ትህነግ ያፈረሰውን የጀግኖች ልጆች ማብቂያ ተቋም በቋሚነት ለመርዳት ዲያስፖራዎች ቃል ገቡ

በአገር ሕልውና ማስከበር ዘመቻው ጉዳት የደረሰባቸው የሠራዊት አባላት ልጆችን በተደራጀ መልኩ በዘላቂነት ለመደገፍ እንቅስቃሴ መጀመሩን የብሔራዊ ጀግኖችና ህፃናት አምባ ገለፀ፡፡የዲያስፖራ አባላት አምባውንንና ወገኖቻእውን ለመርዳት ቃል ግብተዋል። እሃላም ፈጽመዋል።

የብሔራዊ ጀግኖችና ህፃናት አምባ ከተለያዩ አገራት ከመጡ የዳያስፖራ አባላት ጋር የተሰዉና የቆሰሉ የሠራዊት አባላት ልጆችን በዘላቂነት መደገፍ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክሯል፡፡በውይይቱ የሠራዊት ግንባታ ስራዎች ዋና አስተባባሪ ጄኔራል ባጫ ደበሌ፤ የቀድሞ ጦር ሠራዊትና የብሔራዊ ጀግኖችና ህጻናት አምባ የቦርድ አባል ብርጋዴር ጄኔራል ካሳዬ ጨመዳ፣ የቦርዱ ሰብሳቢ ዶክተር አዳሙ አንለይ እና የዳያስፖራ አባላት ተሳትፈዋል።

ጄኔራል ባጫ ደበሌ ኢትዮጵያ የገጠማት ጦርነት በጦር መሳሪያ ብቻ ሳይሆን በዲፕሎማሲና በኢኮኖሚ ትግል ጭምር የሚፈታ መሆኑን ተናግረዋል።ኢትዮጵያ የውስጥና የውጭ ጠላቶች ተቀናጅተው የከፈቱት እንደዚህ አይነት ጦርነት በታሪኳ ገጥሟት አያውቅም ያሉት ጄኔራሉ፤ በአገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን “እኛ እያለን ኢትዮጵያ አትበተንም” በሚል መንፈስ በጋራ ቆመው ድል ማድረጋቸውን ገልጸዋል።ሕብረተሰቡ ከሠራዊቱ ጎን በመቆም ‘አዲስ አበባ እገባለሁ’ ብሎ ሲፎክር የነበረውን አሸባሪ ቡድን በወረራ በያዘው መሬት እንዲቀበር ከፍተኛ አበርክቶ እንደነበረው አንስተዋል።

ዳያስፖራው በዲፕሎማሲና በኢኮኖሚ ግንባር በመዋጋት ረገድ አኩሪ ገድል እየፈጸመ መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህን ተግባር አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት የመጨረሻ ምሽግ የሆነውን የመከላከያ ሠራዊት መደገፍ ደግሞ ከሁሉም ዜጋ የሚጠበቅ ኃላፊነት ነው ብለዋል ጄኔራል ባጫ።

ከዚህ አኳያ በሕልውና ዘመቻው ለተሰዉና ጉዳት ለደረሰባቸው የሠራዊት አባላት ልጆች ትምህርት ቤት አቋቁሞ ለመደገፍ የተጀመረውን እንቅስቃሴን አድንቀው ስራው በፍጥነት እንዲጀመር ጠይቀዋል፡፡”እኛ ኢትዮጵያዊያን በአንድነት ከቆምን የትኛውም አይነት ጠላት አይደፍረንም” ያሉት ብርጋዴር ጄኔራል ካሳዬ ጨመዳ በበኩላቸው፤ አንድነታችንን በመጠበቅ ሠራዊቱን ልንደግፍ ይገባል ብለዋል።

የብሔራዊ ጀግኖችና ህፃናት አምባ የቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር አዳሙ አንለይ ለአገር ዳር ድንበር መከበር መስዋዕትነት እየከፈለ የሚገኘውን ሠራዊቱ ቤተሰብ መደገፍ ተገቢ ነው ሲሉ ተናግረዋል።ለዚህ ደግሞ የጀግኖች አምባ እና ህፃናት አምባ በሚል በሁለት መንገድ ሠራዊቱን ለመደገፍ የሀብት ማሰባሰብ ስራ እየተሰራ መሆኑንና ተጠናክሮም እንደሚቀጥል ገልጸዋል።የዳያስፖራ አባላትም ወደ አገር ቤት የመጣነው ብሔራዊ ግዴታችንን ለመወጣት በመሆኑ በሚያስፈልገው ሁሉ የበኩላችንን ሚና ለመወጣት ቁርጠኞች ነን ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል። በምስል በተላለፈው ዘገባ እንደታየው የዲያስፖራ አባላቱ ቃላቸውን ጠብቀው የሚቻላቸውን ሁሉ ላምድረገና ተከታታይ መዋጮ ለማስገባት ቃለ መሃላም አድርገዋል። ሕሳናት አምባና የጅግኖች አምባን ትህነግ እንዳፈረሰውና በውስጡ የነበሩትን እንደበተናቸው ይታወሳል።

Leave a Reply