የዛሬው “የከፋፍል ዘመቻ” ዕቅድ ከወር በፊት ይፋ ሆኖ ነበር

የጁንታው ምንደኞች ቀጣይ አጀንዳዎች‼️ ከወር በፊት የከፋፍለህ ዘመቻ ዕቅድ መያዛቸውን፣ በእቅዱ መሰረት ይህንኑ ለመተግባር መዋቅርና ስልት ነድፈው እንደነበር ሴራውን የሚያውቅ አስታውቆ ነበር። ( ከአንባቢ የተላከ)

December 8

በአማራ ብሔርተኝነት ስም ለልደቱ አያሌው ጭምር ጥብቅና ሲቆሙ የምናውቃቸው ሰርጎ ገብ የህወሓት ምንደኞች በቀጣይ ሰባት ከፋፋይ አጀንዳዎችን ለማራገብ ዝግጅታቸውን በማጠናቀቅ ላይ መሆናቸውን ባደረግነው ክትትልና ጥልቅ ጥናት ተገንዝበናል፦ በእቅዳቸው መሠረት

1) “የፌድራል መንግስቱ አማራን ክዶታል” የሚለው አጀንዳ በአዲስ መልክ ይራገባል (ዝርዝር አጀንዳ ቀረጻውን ከመግለጽ እንቆጠባለን)፣

2) “የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አማራን ክዶታል” የሚለው አጀንዳ በአዲስ መልክ ይራገባል (ዝርዝር አጀንዳ ቀረጻውን ከመግለጽ እንቆጠባለን)፣

3) በአማራ ብልጽግና እንዲሁም በአማራ ክልል መንግሥት አመራሮች መካከል “የጀግናና ተለላኪ” ትርክት በመፍጠር ልዩነት እና መጠራጠር ለመፍጠር ይሰራሉ (ዝርዝር አጀንዳ ቀረጻውን ከመግለጽ እንቆጠባለን)፣

4) የትህነግ ነጭ ለባሽ የሆነው ይኸ ቡድን አስቀድሞ በማኀበራዊ ሚዲያና በሌሎች መንገዶች ውስጥ ለውስጥ ሲያራግበው ለነበረው “#የፈጠራ_ድርሰት” ተከላካይ ሆኖ ብቅ ይላል (ዝርዝር አጀንዳ ቀረጻውን ከመግለጽ እንቆጠባለን)፣

5) የሽብር ቡድኑ አስቀድሞ ሲያራግበው የቆየውና በኋላ እርግፍ አድርጎ የተወውን (መቼ? እና ለምን? አቆመው ለሚሉ ጥያቄዎች ሰፊ ሐተታ ይኖረናል) “ወሎ ተክዷል” የሚል ሙሾ በአዲስ መልክ ይቀርባል (ዝርዝር አጀንዳ ቀረጻውን ከመግለጽ እንቆጠባለን)፣ ፣

6) በአማራ ክልል ሕዝብ በተለይም በአማራ ሕዝባዊ ሠራዊት (የአማራ ልዩ ሃይል፣ የአማራ ሚሊሻና ፋኖ) መካከል ክፍፍል የሚፈጥሩ አሉባልታዎችን በስፋት ይነዛል (ዝርዝር አጀንዳ ቀረጻውን ከመግለጽ እንቆጠባለን)፣

7) “የፌድራል መንግሥት እንዲሁም የአማራ ክልል መንግሥት #ለወልቃይት የሰጡትን ትኩረት ለሌሎች አካባቢዎች አልሰጡትም” የሚሉና ተየያዥ አሉባልታዎችን በስፋት ይነዛል (ዝርዝር አጀንዳ ቀረጻውን ከመግለጽ እንቆጠባለን)፣
የሽብር ቡድኑን ነጭ ለባሾች የኀቡዕ መዋቅር በመበጣጠስ ኢትዮጵያ አሸንፋ እንድትወጣ ማድረግ የአገር ወዳድ ዜጎች የውዴታ ግዴታ ነው


Leave a Reply