ጀረሚ ከበገና ጋር በፍቅር ከወደቀ ረዥም ጊዜ አልሆነውም።
በአንድ ዕውቅ ኢትዮጵያዊ አርቲስት አማካኝነት ከአንድ ወጣት የበገና መምህር ጋር ተዋወቀ።
መምህሩ በዚህ ሐተታ ማሳረጊያ ታሪኩን የሚተርክልን መምህር ኤርሚያስ የሚባል ሰው ነው።
ጀረሚ የዚህን መሣሪያ ምሥጢር ለመረዳት ተጣጥቦ ወደ መምህር ኤርሚያስ ቀረበ።
ምንም ነገር ሳይሆን “ቀና ልብና ጥልቅ ጉጉት” ይዤ ነው በገና ያነሳሁት ይላል።
ጣቶቹን ወደ በገና ክሮች ባሳረፈ ቅጽበት ነበር ስሜቱ መናወጥ የጀመረው።
መምህር ኤርሚያስ ጀረሚን “ሁልጊዜም የበለጠ ለማወቅ ጉጉት የማይበት ብርቁ ተማሪዬ ነው” ይለዋል።
አሜሪካዊው ጀረሚ፣ “ሕይወቴን ሙሉ ብዙ መንፈሳዊ ፍተሻ አድርጊያለሁ፤ ምሥራቃዊ ጥሞናንም ዘልቄበታለሁ። ለነፍሴ ቅርብ የሆነልኝ ግን በገና ነው” ይላል።
ቀደም ባለው ጊዜ ጀረሚ በቀን ለሦስት ሰዓታት ያህል በጥልቅ ጥሞና ውስጥ ይቆይ ነበር። በተለይ በዮጋና ሜዲቴሽን የምስጠት ሥርዓት ውስጥ።
ይሁንና በገና ስደረድር ነፍሴ ድረስ ዘልቆ የሚሰማኝ አንዳች ነገር አለ ይላል።
ለጀረሚ ያ የሚነዝረው የበገና ድምጽ ዝም ብሎ ድምጽ አይደለም።
“ነገሩ እንዲገለጥልህ ልበ ቀናነት ይሻ ይሆናል። በበጎ መንፈስ ልትማረው ይገባ ይሆናል፣ ብቻ እኔ’ንጃ።”
እንደሱ አገላለጽ በገና ደርዳሪውን ብቻ አይደለም ከዓለማዊ የስሜት ወጀብ የሚፈውሰው። አዳማጩም ከበረከቱ ተጋሪ ነው።
ጀረሚ፣ ‘በጉዳዩ ላይ ሊቅ አይደለሁም፣ ነገር ግን በገና ከመንፈሳዊ ገጽታው ባሻገር ሳይንሳዊ ገጽታ እንዳለው እረዳለሁ’ ይላል።
በተለይም የፊዚክስ ንዝረተ ድምጽ የፈውስ አቅም እንዳለው እንደሚታመን፣ በገናም ንዝረቱ በጆሮ ተንቆርቁሮ ወደ ነፍስ ሲሄድ ነፍስን በቂቤ የመታሸት ያህል እፎይታን እንደሚሰጠው ያብራራል።
“በኳንተም ፊዚክስ ሁሉም ነገር ንዝረት ነው ይላሉ። በበገና በንዝረቶች ውስጥ ከሰውነታችን አንዳች ነውጥ ቀስ እያለ ሲሰክን ነው የሚሰማኝ።”
በአእምሮ ውስጥ የስክነት ጅረት ከአንድ የሰውነት ክፍል ወደ ሌላው ሲፈስም ይሰማል።
ጀረሚ ነጭ አሜሪካዊ እንደመሆኑ 2 ሜትር በገና ተሸክሞ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ዘምበል ደፋ ሲል ሐበሾች ምን ይሉት ይሆን?
- ተጨማሪ አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሊደረግ ነውየኢትዮጵያን…
- ከአርሰናልና ከሲቲ የተሻለ ዕድል ለማን? አሃዛዊ መረጃዎች ወዴት ያደላሉከሚታወቅበት…
- የበዓሉ ግርማ ኦሮማይ – ዛሬ ለምን?ትህነግ…
- የበታችነትና የበላይነት ስቃይ “እኩል የኢትዮጵያ ስጋት ናቸው”መባሉ ጫጫታ አስነሳ?ዛሬ…
- ሩሲያ የኑክሌር ጦር መሳሪያዎቿን ቤላሩስ ውስጥ ልታጠምድ ነውሩሲያ…
- ኦሮሚያ በአራት ወር መቶ ሺህ ዘመናዊ የገጠር መኖሪያ ቤቶች ሊገነባ ነውበቀጣዮቹ…
- በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅከለውጥ…
- በእውሸት “ታሰሩ፣ታፈኑ” በሚል ስማቸው በሚዲያዎች የተሰራጨው ስድስት ወጣቶች የፍቅር ግንኙነት መስርተው ተገኙበአንድ…
- ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ዛሬ ከጉራጌ ማህበረሰብ በቤተመንግስት በነበረው ውይይት ከተናግሩት“ደሜ…