የዘጸዓት ማስጠንቀቂያና ጥሪ “በወልቃይትን ጉዳይ ለመከራከር ሰነድ የለንም”

የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር የፕሮፖጋንዳ ግንባር ቀደም ተሰላፊ እንደሆኑ የሚነገርላቸውና ዘጻዓት Zetseat Save Adna በሊል የፌስ ቡክ ስም የሚታወቁት ሰው በውልቃይት ጉዳይ “ለመከራረከር ማስረጃ የለንም” ሲሉ የትግራይ ምሁራን ከዜሮ ጀምረው እንዲረባረቡ የወቀሳና የማስጠንቀቂያ ጽሁፍ አሰራጩ። ከትግረኛ ወደ አማርኛ የተተረጎመውና በአቶ ቹቹ ገጽ ላይ የታተመው ይህ ጽሁፍ የወልቃይት ጉዳይ ወደ ፍርድ ግልግል እንደሚሄድ ተስፋ የሰነቀ ነው።

የትህነግ ወራሪ ሃይል መሪ በሰላም ካልሆነ በሃይል፣ ዶከተር ደብረጽዮን ደግሞ “ቅድሚያ ተኩስ አቁም”፣ ጻድቃን ጌታቸው ረዳ ቀደም ሲል በሃይል እንደሚደረምሱና እንደሚወስዱት ሲናገሩለት የነበረው የወላቃይትና አካባቢው ጉዳይ ለአቶ ዘጸዓት እድሮ ወደ ግልግል ፍርድ እንደሚሄድ ሲገልሱ መነሻቸውን አላብራሩም። ባድመን በተመሳሳይ ስንፈት እንዳጡ ገልጸው ወልቃይትንም እንደከሰሩ በማስታወቅ ለትግራይ ም ሁራን ሲሉ ጉዳይ ውርደትና የቁም ሞት እንደሆነ አመልክተዋል። ሙሉ ትርጉሙን ተውሰን አቅርበነዋል።

ጫንቃችን ላይ ላይ ያለው ከባድ ዕዳ

ምዕራብ ትግራይ- ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ሑመራ፣ ጠለምትን በሚመለከት ፤ በተለይ ወልቃይትን በሚመለከት አምሓሩ (አማራ ማለቱ ነው) ባለፉት 10 ዓመታት ከ20 በላይ መፅሐፎችን ፅፈዋል።

  • የአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን፣ በታዊቂ ጆርናሎች ከ100 በላይ አርቲክሎች አሳትመዋል።
  • ባለፉት ሃያ ዓመታት በ 500 ዘፈኖቻቸው ወልቃይት ጠገዴን አስገብተው ዘፍነዋል ።
  • በእነ ኪሮስ ቢተውና አባይ ወልዱ መሬታቸው ተቀምቶ ለነ ኪሮስ ቢተው ወዳጆች የታደለባቸው የቀድሞ የህወሐት ታጋዮች እነ ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ የአምሐራ (የአማራ) ብሔርተኝነት አርአያ ሆነው ወጥተዋል ። በእኛ ወገን እሳ ?
  • በፌስቡክ በወቅቱ የነበሩ እነ አይጋ በሚባሉ ዌብሳይቶች የፃፍናቸው ጠርቆሽቆሽ ያሉ አንድ አስር የደከሙ አርቲክላት አይጠፉም ። በሆርን አፌየርስና ሌሎች አንድ ሁለት በሚሆኑ ተጨማሪ ዌብሳይቶች አንድ ሁለት የሚሆኑ ፅሑፎችም አይጠፉም ፤
  • በዚህ ጉዳይ በደንብ የተደራጀ መፅሐፍ – ዜሮ-Major publication – ዜሮ
  • ከተወሰኑት ወጪ አብዛኞቹ ዘፈኖቻችን ከሽሬ ይመለሳሉ … ይኼ እንግዲህ ከዚህ በፊት ያለው ነው ፤ በቅርብ ጊዜ ደግሞ የባሰ ፤ ከቀድሞውም የባሰ ፣ አሳፋሪ ትእይንት በገሃድ ይታያል፤
  • የህወሐት ባለ ስልጣናት መቀሌ እንደገቡ ጭራሽ በምእራብ ትግራይ ያለው ህዝባችን ተረሳ፤ አልፎ አልፎ ተከዜ ላይ ሬሳዎች ተንሳፈው ሲታዩ ከመፃፍ ውጪ ምዕራብ ትግራይ ሙሉ በሙሉ ተረሳ ፤
  • እነ ድምፂ ወያኔ ፤ ጌቾ፤ ትግራይ ቴሌቪዥን ፤ የክልላችን ፕሬዝዳንት፤ ሁሉም ኃላፊዎች ” ትግራይ ሲዒራ / ትግራይ አሸነፈች/”, ሆኗል መፈክራቸው ።”ትግራይ ነፃ ወጣች ” ም ሲባልም ነበር ። በተለይ ደሴ ሲደረስ የምዕራብ ትግራ ጉዳይ ተረሳ፤ ወሬያችን “በሎም” ” መጣን”፣ ” ድል አድርገናል” ሆነ። እነ ዊልያም ምን የማያደርጉን አለ?
  • አምሓሩ (አማሮች ለማለት ነው ) ከሃያ ምናምን ዓመታት በላይ ጥርሳቸውን ነክሰው ሲፋለሙን እኛ ግን የኛ ወገኖች እየተገደሉ ሬሳቸው ተከዜ ላይ የሚንሳፈፉትን ረስተን “ትግራይ ስዒራ/ ትግራይ አሸንፈች / ” የምንል ከሆነ እነ ዊልያም ምን ያላደረጉን አለ ። ስለዚህ Esayas Hailemariam ወቀሳህ ሚዛን የሚደፋ አንደለም ።

እንደ ትግሬ እራሳችን በወደቅን፤ ውድቀታችንን በሰው አናሳብብ ። ይኼ ጉዳይ ወደ አለም አቀፍ መገናኛ አውታሮች ፤ ወደ አሸማጋይ አካላት ቢቀርብ ምን ይዘን ነው የምንቀርበው ? በእጃችን ያዘጋጀናቸው ምን አይነት የሰነድ ጭብጦች አሉን ? ይኼ ጉዳይ ወደዛ የማምራት እድሉም ሰፊ ነው ። በዚህ ጉዳይ ላይ በተለይ የትግራይ ምሁራን ምን እያደረጋችሁ ነው ?

በዚህ ጉዳይ GSTS ትልቁን ድርሻ ሊወጣ ይገባል። በ GSTS ውስጥ ያላችሁ የትግራይ ምሁራን የቀረው ይቅር ብላችሁ ይችን ጉዳይ ስራየ ብላችሁ ብትይዟት በብዙ ሁኔታ እንጠቀም ነበር ። [ በዚህ ጉዳይ ላይ ለመስራት ሃሳብ ያላችሁ አደረጃጀት ውስጥ ያልገባችሁ የትግራይ የታሪክ ምሁራን ሌሎች በዚህ ጉዳይ ላይ መስራት የሚፈልጉ ግለሰቦች ስላሉ በውስጥ አግኙኝና ከእነርሱ ጋር አገናኛችኋለሁ ።]

አስተውሉ ትላንት በስንፍናችን በባድመ የገጠመንን እናውቃለን፤ የትግራይ እንብርትና እስትንፋስ በሆነው የምእራብ ትግራይ የባለፈውን ከደገምን የዘለዓለማዊ ውርደት ፤ የሃዘን፤ የልቅሶ እሽክርክሪት ውስጥ እንገባለን ። አስተውሉ ይኼ ጉዳይ ወደ አሸማጋይ አካላት የመሄድ እድሉ ሰፊ ነው ፤ በአሁን ጊዜ የሚተጣጠፍ ሥራ መስራት ካልቻልን ቀደም ብየ ያልኩት የዘልአለም ውርደትና መጥፋት የምንችልበት ሁኔታ ሰፊ ነው ።

እህትና ወንድሞቼ ፤ ብዙ ሥራ የሠራነው እንዳለ አውቃለሁ፤ 99.9% ዋናው ሥራችን ግን ከፊት ነው ያለው ፤ ስለሆነው ከዜሮ እንደመጀመር ቆጥረነው በጥበብ ፤ በትዕግስት፤ ጥርሳችንን ነክሰን እንስራ ።

Ztseat Saveadna Ananya

Jan0uat0ry0 ia3 a1Spt 2tlhmoreh:306h dAM0  · ኣብ ዝባንና ዘሎ ኸቢድ ዕዳ፣ምዕራብ ትግራይ – ወልቃይት፣ ፀገዴ፣ ሑመራ፣ ፀለምቲ- ብዝምልከት ፤ ብፍላይ ወልቃይት ብዝምልከት ኣምሓሩ ኣብ ዝሓለፉ 10 ዓመታት ልዕሊ 20 መፃሕፍቲ ፅሒፎም እዮም። – ኣብ ዓበይቲ ዓለም ለኻዊ መራኸብቲ ሓፋሻት፣ ፍሉጣት ጆርናላት ልዕሊ 100 ኣርቲክላት ኣሕቲሞም እዮም። – ንልዕሊ 20 ዓመታት ኣብ ልዕሊ 500 ደርፍታቶም ንወልቃይትን ፀገዴን ኣእትዮም ደሪፎም እዮም።- ብኒ ኪሮስ ቢተውን ኣባይ ወልዱን መሬቶም ተሓዲጉ ንፈተውቲ ኪሮስ ቢተው መሬቶም ዝተዓደለሎም ናይ ቀደም ተጋደልቲ ህወሓት እኒ ኮ/ል ደመቀ ዘውዱ ናይ ኣምሓራ ብሄራውነት ኣርሓታት እዮም ኮይኖም ወፂኦም። ብወገን ንሕና ኸ?- ኣብ ፌስቡክን በቲ እዋን ዝነበራ ከም ዓይጋ ዝበላ ዌብሳይታትን ዝፀሓፍናየን ሓደ 10 ጠርቆሽቆሽ ዝበላ ኣርቲክላት ኣይሰኣናን። ኣብ ሆርን ኣፌይርን ሓደ ኽልተ ተወሰኽቲ ዌብሳይታትን እውን ዝተፅሓፋ ሓደ ኽልተ ፅሑፋት ኣይሰኣናን፤- ኣብዚ ጉዳይ ብስሩዕ ዝተዳለወ መፅሓፍ- ዜሮ- Major publication – ዜሮ፣- ደረፍትና- ካብ ዝተወሰኑ ወፃኢ መብዛሕቲኦም ካብ ሽረ ይምለሱ…እዚ ናይቲ ሕሉፍ እዩ፤ኣብ ቀረባ እዋን ድማ ዝገደደ፣ ዝሓመቐ፣ መሕፈሪ ተርእዮ ተጋሂዱ፤- ሰበ-ስልጣን ህወሓት መቐለ ምስኣተው ኣብ ምዕራብ ትግራይ ዘሎ ህዝብና ተረሲዑ፤ ሓልሓሊፉ ኣብ ተከዘ ዝንሳፈፉ ሬሳታት እንትንርኢ ካብ ምፅሓፍ ወፃኢ ጉዳይ ምዕራብ ትግራይ መሊኡ ተረሲዑ፤ – እኒ ድምፂ ወያነ፣ ጌቾ፣ ቴሌቪዥን ትግራይ፣ ፕሬዚዳንት ክልልና፣ ኹሎም ሓለፍቲ “ትግራይ ስዒራ” ኾይኑ ጭርሖኦም።”ትግራይ ሓራ ወፂኣ” እውን ይብሃል ነይሩ።ብፍላይ ደሴ ምስተበፅሐ ጉዳይ ምዕራብ ትግራይ ተረሲዑ፤ ዘረባና “በሎም”፣ “መፃና” ፣ “ተዓዊትና” ኾይኑ።እኒ ዊልያም እንታይ ዘይገበሩ እዮም? ኣምሓሩ ዒስራን ገለን ዓመታት ነኺሶም እንትቃለሱ ንሕና ወገንና በብመዓልቱ እናተቐተለ ሬስኡ ኣብ ተከዘ እናተንሳፈፈ ንኡኡ ረሲዕና “ትግራይ ስዒራ” ንብል እንተኾይንና እኒ ዊልያም እንታይ ዘይገበሩ? ስለዚ Esayas Hailemariam ወቐሳኻ ሚዛን ዝደፍእ ኣይኮነን። ናይ ባዕልና ከም ተጋሩ ዝወደቕናዮ ውድቀት ናብ ሰብ ኣይነጣብቕ።እዚ ጉዳይ ናብ ዓለም-ለኻዊ መጋባእያ፤ ናብ መሸማገልቲ ኣካላት እንተቐሪቡ እንታይ ኢና ሒዝና ክንቐርብ? ኣብ ኢድና እንታይ ዘዳለናዮም ናይ ሰነድ ጭብጢታት ኣለውና? እቲ ጉዳይ ናብኡ ዘምርሓሉ ዕድል ድማ ሰፊሕ እዩ።ኣብዚ ጉዳይ ብፍላይ ምሁራት ታሪኽ እንታይ ትገብሩ ኣለኹም? ኣብዚ GSTS እውን ዓብዪ ተራ ክፃወት ኣለዎ። ኣብ GSTS ዘለኹም ምሁራት ትግራይ ዋላ ኩሉ ገዲፍኩም ነዚኣ ስርሐይ ኢልኩም እንተትሕዙዋ ክንደይ ምተረባሕና።[ኣብዚ ጉዳይ ክትሰርሑ ሓሳብ ዘለኩም ዘይተወደብኩም ተጋሩ ምሁራት ታሪኽ ምስ ካልኦት ኣብዚ ጉዳይ ክሰርሑ ዝደልዩ ዝተወሰኑ ውልቀ-ሰባት ስለዘለው ምስኦም ከራኽበኩም ብውሽጢ መስመር ተዳሃዩኒ።]ኣስተውዕሉ፤ ትማሊ ብሕመቕና ኣብ ባድመ ዝገጠመና ንፈልጦ ኢና፤ ኣብ ጉዳይ ሕምብርቲ ትግራይ ዝኾነ ምዕራብ ትግራይ እዚኣ እንተደጊምና ኣብ ዘለኣለማዊ ናይ ውርደት፣ ናይ ሓዘን፣ ናይ ንብዓት ዓንኬል ኢና ክንኣቱ። ኣስተውዕሉ፣ እቲ ጉዳይ ናብ መሸማገልቲ ናይ ምኻድ ዕድሉ ሰፊሕ እዩ፤ ሐዚ ዝተዓፃፀፈ ስራሕ እንተዘይሰሪሕና ድማ ናይቲ ዝበልኩዎ ዘለኣለማዊ ውርደትን ብርሰትን ተኽእሎ ኣዝዩ ሰፊሕ እዩ።ኣሓትን ኣሕዋትን፤ ዝሰራሕናዮ ብዙሕ ከምዘሎ ይፈልጥ፤ 99.9 % ስራሕና ግን ኣብ ቅድሚት እዩ ዘሎ፤ ስለዚ ዳርጋ ካብ ባዶ ከምእንጅምር ሓሲብና ብጥበብ፣ ብዓቕሊ፣ ስንና ነኺስና ንስራሕ፤


Leave a Reply