61 ጤና ጣቢያዎችና 18 ሆስፒታሎችን አገልግሎት ለማስጀመር በትኩረት እየተሰራ ነው

በአሸባሪው ህወሓት የወደሙ 61 ጤና ጣቢያዎችና 18 ሆስፒታሎችን አገልግሎት ለማስጀመር በትኩረት እየተሰራ ነው

  • በተደረገላቸው ድጋፍ እስካሁን 13 ሆስፒታሎች መደበኛ የጤና አገልግሎቶች መስጠት ጀምረዋል፣

በአሸባሪው ህወሓት የወደሙ የጤና ተቋማትን አገልግሎት ወደነበረበት ለመመለስ በፌደራል ሆስፒታሎች ፣ በአዲስ አበባ ጤና ቢሮና በስሩ በሚገኙ ሆስፒታሎች በተደረገላቸው ድጋፍ እስካሁን 13 ሆስፒታሎች መደበኛ የጤና አገልግሎቶች መስጠት ጀምረዋል።

ሁሉም የድንገተኛ ጊዜ እንክብካቤ፣ የእናቶችና ህፃናት ጤና አገልግሎት፣ የፅኑ ህክምና እንክብካቤ አገልግሎት፣የቀዶ ጥገና አገልግሎት፣ የተመላላሽ ህክምና አገልግሎትና አስፈላጊ የላብራቶሪ አገልግሎቶች እየሰጡ ይገኛሉ፡፡

ትስስር በመፍጠር እስካሁን በተስራው ስራ ጥሩ ውጤት እየተገኘ ነው። አዳዲሶችንም በማስተሳስር የድርሻቸውን እንዲወጡ እየተደረገ ነው።

የጤና ተቋማት አገልግሎት ወደነበረበት ለመመለስ ጤና ሚኒስቴር ከክልሎች፣ ከፌዴራልና ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታሎች ጋር በመተባበር የተጎዱ ተቋማት ጋር ጥምረት በመፍጠር መደገፍናና አገልግሎት ማስጀመር ነው።

በጥፋት ቡድን ምክንያት የወደሙ ጤና ተቋማትን ወደነበሩበት ለመመለስና የጤና አገልግሎት ለማስጀመር የክልል ጤና ቢሮዎችና የዩንቨርስቲ ሆስፒታሎችን ከወደሙ ጤና ተቋማት ጋር በማስተሳሰር ድጋፍ እንዲያደርጉ 61 ጤና ጣቢያዎችና 18 ሆስፒታሎች ላይ ሰፊ ስራ ተጀምሯል።

በዚህ መሰረት ፤
የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ክልል ጤና ቢሮ በደቡብ ወሎ ዞን የሚገኙ 25 ጤና ጣቢያዎች፤
የጋምቤላ ክልል ጤና ቢሮ በሰሜን ወሎ ዞን የሚገኙ 3 ጤና ጣቢያዎች፣
የሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ በሰሜን ሸዋ ዞን ለሚገኙ 10 ጤና ጣቢያዎች፣
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በደቡብ ወሎ ዞን 7 ጤና ጣቢያዎች፣በሰሜን ወሎ 4 ጤና ጣቢያዎች፤ በአፋር ክልል 6 ጤና ጣቢያዎች
የድሬድዋ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ በአፋር ክልል የሚገኙ 3 ጤና ጣቢያዎች፣
የሀረሪ ክልል ጤና ቢሮ በአፋር ክልል የሚገኙ 3 ጤና ጣቢያዎች ይዘዋል፡፡

በተጨማሪም
የዩኒቨርስቲ ሆስፒታሎች ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ➖ ወልድያ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን ፤
ህይወት ፋና ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ➖ አቀስታ ሆስፒታልን ፤
ሀዋሳ ዩንቨርስቲ ሆስፒታል ➖ መርሳ የመጀመርያ ሆስፒታልን፣
ዲላ ዩንቨርስቲ ሆስፒታል ➖ ተፈራ ሀይሉ ሆስፒታልን(ሰቆጣ)፣
ወራቤ ዩንቨርስቲ ሆስፒታል ➖ አጣየ ሆስፒታልን፤
ጅግጅጋ ዩንቨርስቲ ሆስፒታል ➖ አዳርቃይ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን፤
ንግስት ኢሌኒ ሆስፒታል ➖ ዝቋላ ሆስፒታልን፤
ሚዛን ቴፒ ሆስፒታል ➖ ተንታ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን፤
ወላይታ ሶዶ ዩንቨርስቲ ሆስፒታል ➖ ዋድላ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን፤
አርባ ምንጭ ዩንቨርስቲ ሆስፒታል ➖ ላሊበላ ጠቅላላ ሆስፒታልን፤
ወልቂጤ ዩንቨርስቲ ሆስፒታል ➖ አምደወርቅ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን፤
ጅማ ዩኒቨርስቲ ህክምና ማዕከል/ነጆ እና ደምቢደሎ ሆስፒታል ➖ ደላንታ ሆስፒታልን፤
አምቦ ዩንቨርስቲ ሆስፒታል ➖ ቆቦ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን፤
መደ ወላቡ ዩንቨርስቲ ሆስፒታል/አዳማ ሜዲካል ኮሌጅ ➖ ሸዋሮቢት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን፤
መቱ ካርል ዩንቨርስቲ ሆስፒታል ➖ ቀርቻ ሆስፒታልን (ኦሮሚያ)፤
ሰላሌ ዩንቨርስቲ ሆስፒታል ➖ ግዳሚ ሆስፒታልን፤
ወለጋ ዩንቨርስቲ ሆስፒታል/ሻምቡ ሆስፒታል ➖ አቢደንጎሮ ሆስፒታልን፤
ቡሌሆራ ዩንቨርስቲ ሆስፒታል/ያቤሎ ሆስፒታል ➖ ሜልካሶዳ ሆስፒታልን፤
አሰላ ዩንቨርስቲ ሆስፒታል/አዳማ ሜድካል ኮሌጅ ➖ ጉዱሩ ሆስፒታልን፤
ደምቢደሎ ዩንቨርስቲ ሆስፒታል ➖ ቤጊ ሆስፒታል ጋር ትስስር በመፍጠር ወደ ድጋፍ ስራው ገብተዋል።

እነዚህ ሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች በአፋጣኝ ስራ ለማስጀመር እና ሙሉ ለሙሉ ወደነበሩበት ለመመለስ ከፍተኛ መዋለ ነዋይና ድጋፍ ስለሚፈልግ ሁሉም ባለድሻ አካላል ድጋፍ እንዲያደርጉ ጤና ሚኒስቴር ጥሪ አቅርበዋል።

via ENA

Leave a Reply