ኦብነግና ሙስጣፌ ዑመር ከስምምነት ደረሱ፤ ስምምነቱ በኬንያ እየተሰባሰቡ ላሉት አስደንጋጭ ሆኗል

የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር ለሁለት ከተከፈለ በሁዋላ ዋናውን ሃይልና አቅም እንደያዙ የሚነገርላቸው አቶ አብዱራህማን ማህዲ ማዴ ከሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጣፊ ዑመር ጋር ተከታታይ ውይይት ሲያካሂዱ ቆይተው ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ለኢትዮ12 የመረጃ ምንጭ የደረሰው መረጃ ያመልክታል። ስምምነቱ ይፋ ባይወጣም ኬንያ ላይ ተሰባስበው ሃይል ለመግንባት ሲሰሩ በነበሩት አካላትና አስተባባሪያቸው ዘንድ ያልተገመተ መሆኑ ተመልክቷል።

የኢትዮጵያ መንግስት ባደረገው ጥሪ መሰረት ወደ አገራቸው ከገቡት የፖለቲካና የነጻ አውጪ ድርጅቶች መካከል አንዱ የሆነው የኦጋዴን ነጻ አውጪ ግንባር አንዱ ነበር። ድርጅቱ ከኤርትራ ጉዙእን ጠቅልሎ ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ 1,740 የሚሆኑት የታጠቁ የሰራዊት አባላቱ ትጥቅ እንዲፈቱና የክልሉን የጸጥታ አካል እንደ አግባቡ እንዲቀላቀሉ መደረጉም ይታወሳል።

በክልሉ ከገዢው ፓርቲ ጋር በመልካም ጅማሮ ሲነቀሳቀስ የነበረው ኦብነግ፣ ብዙም ሳይቆይ ቅሬታ ሲያሰማና ትህነግ ከሰበሰበው “የፌደራሊስቶች ሃይሎች” ጋር ግንባር ፍጥሮ በመጨረሻ በተለያዩ ምክንያቶች ” ቅር ብሎኛል” በሚል ራሱን ከምርጫ በማግለ ሁሉ አቀፍ የፖለቲካ ውይይት እንዲደረግ አስታውቆም ነበር። የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም ከሚጠይቁት ወገን በመሆንና በሌላ የውስጥ አለመግባባትም ሲናጥ የቆየው ይህ ድርጅት ከምርጫ መውጣት ብቻ ሳይሆን የመከፈል አደጋም እንደደረሰበት ሲዘገብ ነበር።

“… በቀጣይ በሰላማዊ መንገድ እንሰራለን ፣ ለሶማሌ ህዝብ መብቶች መከበር በሰላማዊ መንገድ እንታገላለን፡፡ በኢትዮዮጵያ የሚገኙ ፓርቲዎች ውጥረት  እንዲሁም ጦርነትን አቁመው ወደ ውይይት በመግባት ለችግሩ መፍትሄ እንዲያመጡ  ጥሪ እናቀርባለን፡፡ በኢትዮጵያ ብሄሮች መካከል ትልቅ ክፍተት አለ ፡፡ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ባሉ ቡድኖች እርስ በእር አለመግባበት አለ ስለሆነም ወደ ውይይት መጥቶ መነጋገር እና ችግሮቻችንን መገንዘብ አለብን፡፡ በእውነቱ በሀገር ውስጥ ያለውን ችግር  ዝቅ አድርገን አንመልከትም ስለዚህ ችግሩን ለመፍታት የበኩላችንን ለመወጣት ዝግጁ ነን” ብሎ መግለጫ ከበተነ በሁዋላ የተከፈለው ድርጅት ትልቁና ወሳኝ የሚባለው ሃይል አሁን ላይ ወደ ስምምነት መምጣቱ ተሰምቷል።

ዜናው ይፋ ባይሆንም እንደተሰማው ከሆነ ንግግሩ የተጀመረው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አቶ ሙስጣፌ ዑመርን አዲስ አበባ አስጠርተው እስር፣ ማዋከብና አለመግባባት የሚፈጥሩ ጉዳዮች ቆመው ከፓርቲው ጋር ስምምነት እንዲደረግና ውይይት እንዲጀመር ባዘዙት መሰረት መሆኑ ተሰምቷል። ኢትዮጵያ በሶማሌ ላንድ ወደብ የ19 በመቶ ባለድርሻ በመሆኗና ቀጣይ የማዕድን ማጓጓዣ አማራጭዋ በሶማሌ ድንበር ስለሆነ፣ የባብ ኢልማንደብ ሰርጥ አዲስ ፖለቲካም ማተንጠኛው እዛው በመሆኑ የሶማሌ ክልል ፖለቲካ በመቻቻልና በጋር ትብብር መከናወን እንዳለበት በርካታ ምሁራንና ባለሙያዎችም ሲጠቁሙ ነበር።

አቶ ሙስጣፊ ያለማንም አገናኝና አደራዳሪ በቀጥታ ሰፊውን ሃይልና አቅም ከሚመሩት አቶ አብዱራህማን ማህዲ ማዴ ተከታታይ ውይይት በማድረግ ከትናንት በስቲያ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ዝግጅት ክፍላችን አረጋግጧል። ስምምነቱ በትህነግ አማካይነት በሶማሌ ክልል ላይ ተቃዋሚ ለመትከል ኬንያ ላይ ለተጀመረው ድግስ አስደንጋጭ ሆኗል። ኬንያ በግዛቷ ኢትዮጵያን የሚተናኮሉ ሃይሎችን አሳልፋ ለመስጠት ከስምምነት ላይ መድረሷን ተከትሎ ይህ ዜና መሰማቱ ነገሩን ይበልጥ አስደንጋጭ አድርጎታል።

ዲቪድ ሼን እውቅና ያላገኘችውን የስማሌ ላንድ ፕሬዚዳንት ዋይት ሃውስ መጥራቷ፣ በመካከለኛው አረብ አገሮችም እነ ሳኡዲ አረቢያ ተመሳሳይ ግብዣ ማከናወናቸው ለፕሬዚዳንት ፎርማጆ ልዩ መልዕክት ለማስተላለፍና ኢትዮጵያ፣ ኤርትራና ሶማሊያ የጀመሩትን ህብረት ለመፈትን ቢሆንም ኦብነግና ከትህነግ እቅፍ ወጥቶ ሙሉ በሙሉ በክልሉ አብሮ የመስራት እድል በሚያገኝበት ደረጃ ምስማማቱ ዜናውን እንደሚያጎላው የዜናው ባለቤቶች አምለክተዋል።

ኦበነግ ትህነግ በመራው የሽግግር መንግስት ወቅት ተሳትፎ ከሰባት ወር በሁዋላ የተገለለ፣ ከዛም ” አሸባሪ” ተብሎ የተፈረጀና ከለውጡ በሁዋላ ከሽብር መዝገብ ተፍቆ በክብር አዲስ አበባ አውሮፕላን ማረፊያ በአቀባበል ለአገሩ ምድር የበቃ ድርጅት ነው።የምዕራብ ሶማሌያ ነጻ አውጪ በሚል ስያሜ የተቋቋመና በሶማኤ ጦርነት ወቅት በዚያድባሬ ሲታገዝ እንደነበር ታሪኩ ያስረዳል። በውቅቱ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ትህንግም በተመሳሳይ ከዚያድባሬ ጋር ሆኖ ኢትዮጵያን መውጋቱ በራሱ አመራሮች መመስከሩ አይዘነጋም። ኦብነግ የዜያድባሬ ሃይል ሲመታ ኦብነግ የሚለውን ስም መያዙ እንደያዘ ስለድርጅቱ የተጻፉ መረጃዎች ያስረዳሉ።

Leave a Reply