“መለኮታዊ አገዛዝ” የተባለው የትህነግ ዘመን የውስጥ ቀውስ

መልሶ ማጥቃቱ በስኬት ከተጠናቀቀ በሁዋላ ትግራይን ታኮ የሚወጡ መረጃዎችና የሚታየው የአቋም ለውጥ፣ እንድሁም የአቋቋም መለያየት ቀጣዩ አጀንዳ እንደሚሆን ምልክት ነበር። ምልክቱ እያደር ገሃድ እየወጣና የሚዲያ ቁርስ እየሆነ ነው። ከዚህም መካከል አንዱ ትህነግ ላይ የተነሳው ” የሽግግር መንግስት” ጥያቄ ነው። ሌላውና ትልቁ ውስጥ ውስጡ እየቦካ ያለውና ሊፈነዳ የደረሰው ዜና “ትጥቅ ፍቱ” የሚለው ጉዳይ ወደ ማብቂያው ማምራቱ ሆኗል።

“ፕሬዚዳንት ባይደን ትህነግ የመዋጋት አቅሙና የተተኳሽ ቁሱ ስለተሟጠጠ አመራሮቹ እጃቸውን እንዲሰጡ ያድርጉ” ሲል አትላንቲክ ካውንስል ያወጣውን ሰፊ ሃተተታ ተከትሎ ብዙም ሳይቆይ ፕሬዚዳንት ባይደን ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መደወላቸውና የተሳካ ውይይት ማድረጋቸው ዜና መሆኑ ዝም ብሎ ግጥምጥሞሽ እንዳልሆነ ፖለትከኞች ያስታወቁት ወዲያው ነበር። ይህ ዜና ሊሰማ አካባቢ በትግራይ ፓርቲዎች ከወዲሁ “በድርድር አለሁበት” ሲሉ ድምጻቸውን አሰሙ።

ሟቹ የትህነግ ሊቀመንበር አቶ መለስ ዜናዊ ያገለሏቸው እነ ስዬ፣ ጻዳቃን፣ ተወልደና የመሳሰሉት ከፊት ሆነው ይመሩታል የሚባለውና በኖርዌጂያኑ ፕሮፌሰር ሼትል ትሮድቮል አማክይነት “የትግራይ መከላከያ ሃይል” የሚል ስም የወጣለትን ሃይል፣ ከትህነግ ይልቅ ትህነግ እንዳቋቋማቸው በሚነገርላቸው “የዓላማ ወራሽ” ድርጅት አመራሮች ጋር በተንቤን በረሃ ጥብቅ ግንኙነት እንደገነቡ ይሰማ ነበር። ይህ ግንኙነት አድሮ ሃይል እየሆነ ሲሄድና የልዩነት ቁልፍ ጉዳይ እየሆነ ሲመጣ ደጋፊንና አባላትን ለማረጋጋት አምስት መኮንኖች ሚዲያ ላይ ቀርበው ” ቲዲኤፍ የሚታዘዘው በትህነግ ነው” ሲሉ መግለጫ ሰጡ። ቢቢሲ የህዝባዊ ማዕበል መንጋ በማዝመት የነደፉትን ጦርነት አድንቆ ” ምጡቅ” ያላቸው ሌተናል ጀነራል ጻድቃን ግን አልነበሩም። እንዲያውም ቆየት ብለው ” የግሌ አሳብ ነው “ሲሉ ጽሁፍ አሰራጩ።

በጽሁፋቸው አሜሪካ እንደከዳች የሚያመላክቱ የጉንጭ ውስጥ አሳባቸውን አስፍረው እንደነበር፣ አቶ ጌታቸውም ቀደም ብለው በተመሳሳይ አሚሪካንን ወቅሰው ስለነበር አንድ ላይ ተዳምሮ አጅንዳው በአምባሳደር ፌልትማን ተጠቀለለ። ” 1991 ላይ የተቸከሉ፣ የማይሰሙ” ሲሉ ፌልትማን በገሃድ ትህነግን ኮነኑ። ይህን ተከትሎ በትግራይ እያበበ የመጣው አዲስ አሳብ ሳይሆን እንቅስቃሴ የሚያረጋግጡ መረጃዎች አየር ላይ ይንሳፈፉ ጀመር። “እንወደድ ባዮችን” ያሳፈረው መረጃ ምን ውጤት እንደሚያስከትል አድሮ የሚታይ ቢሆንም አዲስ ነገር ለከሰቱ ግን ጥርጥር እንደሌለ የሚናገሩ ጥቂት አይደሉም። አብይ አሕመድ ” እመኑኝ መልካም ነገር አለ” ሲሉ፣ ራሳቸው የትግራይ ተውላጆች የሆኑና ከትህነግ ጋር አብረው ሲሰሩ የነበሩ “ትህነግ አሹቆናል። በቃው” ብለዋል።

በዚህ መነሻና በሌለኦች ጉዳዮች ተያያዥነት መንግስት ከአሜሪካ ጋር የሚግባባት አውድ ከተፈጠረ ትህነግ አደጋ ውስጥ እንደሚወድቅ አንስተው መገምገማቸው የተሰማው ከሶስት ሳምን በፊት ነበር። የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባር ባካሄደው በዚህ ግምገማ ጦርነቱ መቀጠል የማይችልበት ደረጃ ከተደረሰና የሱዳንን ኮሪዶር ማስከፈት ካልተቻለ የሚፈጠረውን ስጋት በግልጽ አስቀምጦ ጀንበር ሊጠልቅበት እንደሚችል ማንሳቱን የአሜሪካ ተባባሪያችን የግንባሩን መሪ ወዳጆች ጠቅሶ ነበር ያስታወቀው። ሙሉውን ከስር ያንብቡ


ጦርነቱ ካልቀጠለ ትህነግ በሁለት ምክንያቶች እንደሚከስም መገምገሙ ተሰማ

“በሱዳን በኩል የተቆለፈውን በር ማስከፈት ካልተቻለ፣ የውጭ ወዳጅና አጋዦች ጣልቃ የሚገቡበት ሁኔታ ካልተመቻቸ፣ ጦርነቱን መሸከምና መቀጠል ይከብዳል


አዲስ አበባ እንደሚገባ፣ የሚድን ነገርም ሆነ ስልጣን ስለሌለ ሁሉም የመከላከያ አባላት ለትግራይ ሃይል እጁን በአስቸኳይ እንዲሰጥ በየቀኑ መግለጫ ሲያወጣና የሽግግር መንግስት ለማዋቀር ሲጣደፍ የነበረው ትህነግ በሁለት ሳምንት ውስጥ የሆነው ሁሉ ሆኖ ወደ ትግራይ መመለሱን እንዳስታወቀ የተሰማው ነገር ቢኖር አሁን የተሰማው የልዩነት መስመር እንደሚነሳ ነው። ራሳቸውን እንደገመገሙት ሰላም ከወረደ የውስጥ ቀውሱ ትህነግን ማሻመዱ እንደማይቀር ነበር።

“የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግንባርን አገዛዝ የሚቃወሙ” ሲል የጀርመን ድምጽ የጠቀሳቸው ሳልሳይ ወያነ ትግራይ (ሳወት) እና ዉድብ ናፅነት ትግራይ (ዉናት) ትህነግን ” መከኮታዊ ስርዓት ለመትከል የሚሰሩ” ሲል ነው ” በቃ” ያለው። ድርጅቶቹ ከቀናት በፊት ይፋ ያደረጉት ጥያቄ የክልሉን ተወላጆች እያነጋገረ እንደሆነ አስታውቋል። ቢቢሲ “አላየሁም፣ አልሰማሁም” ሲል ጆሮ ዳባ ያለው ይህ ዜና ያሰማው አዋጅ ” በትግራይ የሽግግር አስተዳደር ይቋቋም” የሚል ነው። ሁለቱ ፓርቲዎች በቅርቡ በትግሪኛ ቋንቋ ባሰራጩት የአቋም መግለጫ ሕወሓትን «በስመ መከታ ፍፁም አፈናና ጭቆና የሰፈነበት መለኮታዊ ሥርዓት ለመትከል ተግባራዊ እንቅስቃሴ ጀምሯል» በማለት አብረውት ለግማሽ መዕተ ዓመት ያኗኗሩትንድርጅት ኮንነዋል።


To End Ethiopia’s War, Biden Needs to Correct Course

… But if it were to call for surrender of the TPLF leadership, the United States might at least be positioned to exert some constructive influence on peace talks between the Ethiopian federal government and Tigray, including which parties and individuals are included in those talks—especially if it offers to help foot the reconstruction bills.


አስር ነጥቦችን የያዘዉ የሁለቱ ፓርቲዎች የአቋም መግለጫ የትግራይ ሕዝብ ለሚገኝበት (የችግር) አዙሪት መነሻዉ «ብቁና ቆራጥ ብሔራዊ  አመራር ማጣቱ ነዉ» እንደሆነ አክለው ገልጸዋል። የትህነግን ሽንፈት ተከትሎ ” መለኮታዊ ስርዓት ተካይ፣ ብቁና ቆራጥ ያልሆነ” በሚሉ ከባድ ቃላቶች የተዘለዘለው ትህነግ፣ ውግዘት በዚህ ደረጃ ሲቀርብበት ከህንፍሽፍሽ ዝመን ቀጥሎ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።

ሁለቱ ፓርቲዎች በዚህ ወቅት ይህን አቋም እንዲይዙ ያነሳሳቸዉ «ትግራይ ለወደፊቱ ሰብአዊ መብቶች የሚረገጡባት፣ሁሉም ዓይነት ወንጀሎች የሚፈፀሙባት፣የተዘጋችና የተነጠለች ሐገር እንድትሆን አደጋ ስላንዣበበባት ነው” ሲል መግለጫው ስጋቱን እንዳስቀመጠ የጀርመን ድምጽ ዘግቧል። መግለጫዉ አክሎ «እንደ ሕዝብ ከገባንበት አዘቅት መዉጣት የምንችለዉ መሬት ላይ ያለዉን ነባራዊ ሐቅ (በመገንዘብ) እንደሆነ የዘመኑ ብቸኛ አማራጭ ነዉ።» ሲል ለውጥ የግድ አስፈላጊ እንደሆነና “መለኮታዊ” ያለው አካሄድ ሊያከትም እንደሚገባው ገልጿል።

ፓርቲዎቹ እንዲመሠረት የሚሹት የሽግግር አስተዳደር ትግራይን «የሚያድን ወደ ሐገርነት የሚያሻግር፣ከድርጅታዊና ቡድናዊ ጥቅም ይልቅ ለሕዝብ ሕልዉናና ጥቅም ቅድሚያ የሚሰጥና ሁሉንም ወገኖች ያካተተ መሆን አለበት” የሚሉት ሁለቱ ድርጅቶች፣ የሽግግር አስተዳደር እንዲቋቋም ሲደረግ እንዴትና በምን መልኩ ትግራይን እንደሚያድኗት፣ አሁን የተፈጠረውን ቀውስ እንዴት እንደሚፈቱት አላብራሩም። ይሁን እንጂ ሕወሓት ትግራይን ሙሉ በሙሉ ከተቆጣጠረበት ጊዜ ጀምሮ ባለፉት አርባ ዓመትት ከትግራይ ጠንካራና ግልፅ ተቃዉሞ ሲገጥመዉ ይህ የመጀመሪያ እንደሆነ ዜናውን ከመቀለ የዘገበው የጀርመን ድምጽ ዘጋቢ አመክቷል። ዘጋቢው “ታዛቢዎች እንደሚሉት” በማለት ሁለቱ ፓርቲዎች ትግራይ ክልል ከአዲስ አበባ ማዕከላዊ አስተዳደር ተነጥሎ የራሱን ነፃ መንግሥት እንዲመሰርት የሚያቀነቅኑ እንደሆኑ አመልክቷል።

የአረና፣ ባይቶናና አሲምባ እንዲሆም የራሱ የትህነግ አቋምና ምላሽ ምን እንደሆነ በዘገባው አልተካተተም። ይሁን እንጂ ዜናውን የሰሙ የትግራይ ተወላጆችና የትህነግ አፍቃሪዎች በትግራይ ህዝብ የመረጠው ብቸኛ ድርጅት ትህነግ ስለሆነ አምስት ዓመት የስልጣን ጊዜው ሊጨርስ እንደሚገባ እየተከራከሩ ነው። ለጊዜው ይፋ አይሁን እንጂ ሰፊ መሰረት ሊኖራቸው የሚችሉ ድርጅቶች እየተቋቋሙ መሆኑ እየተሰማ ነው። ድርጅቶቹ ከአማራና ከአፋር እንዲሁም ከኤርትራ ህዝብ ጋር የተፈጠረውን ቂም በማጽዳት የትግራይን ሕዝብ ወደ አዲስ የፖለቲካ ሽግግር እንደሚወስዱ እየተገለጸ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ድርድሩ ሌላ አማራጭ ዮ እንደሚመጣ ይጠበቃል።

የእነ አቶ ስብሃት ነጋን መፈታት ተከትሎ ትግራይን በሚመለከት እየወጣ ያለው ተከታታይ ዜና በጀመረው ፍጥነት አዳዲስ ነገሮችን ይዞ እንደሚወጣ ይገመታል። የትህነግ ባለስልታኖች በምህረት ኮሪዶር ተከፍቶላቸው ወይም በበጎ አድራጊ ድርጅቶች አማካይነት ከአገር እንዲወጡ ሃሳብ መቅረቡም የሚታወስ ነው። ይህን አስመልክቶ ትህነግ በይፋ ያለው ነገር ባይኖርም በአፋር በኩል ዕርዳታ ማስገባት ስላልተጫለ በሱዳን በኩል ኮሪዶር እንዲከፈት የረሃቡን ዜና እያጎላ እንደሆነ ይታወቃል። ትህነግ አውቆ በፋር በኩል ጦርነት እንደከፈተ የአፋር ክልላዊ መነግስት መግለጫ ማውጣቱም ይታወሳል። መንግስት በበኩሉ በሱዳን በኩል ኮሪዶር የማይታሰብ እንደሆነ በተደጋጋሚ ይፋ አድርጓል።

Leave a Reply