ትህነግ የመሰረተው ‘አዲሱ ኢህአዴግ’ በዙም ስብሰባ የሰጠው መረጃ ሚስጢር “ለግብጽ ሲባል የህዳሴ ግድብ መቆም አለበት”

በስብሰባው ማንም ተወካይ ድርጅት ወክሎ አይሳተፍም። አጀንዳ ማስያዝ አልችልም። የቀረበለትን ሰምቶና የቤት ስራውን ምን ያህል እንደሰራ ከማናገር ውጭ ሌላ ሚና የለውም። ይህ አሰራር ልክ ቀደም ሲል ” አጋር ፓርቲ” እንደሚባሉት ዓይነት እንደሆነ ተገልጿል። መረጃውን የሰጡን ” አዲሱ የዙም አጋር ነን” ሲሉ የስብሰባው ተካፋዮች ራሳቸውን እንደገለጹላቸው አመልክተዋል።
  • በፕሮፌሰር ሕዝቅኤል አቅራቢነት አቶ ፌይሰል ሮቤል ወ/ሮ ፊልሰን መንግስትን በጄኖሳይድ እንዲከሱና በታላላቅ ሚዲያዎች ምስክረነት እንዲሰጡ የማግባባት ስራ እንዲሰሩ ሃላፊነቱን ወስደዋል
  • ሱዳንን እያተራመሰች ያለቸው ግብጽ ናት
  • ሸኔ ሁርሶ፣ አሰቦት፣ ኤረርን ተቆጣጥሯል – የተረጋገጠ ሃሰት ነው
  • በወልቃይት አካባቢ ኮሪዶር ለማስከፈት ውጊያ እየተካሄደ ነው
  • ስንቅና ትጥቅ በሚገባ እየተደራጀ ነው
  • መንግስትን ለማስገደድ የሴኩሪቲ ካውንስል አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ ስራ እየተሰራ ነው

በምሥራቅ ወለጋ ዞን 312 የአሸባሪው ሸኔ አባላት እጅ ሰጡ – ETHIO12 – ኢትዮ12

 ከአርሶ አደሩ የተዘረፈ 949 ኩንታል እህል፣ ከ600 በላይ ከብቶች እና ከ6 ሺሕ በላይ ፍራሾች መያዛቸውን 


እንደሚነሱ አስቀድመው በማወቃቸው ምክንያት ቀድመው መልቀቂያ እንዳስገቡ የተነገረባቸው የቀድሞዋ የሴቶች፣ህጻናትና ወጣቶች ሚኒስትር ወ/ሮ ፊልሰን አብዱላሂ የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ የጦር ወንጀል እንደፈጸመ ምስክር ሆነው በታዋቂ ሚዲያዎች እንዲቀርቡ ስለተመቻቸ እሳቸውን የማሳመን ስራ እንዲሰራ በፕሮፌሰር ሕዝቅኤል ጋቢሳ ያቀረቡት እቅድ ተቀባይነት አገኘ። የትህነግ ወኪል አቶ ዮሃንስ አርአያ ለግብጽ ሲባል የህዳሴው ግድብ ግንባታ መቆም አለበት። ኢትዮጵያ ብዙ ውሃ አላት ብለዋል።

የኢትዮጵያ የሴቶች ሕፃናትና ወጣቶች ምኒስትር ፊልሰን አብዱላሒ የሥልጣን መልቀቂያ ደብዳቤ — Iltimos xabar  YeneTube
ወ/ሮ ፊልስን – ዛሬ ኪንያ ናቸው

ዋና አለቃው አምባሳደር ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ ሲሆኑ እሳቸው በዙም ስብሰባ አይሳተፉም። መመሪያና አጀንዳ ለፕሮፌሰር ሕዝቅኤልና አቶ ዮሃንስ እርዓያ በዝግ ስብሰባ ከተሰጠ በሁዋል ሕዝቅኤል ስብሰባውን እንደ መሪ ሆነው ያስኬዳሉ። የእሳቸው እንቅስቃሴና አኳኋን በመገምገም ” ምሁሩ ዱላ” ሲሉ አዲስ ስም አውጥተዋላቸዋል።

እንግዲህ በዚህ መሰሉ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ትህነግ አስቸኳይ ጉዳይ ከሌለ ቢያንስ በሁለት ሳምንት አንድ ጊዜ በዙም የሚሰበስባቸው “የብሄር ብሄረሰቦች ጥምረት” አዲሱ ኢህአዴግ ውይይት ላይ ነው ይህ የተወሰነው። በርካታ ጉዳዮች የተነሱት።

በስብሰባው ከሚካፈሉ ወገኖች ጋር በድርጅት ግንኙነት ካላቸው ወገኖች የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ይህ የተወሰነው በስብሰባው ላይ የሶማሌ ተወላጅ የሆኑት ፌይሰል ሮቤል በመጨረሻ ስብሰባ የወሰዱትን ታስክ ምን ያህል እንደተገበሩ ተጠይቀው ካብራሩ በሁዋላ ነው።

See also  አሜሪካ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን ትብብር አጠናክራ ለመቀጠል ቁርጠኛ መሆኗን ጆ ባይደን ገለጹ

ፌይሰል የተሰጣቸውን የቤት ስራ ሲዘረዘሩ የቀድሞው የሶማሌ ክልል መሪ የነበሩት አብዲ ኢሌ ቡድን ከቱርክና ኬንያ ሆነው ያቋቋሙት ካራ መረዳ የተሰኘ የሶማሊኛ ቋንቋ ቲቪ የፕሮፓጋንዳ ስራ አጠናክሮ እንዲሰራ መደረጉን በስኬት አንስተዋል። አያይዘውም በዋሺንግቶን ኤግዛማይንር ድረ ገጽ መንግስትን ወቅሰውና ወንጅለው ቃለ ምልልስ ያደረጉትን የቀድሞ ሚኒስትር ወ/ሮ ፈሊሰን አብዱላሂን ተሳትፎ አጉልተዋል።ሰብሳቢው ፕሮፌሰር ሕዝቅኤል የሰሙትን አድነቀው አቶ ፊይሰል ወ/ሮ ፍሊሰንን አግባብተው መንግስትን በጄኖሳይድ በመወንጀል በታዋቂ ሚዲያዎች በተከታታይ ምስክር እንዲሆኑ የማግባባት ስራ እንዲሰራ መመሪያ ሰጥተዋል። ሚዲያዎቹ የተዘጋጁ በመሆናቸው እሳቸውን የማሳመኑ ስራ በአስቸኳይ መሰራት እንዳለበት ተናግረዋል። አቶ ፌይሰልም የማግባባቱን ስራ እንደሚሰሩ አመልክተዋል። ወ/ሮ ፍሊሰን ኬንያ እንደሚገኙም ተነስቷል። ይሁን እንጂ በምን አይነት የፖለቲካ ተሳትፎ ኬንያ መቀመጥ እንዳስፈለጋቸው የታወቀ ነገር የለም። መረጃውን የሰጡት ወገኖች ፍሊሰን የግል ጉዳያቸውን ከአገር ጋር በማቀላቀል በሶማሌ ክልል የተፈጸመውን ግፍ ረስተው ዳግም ያንን ቡድን ለመመለስ በሚደረግ ትግል ውስጥ ከመሳታፋቸው በፊት እንዲያስቡበት መክረዋል።

ሕዝቅኤል ገቢሳ አያይዘውም የሸኔ ሃይል ሁርሶ፣ አሰቦትና ኤረርን መቆጣጠሩን አስታውቀው ድሉን የማስፋት ዘመቻ እየተካሄደ መሆኑንን አመልክተዋል። ከዚህኛው ስብሰባ በፊት የትህነግ ሰዎች ሸኔን ተሸክመው መሄድ እንደሰለቻቸው፣ አዲስ አበባ ይገባሉ ተብሎ ሲጠበቁ አንድ ቀበሌ እንኳን መቆጣጠር አለመቻላቸውን በማንሳት ወቅሰዋቸው እንደነበር እነዚህኑ የመረጃ ምንጮች ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል።

አርብ ዕለት የተጠቀሱትን ከተሞች መቆጣጠራቸውን ሕዝቅኤል መናገራቸውን ተከትሎ የመረጃ ሰዎቹ መኢሶ ስልክ ደውለው ለማጣራት ሙከራ ያደረጉ ሲሆን ያገኙት መልስ የሚያዝናና ሆኖ እንዳገኙት አመልክተዋል። “ከአሰቦት ወደ ሁርሶና ኤረር ሲሄዱ መኢሶን ዘለዋት ነው ወይስ ቀላቀለዋት? ” የሚል ምላሽ ማግነታቸውን አመልክተዋል። በተጨማሪም በሁርሶ በአስር ሺህ የሚቆጠር ስልጣኝ ወታደሮችና ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚደረግ እየታወቀ እንዲህ መሰል ሪፖርት መቅረቡ አስገርሟል። መረጃውን ያጋሯቸው የዙም ተሰብሳቢ አካባቢውን በደንብ ስለሚያውቁ ህዝቅኤል ይህን ሲሉ ፊታቸውን ደብቀው ይስቁ እንደነበር ገልጸውላቸዋል።

See also  ሶስት የውጭ ድርጅቶች ከተቋቋሙለት አላማ ውጭ በመንቀሳቀሳቸው የመጨረሻ ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ ለሶስት ወራት ታገዱ

በዚህ ስብሰባ ግብጽ ተነስታለች። የትህነግ ተወካይ እንዳሉት ግብጽ ድጋፍ ታደርጋለች። አሁን ላይ ግብጽ እያደረገች ካለው ድጋፍ አንጻር የህዳሴውን ግድብ የማስቆም ዘመቻው የግድ አስፈላጊ ነው። በሱዳን የወታደራዊ ክንፉን ግብጽ እንደምትደግፍና አሁን እየሆነ ያለውን የመንግስት ግልበጣ የምትመራዋም እሷ መሆኗን፣ ሃላብን ሙሉ በሙሉ የመትቆጣጠረው ግብጽ የቀድሞ የሱዳን ፕሬዚዳንት ሃይሎችንም እያስታጠቀች እንደሆነና ይህ ለትህነግ መራሹ ትግል እጅግ ጥሩ ግብአት እንደሆነ ተመልክቷል። በዝርዝር አልተገለጸም እንጂ የመሳሪያ ድጋፍ መገኘቱም ተመልክቷል።

ከዚህ ጋር አያይዘው ነዋሪነታቸው በካናዳ የሆነው የትህነጉ ተወካይ በወልቃይት በኩል ሰፊ ጦርነት እየተካሄደ መሆኑንና ኮሪዶር የማስከፈቱ ዘመቻ በመላክም ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑንን ገልጸዋል። ኦቻ ትናንት ይፋ ባደረገው ሪፖርት በአፋር በኩል ጦርነት ስላለና እርዳታ ማስተላለፍ ስለማይቻል የሱዳን ኮሪዶር እንዲከፈት እንዲደረግ መጠየቁ ከዚህ ማብራሪያ ጋር የሚስማማ ሆኗል። ትህነግ በአፋር አባላ በኩል ጦርነት የከፈተው ሆን ብሎ የሱዳን ኮሪዶር እንዲከፈትለት በወዳጆቹ አገራት አምካይነት ጫና ለማድረግ እንደሆነ አስቀድሞ መገለጹ ይታወሳል።


ሸባሪው ሕወሓት ጅምላ ጭፍጨፋ ማካሄዱን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ አስታወቀ

… ህጻናትንና ሴቶችን ሳይለይ በጅምላ ዘግናኝ የሆነ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸሙንና በንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመት ማድረሱን 


በአድ አርቃይ በኩል ያለው መንግስት እየገፋ መሆኑን፣ በሱዳን የሚደገፉ የትህነግና የቤኒሻንጉል ሃይሎች በሮኬትና በካባድ መሳሪያ ሽፋን እየተሰጣቸው በተደጋጋሚ ጥሰው ለመግባት ያደረጉት ሙከራ መክሸፉን፣ ትህነግም ባስቸኳት ይህን ኮሪዶር ማስከፈት ካልቻለ በሁለትና ሶስት ወር ጊዜ ውስጥ የውስጥ ተቃውሞና የህዝብ ስደት በማዕበል ደረጃ ሊያጋጥመው እንደሚችል መገምገሙን ባለፈው ሳምንት ማስነበባችን ያታወሳል።

ለጦርነቱ በቂ ስንቅና ትጥቅ መኖሩን የትህነጉ ወኪል አቶ ዮሃንስ አርአያ አስታወቀዋል። ፕሮፌሰር ሕዝቅኤል ገቢሳም ሸኔ ከግብጽ ድጋፍ ማግነቱን በተዘዋዋሪ መንገድ ገልጸዋል።

የሰላም ንግግሩን አስመልክቶ የአማራ ተስፋፊና የኤርትራ ጽንፈኛ መንግስት እንቅፋት መሆናቸውን በማጉላት በቀጣይ በመንግስት ውስጥ ልዩነትንና የርስ በርስ ግጭት በማስነሳት እንዲሰነጠቁ ማድረግ በታክስ ደረጃ ለተሰብሳቢዎች የቤት ስራ ተሰጥቷል። በዚህም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድርድር ለማድረግ፣ ኮሪዶር እንዲከፈትና ሰላም እንዲሰፍን ፋልጎት እንዳላቸው፣ በውስጥ ለውስጥ ንግግር በድብቅ መጀመራቸው ጎልቶ በወዳጅ ሚዲያዎች እንዲነገር፣ የህን ልዩነት በማስፋት በአማራ ክልል መንግስታ፣ በኢሳያስና በመንግስት በኩል መከፋፈል እንዲፈጠር በጥብቅ እንዲሰራ መመሪያ ወርዷል።

See also  ሃገራዊ ምክክሩ - ሃገሪቱ ካለችበት ዉጥረት ተላቃ ወደ አዲስ ምዕራፍ እንድትሸጋገር ..

በስብሰባው ማንም ተወካይ ድርጅት ወክሎ አይሳተፍም። አጀንዳ ማስያዝ አልችልም። የቀረበለትን ሰምቶና የቤት ስራውን ምን ያህል እንደሰራ ከማናገር ውጭ ሌላ ሚና የለውም። ይህ አሰራር ልክ ቀደም ሲል ” አጋር ፓርቲ” እንደሚባሉት ዓይነት እንደሆነ ተገልጿል። መረጃውን የሰጡን ” አዲሱ የዙም አጋር ነን” ሲሉ የስብሰባው ተካፋዮች ራሳቸውን እንደገለጹላቸው አመልክተዋል።

“ለምን በድርጅት ደረጃ መወከል አይቻልም” በሚል ማብራሪያ ጠይቀን ዘጠኝ ድርጅቶችን ሰብስበው ያዋቀሩት ህብረት በመክሸፉ የተነሳ እንደሆነ ገልጸዋል። ” ነጩ ትህነግ” የሚባለው አሌክስ ዱዋል “አዲስ አበባ ዙሪያ ደርሰዋል” በሚል ሰፊ የማዋከብና የማተራመስ መረጃዎች እየተካሄደ ባለበትና ዘጠኝ አባላት ያሉት ህብረት በአሜሪካ እውቅና ይፋ ሲሆን ተቃውሞ ነበር። በማይታመን ደረጃ ” እነዚህ ሰዎች 1991ን መድገም ይፈልጋሉ። ይህ አይሰራም” ማለቱን በማስታወሰ ህብረቱ እንደ ሟሟ፣ ቢኖርም ሊሰራ እንደማይችል አስታውቀዋል። በዚህም ሳቢያ ነው በስብሰባው በድርጅት ደረጃ የሚወከሉ የሌሉት። ፊልትስማንም ” ሰዎቹ 1991 ላይ ተችክለውላ እንደማይሆን ነግረናቸዋል፤ ህዝብም እንደማይወዳቸው እናውቃለን” ማለታቸው አይዘነጋም።

ሌላው መረጃ አቅራቢዎቹ ያስታወቁት ሙስሊም ኦሮሞዎች ይህን ስብሰባ እንደምያደግፉት እነ ሕዝቅኤል ሲናገሩ መስማታቸውን ነው። ምክንያቱ ደግሞ ትህነግ በኦሮሞ ላይ የፈጸመው ወንጀልና ግፍ ዳግም አብረውት እንዲሰሩ ቀርቶ አብረው ተቀምጠው ለመንጋገር እንኳን የሚያስችል ባለመሆኑ ነው። የዚህን ዝርዝር በቀጣይ እናቀርባለን።

በስብሰባው ላይ ጃዋር ይመራው በነበረው በኦኤምኤን ቲቪ በቋሚነት ይሳተፉ የነበሩትን እንድ ጸጋዬ አራርሳ፣ ኢተና የመሳሰሉት የሚገኙ ሲሆን ዶክተር አወል አሎና እሳቸው ዙሪያ ያሉ ጥያቄውን ውድቅ ማድረጋቸው ታውቋል። ትህነግ ይህን ሁሉ የሚያደረገው መንግስት ወደ እርቅ እንዲመጣ ለማስገደደ መሆኑ እየታወቀ እነ ፕሮፌሰር ሕዝቅኤል ስለምን የዚህ ተግባር መጠቀሚያ መሆን እንደፈለጉ አብዛኞች እንደማይገባቸው በተደጋጋሚ እየጠየቁ ነው።

በመንግስት በኩል በወልቃይት በኩል ያለውን አዲሱን የትህነግ ዕቅድ በመረዳት ከወትሮው በበለጠ ዝግጅት መኖሩን፣ ሕዝቡ የተዘጋጀና እራሱን ወታደር አድርጎ እየተበቀ እንደሆነ በተደጋጋሚ የአማራ ቲቪና የመንግስት መረጃ ተቋማት በየዕለቱ ዘግባና የማነቃቂያ ፕሮግራም እያዘጋጁ ነው።


Leave a Reply