ሦስቱ መሪዎቻችን!!

Ethiopia smoke flag

የኢትዮጵያዉ የተወካዮች ምክር ቤት አዳራሽ ከአፍ እስከ ገደፉ ሞልቷል:: ጓድ መንግሥቱ ኀይለ ማርያም የኢትዮጵያ ሠራተኞች ፓርቲ (ኢሠፓ) ዋና ፀሐፊ፣ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት፣ የጦር ኀይሎች ጠቅላይ አዛዥ እጅጌ ጉርድ የሆነዉን ወታደራዊ ልብስ ለብሰው እና መለዮዋቸዉን አድርገዉ በምክር ቤቱ ፊት ለፊት ተሰይመዋል::

“ወንበዴዎቹ የአረብ ምንዳ ተከፋዮችም ጭምር ናቸው!”
“እነኚህን ተላላኪ ሀገር አፍራሾች፣ ከሀገራችን ለማስወገድ አንድ ሰው እና አንድ ጥይት እስኪቀረን ድረስ እንዋጋለን!”
ኮሎኔል መንግሥቱ ኀይለ ማርያም በተናገሩ ቁጥር ቁጣቸዉ ግንባራቸዉ ላይ ተጽፎ ይነበባል:: እልሃቸዉ እና የሀገር ተቆርቋሪነታቸዉም በቁጣ ከሚደመጡት ቃላት ውስጥ ጐልተዉ የታያሉ:: ተሰብሳቢው ንግግራቸዉን የሚያደምጠዉ በጽሞና እና በሙሉ ስሜት ነው::
“ትግራይ ክፍለ ሀገር ለኢትዮጵያ አንድ ቁና እህል አበርክታ አታውቅም:: እኛ ግን የትግራይ ሕዝብ እንዳይራብ እያልን በስንዴ ልመና የነጭ ፊት ይገርፈናል:: የትግራይ ገበሬ ደግሞ ወንበዴ ሆኖ ከቋጥኝ ቋጥኝ እየዘለለ ሀገሬን ይወጋል:: እኛ ለትግራይ ሕዝብ…”
ንግግራቸዉ በደማቅ ጭብጨባ ተቋረጠ:: ማን እንደጀመረዉ ባይታወቅም የአዳራሹ ተሰብሳቢ በሙሉ የግራ እጁን ጨብጦ ወደ ላይ ከፍ እያደረገ “ኢትዮጵያ ትቅደም!” የሚል መፈክር ያስደምጣል::
“ኢትዮጵያ ትቅደም!”
“ኢትዮጵያ ትቅደም!”
በምክር ቤት አዳራሽ ውስጥ ብቻ ሳይሆን ውይይቱን በአንድ ቴሌቪዥን ብዙ ሆነዉ የሚመለከቱ እና የሚያደምጡ ሌሎች ኢትዮጵያውያንም “ኢትዮጵያ ትቅደም!” የሚለውን መፈክር ተቀብለዉ እያስተጋቡት ነው::

የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኮሎኔል መንግሥቱ ኀይለ ማርያም በእልህ ጠረጴዛ እየደበደቡ እና እጃቸዉን እያወራጩ ያደረጉት ንግግራቸዉ ሲቋጭ ፊታቸዉ ላይ ከወረዛዉ ላብ የኢትዮጵያ ምስለ ካርታ ይታይ ነበር::

ሰውዬዉ በብሔራዊ ውትድርና ሰበብ በርካታ የደሀ ልጆችን ወደ ጦር ግንባር አሰልፈዋል ተብለዉ ቢታሙም ሀገራቸዉን በመውደዳቸዉ እና ዘረኛ ባለመሆናቸዉ ግን አንድም ሰው አያማቸዉም::

“አንድ ሰው እና አንድ ጥይት እስከሚቀረን ድረስ እንዋጋለን!” ያሉት ሰውዬ ብዙ ወታደሮች እና ብዙ ጥይቶች እየቀሯቸዉ በአሜሪካ ሴራ ከሀገር እንዲወጡ እና በዚንባቡዌ ጥገኛ ሆነዉ እንዲኖሩ ተገደዋል::

 • * *
  ቀጥሎ ደግሞ የደርግ መንግሥትም ሆነ ምክር ቤቱ ፈርሶ ኢሕአዴግ የነገሠበት ወቅት ነው:: የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትርም የትግራይ ተወላጁ አቶ መለስ ዜናዊ ሆነዋል:: የሀገሪቱ ጦር ጠቅላይ አዛዥም እሳቸዉ ናቸው::
  “ያለምንም ደም
  ኢትዮጵያ ትቅደም!
  የሚለዉ የደርግ ዝማሬ “ትግራይ እስክትለማ
  ሌላው ሀገር ይድማ!” በሚል ዝማሬ ተተክቷል የሚሉ ሀሜተኞችም ተፈጥረዋል::
  “አይጫንም እንጂ ውኃ በመኪና
  መቀሌ ነበሩ አባይ እና ጣና! ተብሎም ተገጥሟል::
  በመንግሥቱ ኀይለ ማርያም ቁና እህል አታመርትም የተባለችዉ የትግራይ ክልል እና ከተማዋ በልማት ተንቆጥቁጠዋል:: ወደ ትግራይ የሚወስዱት መንገዶች ጥራት፣ የመቀሌ ከተማ ውበት፣ የተገነቡት ፋብሪካዎች ብዛት እና ሌሎችም በክልሉ ውስጥ የፈሰሱ ሀብቶች በሀገሪቱ ወርቅ እና ነዳጅ የሚዘንብ እንጂ የሚወጣ እንኳን አላስመሰሉትም::

የኢሕአዴግ ዘመኑ የተወካዮች ምክር ቤት ውይይት ቀጥሏል:: አቶ መለስ አንዳንዴ ከፊታቸዉ ላይ ስውር መሰል ፈገግታ ያሳያሉ:: አንዳንዴ ደግሞ ኮስተር ለማለት ይሞክራሉ:: በአጠቃላይ ገጽታቸዉን አይቶ ባህርያቸዉ አንዲህ ነው ለማለት አይቻልም:: ንግግራቸዉን ግን ቀጥለዋል፤
“አብዛኛዎቹ ኦሮሞዎች ውስጣቸዉ ቢፋቅ ኦነጐች ናቸው:: ይሄ የማይታበል ሀቅ ነው:: ኦነግ ደግሞ የተሰጠዉን ዕድል አልጠቀምም ያለ እና ፓርላማን ሳይሆን ጫካን የሚወድ ቡድን ነው!”

“እኛ ተቃዋሚ ነን የሚሉ ፓርቲዎችን እስከ ግማሽ መንገድ ተጉዘን ለመቀበል ዝግጁዎች ነን!” “የስኳር እና የጨው መጠቅለያ በሆነ ጨርቅ ላይ ያን ያህልም መከራከር የለብንም:: ሰንደቅ ዓላማን መውደድ ሀገርን መውደድ ነው ብዬም አላምንም!”

“አንድ ሰው እጅ ከፍንጅ ሲሰርቅ እስካልተያዘ ድረስ ሌብነቱ እንደ ሥራ ሊቆጠርለት ይችላል!” “አንዳንድ የድሮ ሥርዓት ናፋቂዎች እና ትክህተኞች አሁንም ድረስ በድሮ በሬ እንድናርስ ይፈልጋሉ፤ ይህ ግን ከአሁን በኋላ ህልማቸዉ እንጂ እውን አይሆንም!”

“ለኦሮሞ ሥልጣን መስጠት እና ለሕፃን ልጅ ብርጭቆ መስጠት አንድ ናቸው:: ሁለቱም በተሰጣቸዉ ነገር በአግባቡ መጠቀም ስለማይችሉበት ይሰብሩታል!”
“የአክሱም ሀውልት ለወላይታ ምኑ ነው?”…
የመለስን የምክር ቤት ንግግር ከሚሰማዉ ተሰብሳቢ ይልቅ የተኛዉ ይበዛል:: ያልተኙትም ቢሆኑ እሳቸዉ ሲቆጡ ፊታቸዉ እየተቆጣ፣ እሳቸዉ ፈገግ ሲሉ ከትከት ብለዉ እየሳቁ፣ መሪዉ አድርጉ ያሏቸዉን የሚያደርጉ ገፀ -ባህሪዎች ይመስላሉ::
ከምክር ቤቱ ወጥተናል::

የካቲት 11 የትሕነግ የልደት በዓል ሆኖ ይከበራል:: አቶ መለስ ዜናዊም በመቀሌ ከብዙ የትግራይ ተወላጆች ጋር ተገናኝተዋል:: ፈገግታቸዉ ከምሥራቋ ጮራ ይበልጥ ፈንጥቋል:: ሕዝቡም ደስታዉን ከአለባበሱ ጀምሮ በተለያየ መንገድ እየገለፀ ነው::
“እንበር ተጋዳላይ!” ይዘፈናል::
“አጁሀ! አጁሀ!” ይደነሳል::
ከበሮዎችን እየዘለሉ የሚደልቁ ትግሬዎች በዝተዋል:: ክብ ሠርተዉ “እስክስ!” እያሉ የሚሽከረከሩትም ከልክ በላይ ናቸዉ:: በአጠቃላይ የመቀሌ ስታዲየም እና ራሷ መቀሌ፣ እንዲሁም ኢትዮጵያ በሙሉ የነሱ የሆነች ያህል ፈንጠዚያዉ በዝቷል::

መለስ በትግርኛ ሲናገሩ ስታዲየም ሙሉ የሆነው ሕዝብ ጸጥ ረጭ ብሎ ያዳምጣቸዉ ጀምሯል:: “እናንተ ወርቅ የሆናችሁ ሕዝብ ናችሁ!” ሲሉ በስታዲየሙ የሞላዉ ሕዝብ ጩኸቱን አቀለጠዉ::

“ወርቅነታችሁ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካም ጭምር ነው:: ለምን? ብትሉኝ ያሸነፋችሁት በአፍሪካ በጦር ኀይል ብዛት አንደኛ ነኝ የሚለዉን ደርግን ነው:: ስለዚህ የትግራይ ሕዝብ በእሳት የተፈተነ ወርቅ እና ጀግና ሕዝብም ነው!”
እያንዳንዷን የመለስ ቃል ደስታ እና ሆታ ያቋርጣታል:: አቶ መለስም እጅግ ፈገግ ብለዉ የትግራይ ሕዝብ ከኢትዮጵያ ሕዝብ የተለየ እና ጀግና የሆነ ሕዝብ መሆኑን መናገራቸዉን ቀጥለዋል::
* * *
ከጀግና ሕዝብ ተወለድኩ ያሉት መለስ ዜናዊ በአሜሪካ በሚደረግ አንድ ጉባኤ ላይ አበበ ገላዉ ከሚባል አንድ ኢትዮጵያዊ ታላቅ ተቃውሞ ደረሰባቸዉ:: አበበ ገላው በአዳራሹ ውስጥ ድምፁን ጐላ አድርጐ በእንግሊዝኛ ቋንቋ፣
“መለስ አምባገነን ነው!”
“መለስ ዜናዊ አምባገነን ነው!”
እያለ ደጋግሞ ጮኸ:: መለስም ይሄንን ንግግር ሲሰሙ ልባቸዉ ከዳቸዉ:: ዓይኖቻቸዉ ወደ ሽፋሎቻቸዉ ውስጥ ገቡ:: ፊታቸዉ ተቀያየረ:: ከዚያች ቀን በኋላ መለስ ታመሙ:: የሕክምና እርዳታ በተለያዩ ቦታዎች ሲደረግላቸዉ ቢቆይም እስከ ወዲያኛው ተሸኙ::

 • * *
  መጋቢት 2010 ዓ.ም፤ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነዉ የተሾሙት ደግሞ የኦሮሞው ተወላጅ ዓቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ናቸው:: ሰውዬዉ መጋቢት 24 ወደ ሥልጣን ሲመጡ ባደረጉት ንግግር ላይ “ኢትዮጵያ” የሚለዉን ቃል ለብዙ ጊዜ ደጋግመዉ ጠርተዋል:: እሳቸዉም ጭምር ያሉበት የኢሕአዴግ መንግሥት በሕዝብ ላይ በደል ሲፈጽም እንደነበር አምነዋል::
  “በእናንተ በምንመራችሁ ሕዝብ ላይ ላደረስንባችሁ በደል ይቅር በሉን!”
  “በውጪ ሀገር የምትገኙ የተፎካካሪ ፓርቲዎች ወደ ሀገራችሁ ገብታችሁ በዴሞክራሲያዊ መንገድ መፎካከር ትችላላችሁ!”
  “በአዲሱ መንግሥት ውስጥ የሴቶች ሚና ይጐላል!”
  “ከዚህ በኋላ የኢትዮጵያ ሕዝብ በቀን ጅቦች አይበላም!…”
  የሰውዬዉ ንግግር መላ ኢትዮጵያውያንን ከጫፍ እስከ ጫፍ ያነቃቃ ነው:: ሰውዬዉ በዚህ ብቻ ሳይበቃቸዉ በየክልሉ እየዞሩ ባደረጓቸዉ ንግግሮችም ከፍተኛ የሕዝብ ተቀባይነትን አግኝተዋል:: ሁሉም በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙት ብሔሮች እኩል ናቸው ማለታቸዉም “ኢትዮጵያዊዉ ሙሴ መጣ” እስከመባል አድርሷቸዋል::

ዶ/ር ዐቢይ የገቡበት የአራት ኪሎዉ ቤተ መንግሥት ግን በምቾት አልተቀበላቸዉም:: ወርቅ ሕዝብ ነን ያሉት ትግራዮች እና ተረኛ መሪ መሆን እንፈልጋለን ያሉት ኦነጐች ለሰውዬዉ ከባድ ፈተና ሆነውባቸዋል::

የኢትዮጵያ አና የመሪዋ ፈተና በዝቶም በሰውዬዉ ላይ ተደጋጋሚ የግድያ ሙከራዎች ተካሄዱ:: የአማራ ብሔር ተወላጆች በየአቅጣጫዉ መሰደድ እና መገደል እጣ ፈንታቸዉ ሆነ:: የጐዳና ላይ ተቃውሞዎች በረከቱ:: ኮቪድ የዜጐች ሕይወት ስጋት ሆነ:: የትግራይ ክልል የዓቢይን መንግሥት አንቀበልም አለ:: ትግራዮች የራሳቸዉን ምርጫም አካሄዱ:: ትግራዮች በሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሠራዊት ላይ ጭፍጨፋ አደረጉ::

ኢትዮጵያ ወደ ሕግ ማስከበር ዘመቻ ገባች:: በማይካድራ ብዙ አማራዎች ተጨፈጨፉ:: በመጨረሻም ኢትዮጵያ በሕግ ማስከበር ዘመቻዉ አሸነፈች:: በርካታ የትግራይ መሪዎች ተገደሉ፤ ታሰሩ፤ ተሰደዱ:: መቀሌም በመንግሥት ቁጥጥር ስር ሆነች::

የመንግሥት ሠራዊት ከመቀሌ በተለያዩ ምክንያቶች ሲወጣ ጦርነቱ ዳግም አገረሸ:: የትግራይ ወራሪ ቡድንም በርካታ የአማራ አካባቢዎችን ወረረ:: ሕዝቡን በግፍ ጨፈጨፈ፣ ንብረቱን ዘረፈ፤ አወደመ፤ በርካታ ወንጀሎችን ፈፀመ:: ይህ ሁሉ ሲሆን የትግራይ አሸባሪ ቡድን እና ኦነግ ሸኔ (አሸባሪዎች) ተብለዉ በሀገሪቱ ምክር ቤት ተፈርጀዋል::
ሕግ ማስከበሩ በህልውና ማስከበር ዘመቻ ተተካ:: ዶ/ር ዐቢይም በምክር ቤት ውስጥ እና በተለያዩ ቦታዎች ባደረጓቸዉ ንግግሮች ኢትዮጵያ የማሸነፍ እንጂ የመሸነፍ ታሪክ የላትም!” አሉ::

“ስለ ሀገራችን አንገታችንን እንሰጣለን እንጂ ኢትዮጵያችን አትፈርስም!”
“ኢትዮጵያን ለማሸነፍ የሚፈልጉ ካሉ፣ የኢትዮጵያን ታሪክ የማያውቁ ብቻ ናቸው!…”
ጦርነቱ እየሰፋ እና እየከፋ መጣ:: የትግራይ ወራሪ ቡድን መሪዎችም ኢትዮጵያውያን እጅ እንዲሰጡ ጠየቁ:: አዲስ አበባ ሊገቡ በመሆኑ ከመንግሥት ጋር ድርድር ማድረግ እንደማይፈልጉም ተናገሩ::

ዶ/ር ዐቢይ “እኔ በግንባር ሆኜ ጦሩን ልመራ ዘምቻለሁ እና ተከተሉኝ!” ሲሉ ለኢትዮጵያውያን መልዕክት አስተላለፉ:: የአማራ ሕዝብ ሆ! ብሎ ወደ ግንባር ዘመተ:: የኋላ ደጀኑም ስለ ሀገሩ ሲል በደጀንነት ተሰለፈ::

በአጭር ቀናት ውስጥ የትግራይ ወራሪ ቡድን በአማራም ሆነ በአፋር በወረራ ከያዛቸዉ ሁሉም ቦታዎች ውስጥ ተጠራርጐ ወጣ:: ድሉም የአፋሮች፣ የአማራዎች እና የሁሉም ኢትዮጵያውያን ሆነ::

ትፈርሳለች የተባለችዉ ኢትዮጵያ አልፈረሰችም:: ነገስ ምን እናይ ይሆን?

(እሱባለው ይርጋ)
በኲር ታኅሣሥ 25 ቀን 2014 ዓ.ም ዕትም
(አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን)

Related posts:

«ሕወሓት ጦርነትን እንደ አምልኮ የሚቆጥር ቡድን ነው» – ፕሮፌሰር ሀረገወይን አሰፋ
«በሕገወጦች ላይ ያለ ምኅረት እርምጃ መውሰድ አለብን፤ ይህ የመንግሥት ተግባር ነው» የአማራ ክልል
125 አዳዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ
«በአገሩ መከላከያ ላይ አፉን የሚከፍት ሕዝብ የለም፤ መንግስትም አይታገስም» ክብር ለመከላከያ ሰራዊት!!
በኢትዮጵያና ቱርክ መካከል የተደረገውን የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት ምክር ቤቱ አጸደቀ
የሞት ፍርደኛው የ25 ዓመታት ሰቆቃ! ከመሬት በታች የታፈኑት አባት
«ኢትዮዽያን ማስቀጠል ከሚፈልጉት ጎን በመሆናችን የሚከፋ ከአለ እርሱ መፍረሷን የሚናፍቅ ብቻ ነው!»
ደብዳቤ ለኢትዮጵያ - ከቢልለኔ ስዩም
የዓለም ባንክ የ300 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ፈረመ
"እናቴ ፍጹም እስር ቤት እንድትገባ አልፈግም" ብሎ እግሩን ያጣው ወጣት ምስክርነት ለሮይተርስ
"አልዘምትም" ወይም "ከጠላት ጎን እሰለፋለሁ" ማለት ሲቻል ማውሰብሰብና ማድበስበስ አይገባም!
አብዱላሂ ፋርማጆ ለአዲሱን ፕሬዝዳንት «ሁሉም ወገኖቼ እንዲደግፉህና እንዲጸልዩልህም እጠይቃለሁ»
መንግስ የጸጥታ ሃይሎች ለየትኛውም ዓይነት ትንኮሳ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ማድረጉን አስታወቀ
በትግራይ 5.2 ሚሊዮን ሕዝብ ዕርዳታ እየደረሰ ነው፤ ከሺህ በላይ የጭነት መኪኖች ታግተዋል፤ 76 ቢሊዮን ብር ወደ ትግራይ ተልኳል
የደህንነት ጥናት አዲሱ ምዕራፍ - ጂኦስፓሻል ኢንተለጀንስ

Leave a Reply