በራያ ቆቦ የሮቢት 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት 19 የተናጠልና የጅምላ መቃብሮች ተገኙ

በራያ ቆቦ ወረዳ በሚገኘው የሮቢት 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት 19 የተናጠልና የጅምላ መቃብሮች መገኘታቸውን ተገለጸ፡፡

የወረዳው ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ መንገሻ በላይነጋ እንደገለጹት በሮቢት 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ከተገኙት 19 መቃብሮች 3ቱ በእያንዳንዳቸው እስከ 30 ሰዎች የተቀበሩባቸው የጅምላ መቃብሮች ናቸው።

የአሸባሪው ትሕነግ ወራሪው ቡድን የወረዳውን ትምህርት ፅህፈት ቤት እና በወረዳው የሚገኙ 7 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ 129 ትምህርት ቤቶችን በመውረር ዘረፋ መፈጸሙንና ንብረቶች ማውደሙን ኃላፊው ተናግረዋል።

የሽብር ቡድኑ ከዘረፋቸውና ካወደማቸው ንብረቶችና ቁሳቁስ መካከልም የቤተ ሙከራ ቁሳቁስ፣ ኮምፒውተሮች፣ ፕላዝማዎች፣ የተማሪ ሰነዶችና ሌሎችም የትምህርት ቤቱ ንብረቶች ይገኙበታል።

የሮቢት 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የጥበቃ ሰራተኞች አቶ ይመር አየለና ዝናቡ ሰማው ወራሪው ቡድን ትምህርት ቤቱን የመቃብር ስፍራ እንዳደረገው መናገራቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የሮቢት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ባለፈው ዓመት መጨረሻ ከ1ሺሕ 800 በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ ሲያስተምር እንደነበርም ተገልጿል። via – walata


Related posts:

«ሕወሓት ጦርነትን እንደ አምልኮ የሚቆጥር ቡድን ነው» – ፕሮፌሰር ሀረገወይን አሰፋ
«በሕገወጦች ላይ ያለ ምኅረት እርምጃ መውሰድ አለብን፤ ይህ የመንግሥት ተግባር ነው» የአማራ ክልል
125 አዳዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ
«በአገሩ መከላከያ ላይ አፉን የሚከፍት ሕዝብ የለም፤ መንግስትም አይታገስም» ክብር ለመከላከያ ሰራዊት!!
በኢትዮጵያና ቱርክ መካከል የተደረገውን የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት ምክር ቤቱ አጸደቀ
የሞት ፍርደኛው የ25 ዓመታት ሰቆቃ! ከመሬት በታች የታፈኑት አባት
«ኢትዮዽያን ማስቀጠል ከሚፈልጉት ጎን በመሆናችን የሚከፋ ከአለ እርሱ መፍረሷን የሚናፍቅ ብቻ ነው!»
ደብዳቤ ለኢትዮጵያ - ከቢልለኔ ስዩም
የዓለም ባንክ የ300 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ፈረመ
"እናቴ ፍጹም እስር ቤት እንድትገባ አልፈግም" ብሎ እግሩን ያጣው ወጣት ምስክርነት ለሮይተርስ
"አልዘምትም" ወይም "ከጠላት ጎን እሰለፋለሁ" ማለት ሲቻል ማውሰብሰብና ማድበስበስ አይገባም!
አብዱላሂ ፋርማጆ ለአዲሱን ፕሬዝዳንት «ሁሉም ወገኖቼ እንዲደግፉህና እንዲጸልዩልህም እጠይቃለሁ»
መንግስ የጸጥታ ሃይሎች ለየትኛውም ዓይነት ትንኮሳ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ማድረጉን አስታወቀ
በትግራይ 5.2 ሚሊዮን ሕዝብ ዕርዳታ እየደረሰ ነው፤ ከሺህ በላይ የጭነት መኪኖች ታግተዋል፤ 76 ቢሊዮን ብር ወደ ትግራይ ተልኳል
የደህንነት ጥናት አዲሱ ምዕራፍ - ጂኦስፓሻል ኢንተለጀንስ

Leave a Reply