የጧፍና የፓለቲካ ወዳጆች “ቡጥቡጥ” – እምኑኝ መጨረሻችን አያምርም…

በጣም የሚገርመው በመዋቅርና በመርህ የምትመራ ስርዓት አስተማሪ ንግግር አዋቂ እውቀት ጨማቂ፤ ከሰማይ የሰፋች በእውቀት የጠለቀች የማትመረመር ምጡቅ ረቂቅ የሆነች ቤተክርስቲያን በግለሰቦች ልክ ተሰፍታ የምትታይ የምትገለጥ የምትታወቅ አድርጎ መሳል ተገቢ አይደለም።

ይህማ የመስቀል አደባባይ ጉዳይ ሳይሆን የመሰቃቀያ አደባባይ ብለን ብንጠራው ይሻላል ጠላት ወዳጅ ያደረገ የፍቅር ጥግ የአምላክ ፍቅር ሕዝብና አሕዛብ አንድ ያደረገውን መስቀል እየጠሩ የመስቀሉ ድህነት ያልደረሰው የሲዖል ሟሟሻ እንደሆነ ይሁዳ መሆን መምሰል ጥሩ አይደለም።

ክርስቶስ ከተከተለው ከመምህርነት አልፎ ደቀ መዝሙር ከነበረው ከገንዘብ ወዳጁ ከአይሁድ በምን ተሻላችሁ? ክርስቶስን መከተል ሳይሆን ክርስቶስ መሆን ይገባችዋል ።

ክርስትና በስሌትም ሆነ በስሜት አትመራም ክርስትና በእምነት በድፍረትና በመንፈስ ቅዱስ አይል ትመራለች አባቶቻችን የመሯትም በእዚህ ነው የቤተክርስቲያን ፈተና ሲመጣ ቅዱስ ሲኖዶስ ተሰብስቦ አስቦና አስልቶ ፀልየው ሱባዬ ገብተው አስተሳሰባቸውን በፀሎት ፤ጉልበታቸው በመልካም ንግግር አብርደው ያሸንፋሉ ።

ቤተክርስቲያን በደሏን ሆነ ጉዳቷን የምታወራበት ልሳን አላት ልሳንዋ ቅዱስ ሲኖዶስ እንጂ ግለሰቦች አይደሉም በማንኛውም መንገድ ወጣቶቹን ማንቃት መምከርና የተሻለ አሳብ ይዞ ማቅረብ እንጂ በመጠላለፍ እና በመነቃቀፍ የሚጠቀም ጠላት እንጂ ማንም ኦርቶዶክሳዊ አይኖርም።

ሁለቱም ጋር ድክመት አለ ግን ሁለቱም ጋር እምቅ አይልም አለ ለቤተክርስቲያን ያስፈልጋሉ የሁለቱ ጥል አይደለም ያስገረመን ጥልማ ጰጥሮስና ጳውሎስም በመንፈሳዊ ቅናት ተጣልተዋል የሚገርመው ጥላቸውን የሰሙ ወይም ያዩ የሁለቱ ባልንጀራ ሰባኪያን አልያም ጳጳሳት ሽማግሌ ሆነው አላመገላገላቸው ነው።

መቼም ለምሕረት አብ መካሪ ማን ነው ከተባለ ቅድሚያ የሚጠራው ወንድሙ ዘመዴ ነው የሁለቱ ጥል የአንድ አካል የተለያየ ብልት እንጂ የተለያዩ አካላት አይደሉም የሁለቱም ንትርክ ሆነ ትችት እንደ አንድ አካል ጉዳት መላ አካልን እንደሚያውክ እንዲው ሁላችንም በክርስቶስ አንድ አካል ነንና እንታወካለን።

የምሕረት አብ ጧፍ አቢሪና የዘመዴ ጦመረኛ ጎራ ከፍለው ሲነታረኩ ሲሰዳደቡና ሲበሻሸቁ ስናይ ስህተቱ የምዕመናኑ ሳይሆን የሁለቱም ድክመት ስህተት እንደሆነ ተረድተናል የሚከተሏቸው ሁሉ ተሳዳቢ ፤ስሜታም ፤ወረተኛ ወሬ ቃርሚ ሆነው የተሰሩ እንጂ ክርስትና የተሰበኩ እንዳልሆኑም አውቀናልም።

ይህ ምዕመን ነው ታዲያ ለእዚህቺ እምነት ጠበቃ አለኝታ በክፉ ጊዜ ደራሽ የሚሆነው ?

ሰባኪ ማለት የተለወጠ ማንነት ያለው ሆኖ የሚለውጥ ካልሆነ ይህ መንፈሳዊ ድርሰት በመድረክ ላይ በተዋበ ቃላት ባማረ ስቴጅ ላይ ቆሞ የሰውን ልብ በሚፈልጉት ልክ ማርኮ የሚያስደስት ድራማ ነው ብለን የምንወስደው።

የበራ ጧፍ ይዘን የጨለመ ሕይወት ካለን በሃይማኖት ካፓ ፓለቲካ ከተጫወትንም እምኑኝ መጨረሻችን አያምርም።

ብቻ ምንም ይሁን ምንም ለቤተክርስቲያን እውነት የቆመ መቼም አይወድቅም የተቀባ የሚያስመስል አንድ ቀን ይወድቃል አወዳደቁም የከፋ ነው ወደ ላይ በወጣን ቁጥር አወዳደቃችን የከፋ ነው የሚሆነው ትምክህት ትቢት ማን አለብኝነት ልናሶግድ ይገባል።

በሰው ትከሻ ላይ የተደገፈ ሰው ያ ሰው ሲደክም አብሮ ይወድቃል የሚሻለው በእግዚአብሔር ትከሻ ላይ ተደግፎ ለዘላለም ፀንቶ መቆም ነው የሚገባን የሰው ቲፎዞ መሆናችን በራሱ ለጠላት ደካማ ጎናችንን እንደመንገር ውዳቂ መሆናችንን እያሳወቅን መሆኑን ማወቅ አለብን።

እኛ ያልተስማማን ከመንግስት ጋር የሚያስማማን ምን ጉዳይ አለ? ሰው ከራሱ ጋር ተጣልቶ እንዴት ሌላውን ሊያስታርቅ ይችላል? እና ጥሉን ለጊዜው ተወት አድርገን ልዩነታችን ወደ ጎን አድርገን የገጠመንን ፈተና በጋራ እንወጣው ጥሉ ቤት ዘግተን እንጣላዋለን ይደርሳል።

ህብረታችን ነው የሚያምረው አንድነታችን ነው ነው የሚያሸንፈው ፍቅራችን ዓለምን ያሸንፋል ባለማህተቦቹ ሁላችን በፍቅር ሲሆን ክር አሳሪ ለጠላ ለባሽ የክርስቶስ ወታደር ሆነን ጠላትን በስሙ እናሸንፋለን፤

ከስሜትም ከስሌትም ወጥተን ወደ አባቶቻችን ጳጳሳት ከቅዱስ ሲኖዶሱ ጋር በማበር የሚሰጠንን ተልኮ ከተወጣን ከተናበብን እንኳን መስቀል አይደባባይ ይቅርና ኢትዮጰያን የማን ሆና ነው ሀገር መሆናችንን በተግባር እናስመሰክራለን።

በመጨረሻም – ፀሎቴም ፦ ዘመዴም ስር ከሰደደ ፓለቲካ ምሕረት አብንም በስሜት ልክ ያጣ ጧፍ ማብራቱን ቢቀንስ በዓላትን ቢያንስ ጠብቆ ቢያደርግ ወጣቱን ይዞ የሚያፀና ሰባኪያ ወንጌል አብሮ ቢሳትፍ የምንጊዜም ምኞቴ ነው።

Via – የሰሚ በዕለቱ ወይን አምባ ቅዱስ ገብርኤል page

Leave a Reply