ቻይና ምጽዋንና አሰብን ልታለማ ነው – ኢሳያስ ከቻይና ግብዣ ደረሳቸው፤ ለአሜሪካ መርዶ

በቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ የተመራ የልኡካን ቡድን የኤርትራን ጉብኝት ተከትሎ ምጽዋንና አሰብን ለማልማት የሚያስችል ስምምነት ላይ መደረሱ ተሰማ። የቻይናው ፕሬዝዳት ለኤርትራው አቻቸው ኢሳያስ አፈወርቂ የጉብኝት ግብዣ ማቅረባቸውም ይፋ ሆኗል። ስምምነቱ በቀይ ባህር ፖለቲካ መያዣ መጨበጫ ላጣችው አሜሪካ መርዶ እንደሆነ ተመልክቷል።

የቻይናው ፕሬዝዳንት ለኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የላኩት የጉብኝት ግብዣ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አማካይነት ተሰጥቷቸዋል። ከዚህም በተጨማሪ በተለያዩ አካብቢያዊ፣ ልማታዊና የኢንቨስትመንት ጉዳዮች ላይ መምከራቸው ተመክቷል። ለስራ ጉብኝት አሰመራ የሚገኙት የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዋንግ ዪ ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ ጋር በተባሉት ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን በደፋናው ያመልከቱት የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል ናቸው።

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ የቻይናን የ100 ዓመታት ጉዞ፣ እንዲሁም በዓለም ዐቀፍ ሕጎች ማዕቀፍ ውስጥ ሆና ዓለምን ሚዛናዊ ለማድረግ የምታደርውን ጥረት ማድነቃቸውን ሚኒስትሩ ገልጸዋል። አያይዘውም በምፅዋና አሰብ ወደቦች ልማት፣ በሰው ኃይል አቅም ግንባታ፣ በመሰረተ ልማትና ማዕድን ዘርፍ ትብብራቸውን ለማጠናክር ከስምምነት መደረሱን አመልክተዋል።

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የቻይና ዋንግ ጉብኝትና ቻይና ለፕሬዚዳንት ኢሳያስ ያቀረበችው ይፋዊ የክብር ጥሪ ተከትሎ ጉዳይ ለአሜሪካ” መርዶ” እንደሆነ እየተገለጸ ነው። ኢሳያስ አፉወርቂንና አብይ አህመድን በትህነግ አማካይነት ለማስወገድ ጉድጓድ ስትምስ የከረመችው አሜሪካ በስተመጨረሻ ለጊዜው ኪሳራ ውስጥ እንደገባች ነው እየተገለጸ ያለው። ኢትዮጵያ፣ ኤርትራና ሶማሊያ አንድ ላይ ያቀደቱን የጋራ ውጥን የሚቆም እንዳልሆነ አመላካች እንደሆነም ተመልክቷል።


Leave a Reply