የማይካድራ ጭፍጨፋ በትግራይ ሚሊሺያና ልዩ ሃይል ሽፋን መፈጸሙ ተረጋገጠ፤ የጦር ወንጀል ሆነ

ባለፈው ዓመት በማይካድራ ከተማ እና አካባቢው የተፈጸመው ወንጀል በሰብዓዊነት ላይ የተቃጣ እና የጦር ወንጀል መፈፀሙን ሊያሟሉ የሚችሉ ሁኔታዎች መኖራቸውን ባደረገው የምርመራ ግኝቱ እንደደረሰበት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ገለፀ።
ኢሰመጉ ጥቅምት 30 2013 ዓ. ም በማይካድራ በግልጽ ብሔርን መሠረት አድርጎ ተፈጽሟል ባለው ወንጀል ከ1100 በላይ ሰዎች በጭካኔ ተገድለዋል፣ ከ122 በላይ ሰዎች የተለያየ መጠን ያለው የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፣ ከ20 በላይ ሴቶች የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተፈጽሞባቸዋል።
በምርመራ ግኝቱ ከተገደሉት ሰዎች መካከል የ176ቱ ስም ፣ ጾታ፣ እድሜ ፣ የትውልድ ቦታ እና ብሔር ተዘርዝሯል። በማይካድራ የተፈፀመው ድርጊት ዓለም አቀፍ ሕጎችን የጣሰ የጭካኔ ወንጀል መሆኑንም ኢሰመጉ በግኝት ዘገባው ጠቅሷል።
ጥቃቱ ሣምሪ ከተባለ ሰፈር እና ሌሎች ቀብሌዎች በሄዱ በቡድን የተደራጁ የትግራይ ተወላጆች መፈፀሙንና የድርጊቱ ፈጻሚዎች በትግራይ ልዩ ኃይል እና ሚሊሺያ አባላት በጦር መሣሪያ የታገዘ ሽፋን እና ድጋፍ ይደረግላቸው እንደነበርም ኢሰመጉ አረጋግጫለሁ ብሏል። via DW
Related posts:
«ድርድር አያዋጣንም ሀገሪቷን ማተራመስ አለብን» ታዋቂው ግብጻዊ ፓለቲከኛ
ስምንት የነዳጅ ቦቴዎች ተወረሱ
ሱዳን ትሪቡን ያሰራጨው አሳሳች ምስል!
ከትግራይ የመጡ የሽብር ቡድኑ አባላት በቁጥጥር ሥር ዋሉ
የጌታቸው አሰፋ ፍርድ
“ጠላት አርፎ እንደማይተኛ ታውቆ ለየትኛውም ተጋድሎ ራስን ማዘጋጀት” አማራ ክልል
የፓትሪያርኩ የውጭ ጉዞና - "ተቀነባብሯል" የሚባለው ሴራ እያነጋገረ ነው
በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ መልዕከተኛ ራሳቸውን አሰናበቱ፤ ለአራተኛ ጊዜ የተሰማው ስንብት አነጋግሪ ሆኗል