኑ መቄት ከሚባል ወረዳ ከፍላቂት ከተማ መድኃኒት ተገዝቶ በአህያ ተጭኖ መምጣቱን አስታውሰዋል።
በዚህ መሃል ግን ስር የሰደደ በሽታ ያለባቸው ታማሚዎች ይሞቱ እንደነበር አስታውሰዋል። የቅዱስ ላልይበላ ሆስፒታል ክፍት ነው በሚልም ከወልዲያ፣ ከቆቦና ላስታ ድረስ ሰዎች መጥተው ይታከሙ እንደነበር አመልክተዋል።
አቶ መለስ፣ እንዳሉት፣ በወቅቱ ወደ13 የስራ ክፍሎች በወራሪው ኃይል ተሰባብረዋል። ማህበረሰቡን ሲያገለግሉ የነበረው የጥገና ስራ በማካሄድ ነው። በርካታ የሆስፒታሉ እቃዎች በሽብር ቡድኑ አባላት ተሰርቀዋል። በተለይ የህክምና አላቂና ቋሚ እቃዎች ተወስደዋል።
አስቴር ኤልያስ አዲስ ዘመን ታህሳስ 20 ቀን 2014 ዓ.ም
- ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር ውስጥ ናት፤ በጾሙ ማቅ ለብሰው በንስሃ ችግራቸውን ይፍቱየኢትዮጵያ ታሪክ ቁንጮ እንደሆነች የሚመሰከርላትና እጅግ ውብ ስብዕና ያላቸው አባቶች የሚጠቀሱላት ዕድሜ ጠገብቷ የኢትዮጵያ… Read more: ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በከፍተኛ የውስጥ ችግር ውስጥ ናት፤ በጾሙ ማቅ ለብሰው በንስሃ ችግራቸውን ይፍቱ
- ሕብረቱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ለዩክሬን ጦር መሳሪያ ግዢ ሊያውል ነውየአውሮፓ ሕብረት በአባል ሀገራቱ እንዳይንቀሳቀሱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ዩክሬንን ጦር መሳሪያ ለማስታጠቅ… Read more: ሕብረቱ ከታገዱ የሩሲያ ንብረቶች የሚገኘውን ትርፍ ለዩክሬን ጦር መሳሪያ ግዢ ሊያውል ነው
- ሳኡዲ የምታስገነባው አዲስ ከተማ – “ኒዮም ሲቲ” (Neom City)በረሃን ወደ ከተማነት የመቀየር ጥበብ ልንለው እንችላለን፡፡ ከ1 ትሪሊየን ዶላር በላይ የሚፈጅ ውድ ሥራም… Read more: ሳኡዲ የምታስገነባው አዲስ ከተማ – “ኒዮም ሲቲ” (Neom City)
- Ethiopia, Somalia dispute won’t transform into turmoil for the Horn of Africadeal between Ethiopia and Somaliland has sent waves of debates throughout the region, has… Read more: Ethiopia, Somalia dispute won’t transform into turmoil for the Horn of Africa
- በአማራና ትግራይ ክልል ያሉ የወሰን ይገባኛል ጥያቄ በህዝብ ውሳኔ እንዲቋጭ ስምምነት ተደረሰትህነግ በበላይነት የሚመራው ኢህአዴግ ከፈርሰ በሁዋላ የተነሳውን ጦርነት ተከትሎ የአማራ ክልል ” ነጻ ወጡ”… Read more: በአማራና ትግራይ ክልል ያሉ የወሰን ይገባኛል ጥያቄ በህዝብ ውሳኔ እንዲቋጭ ስምምነት ተደረሰ
- ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ በምትረከበውን የባህር በር ስፍራ ላይ የሁለቱም አገራት ባለስልጣናት መከሩ“ኢትዮጵያ በክልላዊ ጫና ዉስጥ በመሆኗ የሶማሌላንድን እዉቅና ልትሰርዝ ትችላለች ተባለ” ሲል ኢትዮኤፍ ኤም ብሉምበርግን… Read more: ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ በምትረከበውን የባህር በር ስፍራ ላይ የሁለቱም አገራት ባለስልጣናት መከሩ
- የፊልድ ማርሻሉ ሰውኛ ማብራሪያ – “ፖለቲከኞች ባህሪያቸው መመርመር አለበት”More stories አጤ ምኒሊክ እባክዎ ላንዳፍታ ይነሱ!!March 3, 2024 ” የሃይማኖት አባቶች ከፓለቲካ ገለልተኛ… Read more: የፊልድ ማርሻሉ ሰውኛ ማብራሪያ – “ፖለቲከኞች ባህሪያቸው መመርመር አለበት”
- አጤ ምኒሊክ እባክዎ ላንዳፍታ ይነሱ!!ያበደው አንድ ጀግና ታወሰው። አባቱ መቃብር ስር የሚርመጠመጡ ሰዎች ነበሩ። አባቱ የአገር ጀግና ነበር።… Read more: አጤ ምኒሊክ እባክዎ ላንዳፍታ ይነሱ!!
- የኢትዮጵያን መጻዒ ዕድል የሚወስኑ “ሁለቱ የውሃ አካላት”ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ተጋሪ የነበረችና አሁንም ቢሆን በቅርብ ርቀት የምትገኝ ወሳኝ ሀገር ናት፡፡ ለዓባይ… Read more: የኢትዮጵያን መጻዒ ዕድል የሚወስኑ “ሁለቱ የውሃ አካላት”
- ” የሃይማኖት አባቶች ከፓለቲካ ገለልተኛ በመሆን ሁሉን በፍቅርና በእኩልነት ማቀራረብ ይገባቸዋል ” አቡነ ማቲያስቅዱስ ፓትርያርኩ ” የሃይማኖት አባቶች ከፓለቲካ ገለልተኛ በመሆን ሁሉን በፍቅርና በእኩልነት ማቀራረብ ይገባቸዋል ”… Read more: ” የሃይማኖት አባቶች ከፓለቲካ ገለልተኛ በመሆን ሁሉን በፍቅርና በእኩልነት ማቀራረብ ይገባቸዋል ” አቡነ ማቲያስ
- Army Ready To Maintain Legacy Of Adwa Victory: Field Marshal BirhanuIn his remarks at the 128th Adwa Victory Day, Chief of the General Staff of… Read more: Army Ready To Maintain Legacy Of Adwa Victory: Field Marshal Birhanu