“ከድል በኋላ ያሉ ድኅረ ድል መዛነፎችን ማረም እና የጋራ መግባባት መፍጠር አስፈላጊ ነው” አቶ ተመሥገን ጥሩነህ
የአማራ ክልል ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች የምክክር መድረክ በባሕር ዳር እየተካሄደ ነው፡፡
የምክክር መድረኩ ዓላማ የክልሉን አመራር ለቀጣይ ተልዕኮ ማዘጋጀት እና ማብቃት ነው ተብሏል፡፡
የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ተመሥገን ጥሩነህ ኢትዮጵያ የገጠማትን የሕልውና ጦርነት በተሟላ ድል የምታጠናቅቀው አፍራሽ አስተሳሰቦች ፈጽመው ሲከስሙ ነው ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ የገጠማት ጦርነት ወታደራዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ትርጉም ያለው ዘርፈ ብዙ ነበር ያሉት አቶ ተመሥገን አንጸባራቂ ድሎች ተመዝግበዋል፤ ድሉም የመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ድል ነው ብለዋል፡፡
አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በአማራ እና አፋር ክልል ወረራ ሲፈጽም የሀገሪቱን መውጫ እና መግቢያ በሮች በመቆጣጠር ኅልውናዋን መገዳደርና ወደሚፈልገው ድርድር መምጣት፣ በሱዳን በኩል መውጫ ኮሪደር ማስከፈት፣ የአማራን ሕዝብ አንገት ማስደፋት እና ኢትዮጵያን ማፍረስ ነበር ያሉት አቶ ተመሥገን የሽብር ቡድኑ በሁሉም ዘርፎች አልተሳካለትም ብለዋል፡፡
ከድል በኋላ ባሉ የድኅረ ድል መዛነፎችን ማረም እና የጋራ መግባባት መፍጠር ያስፈልጋል ያሉት አቶ ተመሥገን በችግሮች ላይ ሰፊ፣ ቀና እና በተግባር የተደገፈ ውይይት ከተደረገ መፍትሔዎቹ ቀላል ናቸው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም በጦርነቱ የደረሰው ጉዳት ቀላል ባለመሆኑ የጋራ ትብብር እና ሕዝባዊ ተሳትፎ ወሳኝ ነው፤ የምክክር መድረኩም በዚህ ላይ ትኩረት ያደርጋል ነው ያሉት፡፡
ክልሉ ለወራት በዘለቀው ወረራ ማኅበራዊ፣ ምጣኔ ሃብታዊ እና ፖለቲካዊ መዛነፎች ተፈጥረዋል ያሉት የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ከዚህ ዘርፈ ብዙ ፈተና በፍጥነት ለመውጣት ወጥ አቋም ያለው፣ በቆራጥነት የሚሠራ እና ሕዝብን የሚያገለግል የአመራር ሥርዓት መዘርጋት ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡
ከችግሮቻችን በፍጥነት ለመውጣት ተከታታይ ምክክር፣ ውይይት እና ስልጠና ያስፈልጋል ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ የጋራ አቋም፣ ወጥ እሳቤ እና ተቀራራቢ አፈፃፀም አሁን ካለው አመራር የሚጠበቅ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በየደረጃው የሚገኘው የክልሉ ሕዝብ ሥራ አስፈፃሚ ከሕዝቡ ጋር መነጋገር፣ የጋራ መግባባት ላይ መድረስ እና በተግባር የተገለጸ ችግር ፈች እርምጃ ያስፈልጋል ያሉት ርእሰ መሥተዳደር ዶክተር ይልቃል ይህንን ለማድረግ ደግሞ በቂ ጊዜ ስለማይኖር ቀን እና ሌሊት ያለረፍት መሥራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
ርእሰ መሥተዳድሩ መሰረታዊ የሆኑ የክልሉ ሕዝብ ጥያቄዎች እንዲመለሱ ቁርጠኛ አቋም መውሰድ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡ የምክክር መድረኩ ተሳታፊዎች የቀጣይ ተልዕኮ በዚህ “የጊዜ የለንም መንፈስ” የተቃኘ ሆኖ እንዲወጣም አሳስበዋል፡፡
በምክክር መድረኩ ከፌደራል እስከ ወረዳ ያሉ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ተሳታፊ ናቸው፡፡ ምክክሩም ለሦስት ተከታታይ ቀናት እንደሚቀጥልም ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ዘጋቢ፡- ታዘብ አራጋው – (አሚኮ)
- “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”“የሚሊሻ ኀይሉን በተመለከተ የሚዘዋወረው መረጃ ፍጹም መሠረተ ቢስ ነው” ሲሉ ኮሎኔል ግርማ ገሰሰ… Read more: “የአማራ ክልል ሚሊሻዎች ትጥቅ ይፍቱ በሚል የሚሰራጩ መረጃዎች ‘ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው’ ከሚል ቅዠት የተወለደ ቅጥፈት ነው”
- “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን“የትግራይ ተወላጆች ትህነግ ለፈጸመው ወረራ፣ ዘረፋ፣ ማፈናቀልና የግድያ ተግባራት የተቀናጀ የፖለቲካና የሚዲያ ድጋፍ… Read more: “የህዝባችንን ድምጽ የሚቀማና የሚያፍን የ’አማራ ስብስብ’ ለአማራ ክልል ተግዳሮት ሆኗል… ትህነግ ዘርፎ እያጋጋዘ ነው” አብን
- “ትህነግ ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው ” የዜናው ሰም፣ ወርቅና የትህነግ ‘ ሃሰት ነው’ ማስተባበያለአንድ ቀን ከጮኸና አየሩን ሁሉ ከተቆጣጠረ በሁዋላ ውሃ የተቸለሰበት “ሕወሓት ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር… Read more: “ትህነግ ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው ” የዜናው ሰም፣ ወርቅና የትህነግ ‘ ሃሰት ነው’ ማስተባበያ
- National Dialogue, Transitional Justice And Rehabilitation Process Pillars of Lasting Peace, Prosperity: CouncilThe Ethiopian National Security Council has issued a statement on latest developments in… Read more: National Dialogue, Transitional Justice And Rehabilitation Process Pillars of Lasting Peace, Prosperity: Council
- ቀሲስ በላይ በተጠረጠሩበት ወንጀል ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀረቡ ዋስትና ተከለከሉየፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት የቀሲስ በላይ መኮንንን ጨምሮ… Read more: ቀሲስ በላይ በተጠረጠሩበት ወንጀል ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀረቡ ዋስትና ተከለከሉ