ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ከአሜሪካው መሪ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ጋር በስልክ ውይይት ማድረጋቸውን ተከትሎ ኬንያን ቀደም ሲል ከኢትዮጵያ ሲቀርብ የነበረውን ጥያቄ መቀበሏ ተሰማ። በጥያቄው መሰረት ድንበሯን ትዘጋለች። ኬንያ ተቀምጠው አማጺያንን የሚያደራጁ ተላልፈው ይሰጣሉ። ዘጠኝ አባላት አሉት የተባለው ህዝብረት መፈረሱ ተሰማ።

በኬንያና ኢትዮጵያ ድንበር ኮሪዶር፣ እንዲሁም ናይሮቢ ቢሮ ከፍተው የሚንቀሳቀሱ ነባርና አዳዲስ አማጽያንን ከነመሪዎቻቸው ኬንያ አሳልፋ እንደምትሰጥ ምላሽ መስጠቷ ነው የተሰማው።

ሁለቱ አገሮ አንዳቸው በሌላኛው ላይ አማጺ ላለማደራጀትም መሆን ነጻ መሬት መስጠት የሚከለክል የቆየ መግባባት ቢኖራቸውም በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኬንያን እንደ መሸጋገሪያና ሎጂስቲክ ማደረጃ መጠቀም የተለመደ ሆኗል። ከኢትዮጵያ በኩል በተደጋጋሚ በዚህ ጉዳይ ንግግር የተደረገ ሲሆን አሁን ላይ ኬንያ ፍጹም ተባባሪ እንደምትሆን፣ ድንበሯ ላይ ቁጥጥር እንደምታካሂድ በይፋ ለመንግስት አስታውቃለች።

ትህነግ ያደራጀውና በቅርቡ ድምጹ የተሰማው የሶማሌ ረዚስታንስ ( አማጺ) ዋና መቀመጫውን ኬንያ ማድረጉና በስምና በስልጣን የሚታወቁ ጥቂት የክልሉ ተወላጆች ናይሮቢ ሄደው ድርጅቱን በይፋ መቀላቀላቸው ሲገለጽ እንደነበር ይታወሳል። ይህ አማጺ የቀድሞ የሶማሌ ክልል መሪ አብዲ ኢሌ ዘመዶችና ወዳጆች የሚሳተፉበት ሲሆን፣ ዋናዎቹ አመርሮቹ ቱርክ መሆናቸው ይነገራል።

የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሙስጣፌ ኡመር በክልሉ ካላቸው ተቀባይነት አንጻር ድርጅቱ ብዙም መራመድ እንደማይችል አቅሙን የሚያውቁ ይናገራሉ። ሆኖም ግን ገና ሳይደራጅና ሰንኮፉ ሳይረዝም ለመቆጣጠር ሰፊ ስራ እየተሰራ መሆኑንን የዜና ባለቤቶች ገልጸዋል። በናይሮቢ በኦሮሞ ስም የሚንቀሳቀሱ ደርጅት አመራሮች ( የተዋጊዎች መሪዎች) ኬንያ ድንበር አላይ እንደሚገኙ በተደጋጋሚ ሲገለጽ ነበር።

ይህ በንዲህ እንዳለ የትግራይ ነጻ አውጪ ወራሪ ሃይል ደብረ ሲና ሲደርስ ተዘርግቶ በነበረው የተቀነባበር ሴራ በድንገት ወደ ሚዲያ ወጥተው በትህነግ መሪነት የሽግግር መንግስት ለማቋቋም ማቀዱን ይፋ ያደረገው ህብረት መፍረሱ ተሰማ። በአሜሪካ ዕውቅና ሰጪነት የተሰባሰቡት ግለሰቦች ራሳቸውን ድርጅት በማድረግ ከወጡ በሁዋላ ለድጋሚ መግለጫ እንኳን እንዳልበቁ ያስታወሱት በቅርብ የሚያውቋቸውና በዙም ስብሰባ የሚከታተሏቸው ናቸው።

“ፕሮፌሰር ሕዝቄል በሚመሩት የዙም ስብሰባ በግል እንጂ በድርጅት ደረጃ የሚሰበሰብ የለም” ያሉት የመረጃው ሰው፣ “እንደ ድርጅት ኦነግ ሸኔና ትህነግ እንጂ ሌሎቻችን በግል ነው ስብሰባ የንጠራው” ብለዋል። በትህነግ በኩልም ካናዳ ያሉት አቶ ዮሃንስ እንጂ ሌላ የሚገኝ ሰው እንደሌለ፣ ስብሰባውም በሁለት ሳምንት አንዴ ለመረጃ ልውውጥ የሚደረግ እንጂ እንደ ጥምር ድርጅቶች የሚሰራ ምን ነገር እንደሌለ አመልክተዋል። ፕሮፌሰሩ ከአምብሳደር ብረሃነ የሚሰታቸውን መመሪያ በመቀበል መረጃ እንደሚሰጡ ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል። የመረጃው ባለቤት ደጋግመው ” ..ስብስቡ እንደ ድርጅት የሚሰራው ስራ የለም። ሁሉም በግል ነው የሚወከለው። አጀንዳና መመሪያ የሚመጣው ከትህነግ ነው። እኛ ማለት ልክ እንደ ድሮው ኢህአዴግ በውጭ የምንኖር ዲጂታል አጋር ድርጅቶች ነን” ሲሉ ቀልደዋል። “ለምን ታዲያ አትወጡም” ለተባሉት ” እዛ በመሆኔ መረጃ ተገኘ” ሲሉ በይፋ ራሳቸውን ገልጸው እንደሚናገሩ አመልክተዋል።

ዘጠኝ የሚሆኑ ፀረ መንግሥት ድርጅቶች ከህወሃት ጋር መጣመራቸውን ቀድሞ ሮይተርስ ነበር ያስታወቀው። ሮይተርስን ተከትሎ ቪኦኤ ሰፊ ሽፋን የሰጣቸው  

የትህነግ ወደ ደብረሲና መምጣት ስጋት እንደሆነባት በመጥቀስ ሁሉም ወገኖች ተኩስ እንዲያቆሙ እየገለጸች በሌላ በኩል ልዩ ሳሎኗን ከፍታ “ጥምረት” ለተባለው ብዙም የማይታወቁ ሰዎች ስብስብ እውቅና ስትሰጥ የነበረችው አሜሪካ ድርድርም እየጠየቀች ነበር።

ቪኦኤ “ዘጠኝ የሚሆኑ ጸረ- መንግሥት ቡድኖች ዋሺንግተን ዲሲ ውስጥ ዛሬ ከህወሃት ጋራ በመሆን መንግሥትን ለመጣል ጥምረት እንመሰርታለን ማለታቸውን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል” በሚል መዘገባቸው ይታወሳል።

ለዚህ ዜና አስተያት እንዲሰጡ የተተየቁት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ቃል አቀባይ ቢልለኔ ስዩም ሮይተርስን “ከዚህ ቀደም በትዊተር ገጼ የጻፍኩትን ተጠቀም” ሲሉ ስብስቡን እንደ ስብስብ ለመቁጠር እንደሚችገሩ አመልክተው ነበር። “ከሦስት ዓመታት በፊት የተከፈተው የፖለቲካ ምህዳር ለተቀናቃኞች ልዩነታቸውን በምርጫ ኮሮጆ በሰኔ 2013 ዓ.ም እንዲፈቱ ዕድል ፈጥሯል” ሲሉ ድርጅቶቹ የነበሩ ቢሆኑ ኖሮ እድሉን ከመተቀም የሚያግዳቸው ምንም ምክንያት እንደማይኖር አመላክተው ነበር።

“ይህ በሆነ በቅጽበት የጦር ሚዳው ውሎ መልኩን በመቀየሩና ትህነ ተኩስ ማቆም፣ ድርድር ጠያቂና ሰላም ሰባኪ መሆኑንን ተከትሎ ነው ስብስቡ ሳይጸና የተበተነው” ሲሉ መረጃ የሰጡን አመልክተዋል።


Leave a Reply