ትህነግ እየጎመዘዘው እንዲውጠው የቀረበለት የአብይ አሕመድ የመጀመሪያ ስጦታ “ሰራዊትህን በትን”

አሁን ላይ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ፣ እንዲሁም አገልግሎት አልባ መሆን የትግራይ ክልል ልዩ አጀንዳ ሆኖ በስፋት እየተሰማ ነው። የጦርነት ዝግጅት ስለመኖሩ ቢነገርም በመንግስት ወገን “ተራ ግጭት” በሚልና በቂ የአጻፋ ዝግጅት እንዳለም ይነገራል። በትህይነግና በትህነግ ወዳጆች በኩል ግን ማህበራዊ ቀውስ እጅግ ገኖና ሰፊ መልክ ይዞ እየተገለጸ ይገኛል።

“አፈገፈኩ” ቢልም በሽንፈት ከጥቃት የተረፈና የተበታተነ ሃይሉን ይዞ ወደ ትግራይ ተመልሷል የሚባልለት የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር አመራሮች ተተኳሽ በመጨረሳቸውና ካሁን በሁዋላ የመዋጋት አቅማቸው ስለተዳከመ አሜሪካ በይፋ አመራሮቹ እጅ እንዲሰጡ ጥሪ በማቅረብ ጦርነቱ እንዲቆም በይፋ ለኢትዮጵያ ሰላም ያላትን ተባባሪነት ልታሳይ እንደሚገባ የተገለጸው በማስረጃ ነው። ይህንኑ ተከትሎ ” የትህነግ አዋላጅ” የሚባሉት ኽርማን ኮሆን ” ምህረት ይደረግላችሁና አገር ለቃችሁ ውጡ” የሚል የመጨረሻ ምክራቸውን ሰንዝረዋል። ብርቅርብ የሚያውቋቸው “የማይጨበጡ” ሲሉ የሚገልጿቸው አምባሳደር ዴቪድ ሼን አሜሪካ ምንም አይነት የአቋም ለውጥ እንዳላደረገች ገልጸው ቢናገሩም ከትህነግ ሰዎች የእርቅና የድርድር ጥያቄ በተደጋጋሚ እየተሰማ ነው።

በአትላንቲክ ምክር ቤቱ የአፍሪካ ማዕከል ተመራማሪ የሆኑት ብሮንዋይን ብሩተንና የባልሲሊ ዓለማቀፋዊ ጉዳዮች ትምህርት ቤት ሊቀመንበርና የዓለም አቀፍ ደኅንነት ፕሮፌሰር አን ፊትዝ ጀራልድ ፖሊሲ አውጪዎችና ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ዘንድ ተነባቢነት እንዳለው በሚነገርለት የፎሬን ፖሊሲ መፅሄት ላይ ባወጡት ፅሑፍ ነው ለጆ ባይደን የትህነግ አመራሮች እጅ እንዲሰጡ ጥያቄና ምክረ ሃሳብ ሲያቀርቡ በአመክንዮ አስደግፈው ነበር። ከልምድ እንደሚታወቀው ተቋሙ ዝም ብሎ አይጽፍምና እነሱ ይህን ሃሳብ ባቅረቡ ቀናት ውስጥ፣ ጆ ባይደን ለተቅላይ ሚኒስትር አብይ ስልክ መደወላቸው የተነጋገሩት ቃል በቃል ባይታወቅም አንድ ነገር እንዳለ አመላካች ሆኗል።

ከቀድሞ የትህነግ መሪ አቶ ስብሃት ነጋ ጋር ስድስት አቅማቸው የደከሙ የተባሉ መፈታታቸውን ተከትሎ የቀድሞ የናይጀሪያ ፕሬዚዳንት መቀለ ሄዶ መመለስ፣ የጆ ባይደን ተደጋጋሚ የስልክ ውይይት እንደሚደረግ መጠቆምና አሜሪካ ሰላም እንዲሰፍን አብዝታ እንደምትሰራ በይፋ ማስታወቋ በቅርቡ ” በግድ የሚዋጡ” አለያም ” የሚያስፈነጥዙ ዜናዎች” እንደሚሰሙ እሙን ነው። በርካቶች እንደሚሉት ሕዝብ እየተሰቃየ የፖለቲካ ቁማር በሁሉም ወገን ሊቆም ይገባል። ተፈለገም አልተፈለገም በድፍረት እርምጃ ተወስዶ ሰላም እንዲወርድ መሰራት አለበት።

የትግራይ ሕዝብም ሆነ ሌላው ሕዝብ ከዚህ በላይ ችግርና የፖለቲካ ሴራ መሸከም ስለማይችል በሁሉም ረገድ ለሰላም አስፈላጊው ሁሉ መደረግ እንደሚኖርበት የሚያምኑ እንደሚሉት ኬንያ ላይ እንዳንድ የሰላም ሂደቶች ተጀምረዋል። አካሄዳቸው እጅግ ጥንቃቄ የተመላበት በመሆኑ ይፋ ባይደረግም፣ ትህነግ ሰራዊቱን ካላፈረሰ መንግስት አንድ ስንዝር እንደማይነቃነቅ በሁሉም አደራዳሪ ወገኖች ዘንዳ አሜሪካንን ጨምሮ ታምኖበታል።

በአንድ አገር ውስጥ ሁለት የመከላከያ ሃይል ሊኖር እንደማይገባ፣ ትግራይ ልክ እንደሌላው ክልል በመከላከያ ውስጥ በልኳ ትወከላለች እንጂ ታንክና መድፍ የታጠቀ ሃይል ይዞ ወደ ድርድር ለመምጣት እንደማይቻል መንግስት የያዘውን ቁርጠኛ አቋም ኦባሳንጆ እያግባቡበት ያለና አሜሪካ የምትደግፈው እንደሆነ ስለ ጉዳዩ የሚያውቁ ገልጸውልናል። መንግስት “ድርድር” ያለው እንዴትና ከማን ጋር፣ በምን አግባብ እንደሆነ ግልጽ ባይቀመጥም፣ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ቅድሚያ ያቀረቡት ቅድመ ሁኔታ “ትህነግ ሰራዊቱን ትጥቅ ያስፈታ፣ ይበትን” የሚል እንደሆነ ታውቋል። ይህ ጥያቄ ትህነግ ስጋት እንዳይሆን የሚያደርግና ሰሎአም የሚያሰፍን እንደሆነ አሜሪካም አምናለች። የሁሉም ጉዳይ ቁልፍ ያለው እዚህ ነጥብ ላይ ስለመሆኑ ስምምነት መኖሩን ዜናውን የሰጡን ገልጸዋል።

This image has an empty alt attribute; its file name is Ann-and-Bruton-1024x576.jpg

ለመረጃ ይረዳ ዘንድ ይህን አካሄድ አስቀድመው የተረዱት፤ በአትላንቲክ ምክር ቤቱ የአፍሪካ ማዕከል ተመራማሪ የሆኑት ብሮንዋይን ብሩተንና የባልሲሊ ዓለማቀፋዊ ጉዳዮች ትምህርት ቤት ሊቀመንበርና የዓለም አቀፍ ደኅንነት ፕሮፌሰር አን ፊትዝ ጀራል አስቀድመው የጻፉትንና እኛ ያተምነውን ከታች አቅርበን ነበር።

ምንም እንኳን አሜሪካ ለአሸባሪ ቡድኑ ህወሃት በማድላት ሥህተት ሥትፈጽም ብትቆይም አሁንም ለሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ማብቃት አዎንታዊ ሚና ለመጫወት ያላት ዕድል  እንዳልተሟጠጠ የሚያትተው ጽሁፍ የተሰራጨው የትህነግ ወራሪ ሰራዊት መሪ ጻድቃንና የኖርዌይ ተወላጅ የሆኑት ፕሮፌሰር ሺትል ትሮድቮል በተከታታይ የሰላም ጥሪ በያዘና “ከቃል ያለፈ ድጋፍ አልተደረገም” በሚል የትጥቅ ድጋፍ በጠየቁበት ተመሳሳይ ወቅት መሆኑ ጽሁፉን ሰፊ መነጋገሪያ አድርጎታል። ምሁራኑ በጽሑፋቸው ከአራት ዓመት በፊት ለ27 ዓመታት ሲገዛ በነበረው አንባገነኑ የህወሓት ቡድን ላይ ህዝባዊ አመጽ እንደተቀሰቀሰና አገዛዙ እንደተገረሰሰ አስታውሰዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ወደ ማዕከላዊ ሥልጣን ከመጡ በኋላ ምንም እንኳን በህወሓት ታፍነው የቆዩ የብሄር ተኮር ጥያቄዎች እዛም እዚህም እየፈነዱ ሀገሪቷ ባትረጋጋም በርካታ ማሻሻያዎች አድርገው የዜጎችን ጥያቄዎች በልካቸው ለመመለስ እንደሰሩ ትዝብታቸውን አኑረዋል። “ነገር ግን” ይላሉ ጸሐፊዎቹ ምንም እንኳን አሸባሪ ቡድኑ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን መንግስት “አልቀበልም” ብሎ በማመጽ ወደ ትግራይ ሄዶ ቢመሽግም  ቡድኑ ቀደም ብሎ በዘረጋው የእንደራሴዎቹ ሠንሠለት የሀገሪቷን ኢኮኖሚ እና የመከላከያ ኃይል መልሶ ለመቆጣጠር ሰርቷል ብለዋል። የውክልና ሥራውን ለማስፈጸምም ከሀገሪቷ የዘረፈውን በቢሊየን ዶላሮች የሚቆጠር ሐብት ጥቅም ላይ እንዳዋለ አንስተዋል፡፡

በወቅቱ አብዛኞቹ ምዕራባውያን በለውጡ ሲደሰቱ አንዳንዶቹ ግን ከህወሓት ጋር ወታደራዊ ግጭት ሊፈጠር እንደሚችል ሲናገሩ እንደነበርም ጽሁፉ ያወሳል፡፡ ጸሐፊዎቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከኤርትራ ጋር ሠላም መፍጠሩ ለኖቤል የሠላም ሽልማት እንዳበቃቸው፣ በሀገራቱ መካከል ለሁለት አሥርት ዓመታት አኮራርፏቸው የዘለቀው የድንበር ጉዳይም በዕርቁ መፈታቱ ህወሓትን እንዳስኮረፈውና ጥግ እንዳስያዘው፣ ህወሓት በኤርትራ ድንበር አቅራቢያ ያሰፈራቸውን ኃይሎች ትጥቅ እንዲያስፈታ መንግስት ቢጠይቅም አሻፈረኝ እንዳለ፣ ይህም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ራስ ምታት ሆኖ መቆየቱን ዘርዝረዋል፡፡

ጽሑፉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሠላምን ለማስፈንና ዕርቅ ለመፍጠር በርካታ የዕርቀ-ሠላም ልዑካን ወደ ትግራይ ቢልኩም በአሸባሪው የህወሓት ቡድን እብሪት እንዳልተሳካ አመላክቷል። አክሎም ዐቢይ አህመድ በርካታ የህወሓትን ባለሥልጣናት ማንሳቱ፣ በተለይም የወታደራዊውን ማዕከላዊ ዕዝ በፈለጋቸው አመራሮች መተካቱና በትግራይ ተወላጆች ቁጥጥር ሥር ብቻ የነበረው የዕዝ ሠንሠለት በበርካታ ብሄሮች ስብጥር እንዲዋቀር መደረጉ እንዳስደነገጣቸው፣ እንዳስኮረፋቸውና ወደ ጦርነት ለመግባት መስማማት ላይ እንዳደረሳቸው ገልጸዋል። የሰሜን ዕዝ ላይ የተከፈተው ጦርነትም የዚሁ አካል እንደሆነ አመልክተዋል።

የትግራይ ባለሥልጣናት በሰሜን የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ዕዝ ላይ የፈጸሙት “መብረቃዊ ጥቃት” ጦርነትን ቀስቅሷል ሲሉ ያስታወቁትና በኢትዮጵያ ጉዳይ በቂ መረጃ ያላቸው ሁለቱ ጸሃፊዎች፣ አሸባሪው የህወሓት ቡድን ከዚህ ጥቃት በኋላ የአማራን ዘር ለማጥፋት በሚመስል መልኩ በማይካድራ በበርካታ መቶዎች የሚቆጠሩ አማራዎችን መጨፍጨፉን አግለጠዋል።

የምዕራባውያኑ መገናኛ ብዙኃንም ጭፍጨፋውን በማነሳሳቱ ረገድ መንግስት ተጠያቂ መሆን እንዳለበት እንዲሁም በትግራይ ላይ የዘር ማጥፋት እንደፈጸመ አድርገው አጀንዳ በመቅረጽ መሥራት መጀመራቸውን ብሮንዋይን ብሩተን እና አን ፊትዝ-ጀራልድ በጋራ ባወጡት ጽሑፍ አሳይተዋል። መገናኛ ብዙኃኑ ከህወሓት ባልተናነሰ ለአሸባሪው ሸኔም እውቅና በመስጠት ከተገፋው ህወሓት ጋር በማበር የኦሮሞን ህዝብ ከጭቆና ነጻ ለማውጣት በጋር እየሠሩ መሆናቸውን ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ለማሳመን ሲሰሩ መቆየታቸውን ጠቅሰዋል። ከመገናኛ ብዙኃኑ በተጨማሪ ዓለምአቀፍ የዕርዳታ ድርጅቶችም ህወሓትን ሲደግፉ መቆየታቸው ይፋ አድረገዋል።

አሁን አሁን አሸባሪው የህወሓት ቡድን እየተዳከመ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ መገናኛ ብዙኃኑ ጉዳዩን እንደ ቀድሞው ከማራገብ ጋብ ብሏል ሲሉ ሐፊዎቹ ምልከታቸውን በታዋቂው መጽሄት ላይ አስፍረዋል።

ፀሃፊዎቹ የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ያለምንም ምክንያት የአሸባሪ ቡድኑን ህወሃት ወንጀል ለመሸፈን በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ብቻ ያነጣጠረ ቅጣት እየጣለ መቆየቱን አንስተዋል።

ምንም እንኳ ጦርነቱን የቀሰቀሰው፣ ከሰሜን እዝ የጦር መሳሪያን ዘርፎ እና ቁጥሩ አያሌ የሆነ ሚሊሻ ያሰለፈው ህወሃት ሆኖ ሳለ የምእራቡ ዓለም መገናኛ ብዙሃን የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መንግስትን የጦርነት ቀስቃሽና ፈላጊ አድርገው መሳላቸውን ነው አጉልተዋል። በዚህ መልኩ ዩናይትድ ስቴትስ ለህወሃት በማድላት ለአሸባሪ ቡድኑ የፖለቲካ ድጋፍ መስጠቷን በመጠቆም ስህተት መፈፀሟን አመልክተዋል።  የባይደን አስተዳደር ይህንን የተሳሳተ አካሄዱን በማረም የሰሜን ኢትዮጵያን ግጭት በማቆሙ አወንታዊ ሚና ለመጫወት አሁንም እድል እንዳለው መክረዋል።

ህወሃት ከአማራ እና አፋር ክልሎች ተሸንፎ መውጣቱን የሚያነሱት ፀሃፊዎቹ፥ ይህ ቡድን በተተኳሽ እጦት እና በሎጀስቲክ ድርቅ ምክንያት ምንም ወታደራዊ ስኬት የማየት እድል የለውም ባይ ናቸው።

እናም ዩናይትድ ስቴትስ ቁልፍ የህወሃት አመራሮች እጃቸውን እንዲሰጡ በይፋ በመጠየቅ፥ ለዚህ የሽብር ቡድን ምንም ድጋፍ እንደሌላት ለኢትዮጵያ ህዝብ ልታሳይ እንደሚገባ አመልክተዋል።

እነዚህ ቁልፍ የህወሃት አመራሮች ሰላምን በመምረጥ እጅ ለመስጠት ፈቃደኛ ካልሆኑም በውጭ ዓለም የተከማቸ ሀብት እና ቤተሰብ ባላቸው በእነዚህ የህወሃት መሪዎች ላይ ማእቀብ ልትጥል እንደሚገባ ገልፀዋል።

አሜሪካ አጀንዳዎቿን የሚያስፈጽሙ መገናኛ ብዙኃን፣ የእርዳታ ድርጅቶች በሰብዓዊነት ስም የሚንቀሳቀሱ ካውንስሎች እና ኤጀንሲዎች፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦቿን ጋብ እንዲሉ በማድረግ እና አሸባሪው ቡድን ለፈፀማቸው ጥሰቶች ሁሉ በወንጀል ተጠያቂ የሚሆንበትን ምህዳር በማመቻቸት በኢትዮጵያ ላይ የፈጸመችውን አድልዖ እና በደል በመጠኑም ቢሆን መካስ እና ግንኙነቷን ወደ ቀደመው ሁኔታ መመለስ እንደምትችል ምሁራኑ ባሰፈሩት ጽሑፍ መክረዋል።

Related posts:

ቴድሮስ ስልጣናቸውን በመጠቀም የሕወሓትን አላማ ማስፈጸማቸውን እንዲያቆሙ ተጠየቀ
«ሕወሓት ጦርነትን እንደ አምልኮ የሚቆጥር ቡድን ነው» – ፕሮፌሰር ሀረገወይን አሰፋ
«በሕገወጦች ላይ ያለ ምኅረት እርምጃ መውሰድ አለብን፤ ይህ የመንግሥት ተግባር ነው» የአማራ ክልል
125 አዳዲስ የገጠር ከተሞችና መንደሮች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ
«በአገሩ መከላከያ ላይ አፉን የሚከፍት ሕዝብ የለም፤ መንግስትም አይታገስም» ክብር ለመከላከያ ሰራዊት!!
በኢትዮጵያና ቱርክ መካከል የተደረገውን የወታደራዊ ማዕቀፍ ስምምነት ምክር ቤቱ አጸደቀ
የሞት ፍርደኛው የ25 ዓመታት ሰቆቃ! ከመሬት በታች የታፈኑት አባት
«ኢትዮዽያን ማስቀጠል ከሚፈልጉት ጎን በመሆናችን የሚከፋ ከአለ እርሱ መፍረሷን የሚናፍቅ ብቻ ነው!»
የኦሮሞ ዞን ምክር ቤት ጥብቅ ገደብ ጣለ
ደብዳቤ ለኢትዮጵያ - ከቢልለኔ ስዩም
የዓለም ባንክ የ300 ሚሊየን ዶላር የድጋፍ ስምምነት ፈረመ
"እናቴ ፍጹም እስር ቤት እንድትገባ አልፈግም" ብሎ እግሩን ያጣው ወጣት ምስክርነት ለሮይተርስ
"አልዘምትም" ወይም "ከጠላት ጎን እሰለፋለሁ" ማለት ሲቻል ማውሰብሰብና ማድበስበስ አይገባም!
አብዱላሂ ፋርማጆ ለአዲሱን ፕሬዝዳንት «ሁሉም ወገኖቼ እንዲደግፉህና እንዲጸልዩልህም እጠይቃለሁ»
የ18 ዓመቱ ጎረምሳ በኒውዮርክ የገበያ አዳራሽ በጥይት እሩምታ አስር ሰው አጠፋ

Leave a Reply