ንፋስና ብስጭት – የቤተመንግስት ግብዣ ልዩ ቢፌ

“… በእርግጠኛነት እነግራችኋለሁ ውጤቱ ግሩም ይሆናል። እናንተም ባትሆኑ ቤተሰቦቻችሁ ለአምስት ዓመት ኮንትራት ሰጥተውናል። አገር አንበትንም። … ከትህነግ ጋር ሳይሆን ከትግራይ ሕዝብ ጋር ጉዳይ አለን። የትግራይ ሕዝብና እኛ መካከል የናዚና የአይሁድ አይነት ቂም የለም።” ሲሉ የወታደራዊ ዘመቻውን መከራና ጀግንነት በማንሳት ሲናገሩ በታላቁ ቤተ-መንግስት በተካሄደው የእራት መርሀ ግብር የታደሙ እንግዶች ከመተንፈስ ውጭ ሌላ ነገር ማድረግ አይችሉም ነበር። ንግግራቸው ልብን የሚነካ፣ በተስፋ የሚሞላና በመከራ ውስጥ ያለን ልዕልና የሚያመላክት ነበረና የስሜት መደበላለቁ ከፈተኛ ነበር።

“ሲጀመር ፈጣሪዬ ከኔ ጋር ባይሆን አይሆንም አሸነፍኩ ብዬ የፈጠሪን ክብር አልውስድም” ሲሉ- የራሱን ሽንት እየጠጣ ሶስትና አራት ቀን ስለሚጓዘው ጀግና ወታደር ሲናገሩ አይኖች እንባ ያቆረዘዙ;; “ፈጣሪ ምን እንዳደረግ አውቃለሁ” እንግዶች በድንገት በደስታና በምስጋና የልብ መለከት መንፋት ጀመሩ ;; ይህ ሲሆን ዝምታ የዋጠው እድምተኛ ተነስቶ ስሙ ለተነሳው ፈጣሪ ክብረ ሰጠ።

“እስረኛ ስንፈታ ቀድመው የጮኹት እነሱ ናቸው። ምክንያቱም ምን እንደምናተርፍ ያውቁታል” ሲሉ አብይ አምላክን ለማመስገን ለተነሱት ሁሉ “ክብረት ይስጥልን” ካሉ በሁዋላ።”የእናንተ መምጣት የአፍሪካ መሪዎች ስብሰባ እንዲደረግ አስወሰነ” አሉና የቤቱን የደስታ ሞገስ አነደዱት። በቤተ መንግስት ብቻ ሳይሆን በጸሃይና በብርድ ለአገሩ አንድ ሆኖ የጮኸው ዲያስፖራ አገሩ ከዓለም ዓቀፍ ድግስ እንድትጎድል ያበረከተው አስተዋጾ ታላቅ ውጤቱ አኮራው። አብይ በዚህ አላቆሙም ” አጸንፋችሁ ይቅርታ አደረጋችሁ። እመኑኝ ውጤቱ ታላቅ ነው” ሲሉ በተረት እንደሰየሟት ንግስት የዩቲዩብና ማህበራዊ ሚዲያ አድማቂዎችን በመስማት ከዚህ ታላቅ ማማ ላይ መውረድ እንደማይገባ አስታወቁ።

“በኪሳችሁ ይዛችሁ ከመጣችሁት በላይ ኢትዮጵያን ከማስከበር አንጻር የተጫወታችሁት ሚና ትልቅ ነው” በማለት አመስግነው። ለኢትዮጵያዊ ዲያስፖራ የሚገባውን ክብር ሲሰጡ፣ አያያዙና “ውጡ ውጡ ስንባል እምቢ ብለን …” በሚል የነበረውን ጫና አመላክተው ዛሬ ላይ መደረሱ የአንድነት ውጤት ስለሆነ ይህ መቀጠል እንዳለበት አስረግተው አሳሰቡ።

“ካሸነፋችሁ በሁዋላ እስረኛ ተፈታ ብላችሁ ማሊያችሁን ካወለቃችሁ ኢትዮጵያዊ አይደላችሁም” ሲሉ ከይቅርታው ውስጥ ህብስት ስለመኖሩ ያመለከቱት በትግራይና በኢትዮጵያ ህዝብ መካከል ልዩነት እንደሌለ፣ ልዩነቱ ያለው ክትህነግ ጋር ብቻ መሆኑንን መረዳት ግድ መሆኑንን በማስረገጥ ነው። እንኳንም አሸንፈን ይቅርታ ለማድረግ አበቃን። ሲሉም ሌላው ተቃራኒ ጉዳይ ሆኖና የጠላት አሳብ ተሳክቶ ቢሆን ኖሮ ምን ሊሆን ይችል እንደነበር ጠቆም አድርገው በፈገግታ አለፉ።

ለአንድ ሙሉ ትውልድ ዕድሜ ተከርችሞ በኖረው የኢትዮጵያ ቤተመንግስት ውስጥ መዛናናት፣ ፎቶ መነሳት፣ በተለይም ቤተ መንግስት ግብተው ለመስተናገድ እድል ያገናሉ ተብሎ የማይታሰብ የህብረተሰብ ክፍሎች / ምስኪኖች/ ቤተመንግስት ገብተው መብላት፣ መጠጣትና መስተናገዳ የጀመሩት አብይ አሕመድ ወደ ስልታን ከመጡ በሁዋላ ነው።

ትምህርት ቤት መዋል አቅቷቸው ረሃብ የሚደፋቸው ሕጻናት በቋሚነት አገራቸው ምግብ እንድታበላቸው፣ የመማሪያ ቁሶችና የመለያ ልብስ እንድታለብሳቸው የተደረገው አሁንም የበሻሻው አብይ ወደ ስልታን ከመጡ በሁዋላ ነው። ከሁሉም በላይ አስደናቂው ደግሞ በፖለቲካ አመለካከታቸው ሳቢያ ከአገር የተሰደዱ ኢትዮጵያዊያን ወደ አገራቸው እንዲገቡ የተወሰነው ውሳኔ ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መንግስት “ጸሃዩ” የሚል ውዳሴ ያጎናጸፈ ነበር። ብዙ ያልተለመዱና በዚህ ትውልድ ዘመን ይደረጋሉ ተብለው ያልታሰቡ በረከቶች ሆነውም ነበር።

“አልዓዛር ሃይሌ ቤተመንግስት ገብቼ ባየሁትና በሰማሁት ሁሉ የተሰማኝ ስሜት እንዲሁ በቀላሉ ከውስጤ የሚወጣ ሆኖ አላገኘሁትም” ሲል አስተያየቱን የሰጠው በዚሁ መነሻ ይመስላል። ከሃያ ሁለት ዓመታት በሁዋላ ወደ አገሩ የተመለሰው አልዓዛር፣ እንዳለው ሁሉ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ትውልደ ኢትዮጵያዊያንና ኢትዮጵያዊያን በተደረገላቸው አቀባበል ደስተኞች ናቸው።

መንግስት ግን “ያጎደልኩት ካለ ከልምድና ከአቅም እጥረት ሊሆን ይችላል እንጂ በሌላ ምክንያት አይደለም” ሲል ከዚህ በላይ ቢያደርግ ደስተኛ መሆኑንን አመልክቷል። ይቅርታም ጠይቋል። ይቅርታ የጠየቀውም በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አማካይነት፣ በቤተ መንግስት፣ ከማዕድ በፊት በተደረገ የመግቢያ ንግግር ነው። እገረ መንገድም ” ተደናግራቸኋል ይባላልና አንዳንድ ነጥቦች ላንሳ” ሲሉ አብይ አህመድ የመግቢያ ንግግራቸውን ስንቅ ወደማስጨበጥ ቀየሩት።

የዲያስፖራ አባላት ገና ወደ አገር ቤት መግባት ሲጀምሩ ” በሄዳችሁበት ሁሉ ያያችሁትን በሙሉ በመረጃ ቋታችሁ ይዛችሁ በምትሄዱበት ሁሉ ዲፕሎማት ሁኑ፤ እውነትን በማስረጃ ታጠቁና ዝመቱ” ተብሎ ነበርና አብይ አህመድ “የተምታታ” ስለተባለው ስሜት ቀበኞች እንዳሻቸው እየተረጎሙ ለማሰናከያ ስለሚጠቀሙበት ወቅታዊ ጉዳይ አነሱ።

“ምንም ነገር ስናደርግ ሶስት መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ተንተርሰን ነው” ሲሉ ጀመሩ። ነገሩ በትህጋራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር መሪ አቶ ስብሃት ነጋና ቤተሰቦቻቸው መፈታት ጋር በተያያዘ የተነሳውን የተራራቀ አሳብ በበቂ ግንዛቤና በበቂ አመክንዮ ማስረዳት ዴያስፖራውን ማስታጠቅ ነውና ጭብጨባ ተለገሰው።

በኢትዮጵያ ሏአላዊነት የመዳደር ስብዕናም ያለው መንግስትም ሆነ ግልሰብ የለም ሲሉ አንደኛውንና አንኳር የሆነውን ጉዳይ አስታወቁ። እንዲህ ያለ ስብዕና ያላው መንግስት እንደሌለ ባለፉት ጥቂት ቀናት እንደተረጋገጠ አመልክተው ” በዚህ ጉዳይ አሳብ አይግባቹህ” አሉ። “ለዚህች አገር ምን ዓይነት ብሄራዊ ጥቅም ያስገኛል” በሚል መመዘኛ ማንኛውም ጉዳይ እንደሚታይ አመለከቱ። ሶስተኛው ደግሞ ምን ደሃ ብትሆንም ኤትዮጵያና ሕዝቧ አገራዊ ክብራቸውን አሳልፈው እንደማይሰጡ ባህላቸው፣ ታሪካቸውና ገድላቸው ሁሉ ምስክር ነውና ይህን የኖረ አቋም ሊለውጥ የሚችል አንዳችም ነገር እንደማይኖር አረጋገጡ።

“አንድም አገር ጠላት ብለን አንፈርጅም” ሲሉ አብረው ኢትዮጵያን ብመደገፍ ለዘለቁት ምስጋና ያቀረቡት አብይ ” ወደ አሳባችን ከተመለሱ እናስተናግዳቸዋለን” ሲሉ የሰሞኑንን የፖለቲካ ለውጥ አዙረው ጠቆም አድርገዋል። ሁሌም ” ክብራችንን እወቁ በሚል ወደ እኛ አሳብ በማቅረብ አክብረውን እንዲሰሩ እናደርጋለን” ሲሉ ከላይ ያስቀመጧቸው ሶስቱ መርሆች እንደማይገረሰሱ አስታውቀዋል።

“ብሄራዊ ንግግር ይደረግ ሲባል ቅድመ ሁኔታ እንዲቀመጥ የሚጠይቁ አሉ” ሲሉ ወደ ዋናው ጉዳይ የዘለቁት አብይ “ኢትዮጵያዊያን ከጫፍ ጫፍ መገንጠልን ይደግፋሉ ብዬ አልምንም። ይሁን እንጂ አስርና አስራ አምስት ሰዎች ይህን ቢያስቡ ተነጋግረን ወደ እኛ አሳብ እንዲመጡ እንወያያለን” ሲሉ አንድነት ጠቀሜታው ምን ያህል የጎላ እንደሆነ በዲስኩራቸው አመልክተዋል። “የውይይቱና የንግግሩ ፍሬ ሉዓላዊነት፣ ክብር እንዲሁም አንድነት የማይነካ ከሆነ መላዘብ ግድ ነው” ያሉት አብይ አሕመድ ትልቁን ስዕል በመመልከት ሆንደ ሰፊ መሆንና የአሸናፊነት ስሜት ውስጥ ሆኖ መሃሪ መሆን አሁን ላይ የሚፈለግ ዋና ነጥብ መሆኑንን ገልጸዋል።

“በአየር የተሞላ ፊኛና በንዴት የተሞላ ልብ አንድ ናቸው። በአየር የተሞላ ፊኛ ተጨማሪ አየር ከተሰጠው ይፈነዳል። በጥላቻ፣ በተንኮልና በቂም የተሞላ ልብም በቀጣይነት ብስጭት ከተመገበ ይፈነዳል። ስለዚህ ለማርገብ ከንፋሱም፣ ከብስጭቱም ቀነስ ማድረግ ያስፈልጋል” ሲሉ የመነጋገርንና፣ በመነጋገር ስለሚገኘው ውጤት አስፈላጊነት ያመለከቱት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በዚህ መንገድ ብቻ ሲሆን አገርን ለልጆችና ለቀጣይ ትውልድ ማሻገር እንደሚቻል አበክረው አስታውቀዋል።

አብይ አህመድ “ታስረው የተፈቱም ሆነ በይቅርታ ወደ አገር ቤት የገቡ እንደ እኔ ያዋረዱትና የሰደቡት ሰው የለም” አሉና “የግል ጉዳይ ስላልሆነ አባቶቻችን እየጋበዙ፣ እየጠቁና እየተመካከሩ እንዳደረጉት እኛም እየመከረን በይቅርታ ስሜት አገር እናቀናለን” ሲሉ ምንም ጉዳይ ክገል ነገር ጋር እንዳይያያዝ መክረዋል።

ናዚ 5 ሚሊዮን አይሁድ መፈጀቱን አስታውሰው በትግራይና በሌላው ሕዝብ መካከል ያን ያህል ልዩነት እንደሌለለ በማመልከት” በይቅርታ ስሜት በምትሄዱበት ሁሉ ይህን አስተምሩ።” ሲሉ አብይ አሕመድ እንግዶቻቸውን የዲያስፖራ አባላት የለቱን ትጥቅ አስታጥቀዋል። “ይቅርታ ለነገ እንጂ ለትናንት አይደለም። በደል በደልን እየወለደ እንዳይሄድ የሚደረግ ነው። ስለዚህ ነገሮችን በዚህ መልኩ ተመከቱ” ሲሉም ሆን ብለው ከሚያደናግሩ ራሳችውን እንዲጠብቁ ነገረዋል።

“ብዙ ነገር ለመናገር አይመችም” ብለው ” አንድም መንግስት ይፈቱ ብሎ የጠየቀኝ የለም ” ሲሉ አሁን ክሳቸው የተቋረተላቸው ወገኖች እንዴት ሊፈቱ እንደቻሉ፣ ደነገጥኩ ንያሉበትን ምክንያትና መስለ ተያያዥ ጉዳዮች በትነው አስረድተዋል።

ትህነግ ደብረ ሲና ደርሶ እያለ “ደብረሲና ደርሰዋል ገብተው ከሚፈቷቸው እኛ እንፍታ ያሉ ከፍተኛ አመራሮች ነበሩ” ሲሉ በመጠኑም ቢሆን ሚስጢር ይፋ ያወጡት የኢትዮጵያ ተቅላይ ሚኒስትር፣ “የለም ወያኔም አዲስ አበባ አይገባም እናሸንፋቸዋለን” በሚል የጸና አቋም ለዛሬ መደረሱን አስታወቀዋል።

የመከላከያ ከፈተኛ መኮንኖችን ሹመት አንስተው ” አዝናለሁ” ሲሉ የተሰራውን የሚያስመሰግን ስራ ካወሱ በሁዋላ ” ማንም ሆነ ማን የኢትዮጵያን ከፍታ በሚነካ መልኩ የሚነቀሳቀስ ከሆነ እንደ ወያኔ ይደመሰሳል ሲሉ ለራሳቸው መኮንኖች ሳይቀር በይፋ ማስጠንቀቂያና ምክር ሰንዘረዋል።

Leave a Reply